EPISODE · Dec 4, 2025 · 1H
የውኃ ነገር፡ በቀጠናዊ አጋርነት እና ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር ፍትሃዊ ክፍፍል የሚሻው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት
from Sovereignty Sources
''ውኃ ጥቅም ብዙና ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ኃብት እንደመሆኑ በዋነኝነት አንዳንድ ሀገራት ለግብርና ሲያውሎት፣ አንዳንዶቹ ለሥራ ፈጠራ ዕድል፣ ሌሎቹ ደግሞ ኃይል ለማመንጨት ይጠቀሙበታል — ሀገራት እርስ በርስ በትብብር መሥራት የሚችሉባቸው መሠረቶቹ ሲኖሩ ደግሞ ከውኃ የሚገኘውን ከፍተኛ ኃብት መቋደስ ይችላል፡፡'' ሲሉ በውኃና መሬት ኃብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬከተሩ ጠና አላምረው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን የመጀመሪያ ክፍል ፍትሃዊ የውኃ ኃብት ክፍፍል በሀገራት መካከል እንዲፈጠር ቀጠናዊ አጋርነቶች እንዲሁም ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር መጠናከር በሚመለከት በውኃና መሬት ኃብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬከተሩ ጠና አላምረው (ዶ/ር) በእንግድነት ጋብዘናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና እንዲሁም ስትራተጂካዊ ግንኙነትን በደቡብ አፍሪካ የግብርና ቢዝነስ ምክር ቤት ዋና የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ዋንዲሊ ሲህሎቦ ያስረዱናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የውኃ ነገር፡ በቀጠናዊ አጋርነት እና ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር ፍትሃዊ ክፍፍል የሚሻው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.