EPISODE · Nov 20, 2025 · 1H
የዘረመል ንቅለ ተከላ እና ጂኦፖለቲክስ፡ የኢትዮጵያን የወደፊት ሁኔታ የሚቀርጹ ሁለቱ ኃይሎች
from The Rising South
“[ምዕራቡ ዓለም] ወጥመድ ውስጥ ለማስግባት ይሞክራሉ፣ ምክንያቱም በገንዘብ በሚረዱበት ጊዜ ሁሉ የራሳቸውን መስፈርት ያስቀምጣሉ። የአንተ ፍላጎት በእነሱ ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም።[...] አንተ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ መወሰን አለብህ። ለእነዚያም ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች ከሀገር ውስጥ ገንዘብ እንዲገኝ ማድረግ ይገባል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ጄኔቲክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ደረጀ በየነ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል የ የዘረመል ንቅለ ተከላ (Genome Editing) የአፍሪካን የምግብ ስርዓት፣ ሳይንሳዊ ሉዓላዊነት እና የመቋቋም አቅም እንዴት እየለወጡ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ጄኔቲክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ከሆኑት ከ ደረጀ በየነ (ዶ/ር) ጋር የተወያየን ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ወደ አፍሪካ ቀንድ ዲፕሎማሲና ደኅንነት ተሻግረን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በቅርቡ ባደረጉት ንግግር ዙሪያ፣ በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ በቀይ ባህር ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፈር በድሩ ( ዶ/ር) እና ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር የሰጡንን ትንታኔ አካትተናል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የዘረመል ንቅለ ተከላ እና ጂኦፖለቲክስ፡ የኢትዮጵያን የወደፊት ሁኔታ የሚቀርጹ ሁለቱ ኃይሎች
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.