EPISODE · Dec 15, 2025 · 30 MIN
የውጭ እርዳታ መቀነስ፡ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ተስፋና ስጋት
from The Rising South
“የውጭ እርዳታ ማጣት በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው […] ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ እና ወባ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን ግዥ ያለ እርዳታው በተግባር የማይቻል ነው። ነገር ግን አርቀን ስንመለከት ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል። ለአፍሪካ ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ ወይም ጤና ብቻ ሳይሆን ለእርሻ፣ ትምህርት እና ሌሎችም ሀብትን በማሰባሰብ በራሷ ላይ ለመደገፍ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።” ሲሉ የ'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በቲቢ በሽታ ከፍተኛ ጫና ካለባቸው አገሮች መካከል የሆነችው ኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቷ ዋነኛ የጀርባ አጥንት የነበረው የውጭ እርዳታ እየቀነሰ በመምጣቱ ወሳኝ ወቅት ላይ ትገኛለች። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ የቲቢ ቁጥጥር ጥረቶችን ማለትም ምርመራን፣ ሕክምናን እና የመድኃኒት መቋቋምን አደጋ ላይ እየጣለ ነው። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ከ'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፍቃዱ ጋር በመሆን የጤና በጀት ቅነሳ በኢትዮጵያ የሳንባ ነቀርሳ ህክምና ላይ የሚያሳድረውን ተጨባጭ ተፅዕኖ ዳስሰናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
የውጭ እርዳታ መቀነስ፡ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ተስፋና ስጋት
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.