የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ podcast artwork

PODCAST · society

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።

Publisher-supplied feed metadata · PodParley refreshed Aug 4, 2026 · Source feed

  1. 45

    ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ

    ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ እንደምን ከአገረ ኢትዮጵያ በጃፓን ዞረው ለአውስትራሊያ ምድር እንደበቁ፤ የትምህርት፣ የሥራ፣ የቤተሰብ፣ ማኅበረሰባዊና መንፈሳዊ ሕይወት ትስስሮሻቸውን አንስተው ያወጋሉ።

  2. 44

    "ሕይወት የጣለችብኝን ውጣ ውረድ ተወጥቻለሁ፤ ተስፋ ብቆርጥ ኖሮ አልኖርም ነበር፤ አሁን በሁለት እግሬ ቆሜያለሁ" ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም

    ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በአዲስ አበባ አራዳ የዕድገት፣ በሱዳን የስደትና በአውስትራሊያ የሠፈራ ከፊል ሕይወቷን አጣቅሳ በቀዳሚ ሁለት ከፍለ ዝግጅቶች አውግታለች። የመደምደሚያ ግለ ታሪኳ የሚቋጨው በምስጋና ጀምሮ በወደፊት ትልሞቿ ነው።

  3. 43

    ብዕሊ አድሃኖም፤ ከላጤ እናትነት እስከ ምሕንድስና

    ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት በለጋ የወጣትነት ዘመን ከአዲስ አበባ - አራዳ ተንስታ፤ የሱዳንን አዋኪ የስደት ሕይወት ገፍታና ለአቅመ ሔዋን ሳትደርስ የመጀመሪያ ልጇን አገረ አውስትራሊያ ውስጥ ለመገላገል እንደምን እንደበቃች አውግታለች። በቀጣዩ ትረካዋ የአውስትራሊያ የሠፈራ ኑሮን ተቋቁማ እንደምን ለምሕንድስና ባለሙያነት እንደበቃች አንኳር የሕይወት ጉዞ ተግዳሮቶችና ስኬቶቿን በመንቀስ ታነሳለች።

  4. 42

    ብዕሊ አድሃኖም፤ ከአራዳ እስከ አውስትራሊያ

    "ልቤን ተከትዬ ጥፋት ሠራሁ" የምትለዋ ብዕሊ አድሃኖም ግለ ታሪክ መነሻ ከአዲስ አበባ ዕምብርት አራዳ ነው። አውስትራሊያን ሁለተኛ አገሯ ለማድረግ የበቃችው በለጋ ዕድሜዋ ፈታኙን የስደት ሕይወትን በአገረ ሱዳን ተቋቁማ ነው።

  5. 41

    ስጦታው በፍቃዱ፤ ከቤተ እምነት እስከ ማረሚያ ቤት በጎ አድራጎት

    ደራሲ ስጦታው በፍቃዱ በአፍላ ዕድሜያቸው ወደ አውስትራሊያ የዘለቁት ነፃ የሃይማኖት ትምህርት ዕድል አግኝተው ነው። አዘላለቃቸው ግና ያለ ቪዛ ነበር።

  6. 40

    ስጦታው በፍቃዱ፤ ከማይጨው እስከ አውስትራሊያ

    "ከማይጨው እስከ ሲድኒ" ግለ ታሪክነቱ የደራሲ ስጦታው በፍቃዱ ቢሆንም፤ የተነሳሽነት ግፊትና ዕሳቤዎቹ የፈለቁት ግና ከአንድ የእምነት ተጋሪ ወዳጃቸውና ከሴት ልጃቸው ሊዲያ ነው።

  7. 39

    "የትም አገር ልኑር ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊነት ከደም የሚወጣ አይደለም" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" የማነ

    ድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ የማነ፤ የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ ከቀበሌ ተንስቶ የምሽት ክለብ መድረኮች ላይ አላከተመም። ከቶውንም በጦር ትምህርት ቤት ሁርሶ፣ በስደት ሞቃዲሾ፣ በዳግም ሠፈራ ኒውዝላንድና አውስትራሊያ የጥበብ ሙያው እስትንፋስ ሆኖ ዛሬም ድረስ አለ።

  8. 38

    "ፍቅር ፍርንባዬ ድረስ ነበር የያዘኝ፤ ማሰብና መናገር እስኪያቅተኝ ድረስ" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ"

    "የማትፈታህ ሚስት ሙዚቃ ነች" የሚለውና በቀዳሚ ክፍለ ግለ ሕይወት ትረካው ከውልደት እስከ ምሽት ክለብ ጅማሮው ያወጋው ድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ"፤ ትረካውን የምሽት ክለቡ ከቸረው የጥበብና የፍቅር ሕይወት እስከ ለጥቆ አገር ሲፈር እማኝ አስከ ሆነባትና ዝናን እስካተረፈባት የሶማሊያ ስደት አሻግሮ ያጋራል።

  9. 37

    ለድቁና ታስቦ ለሙዚቃ መድረክ የበቃው ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ"

    ድምፃዊ ኤልያስ የማነብርሃን ዳምጤ በቅፅል መጠሪያ ስሙ "ኪዊ" ተብሎ ይጠራል። ኒውዚላንድ በአንድ ወቅት ጥላ ከለላው ነበረችና የአገረ ኒውዚላንድ መለያ ቅፅል ስምን ይጋራል። ኤልያስ ለመድረክ የበቃው ድምፁን በሙሉቀን መለሰ ዘፈኖች አሟሽቶ፤ በጥላሁን ገሠሠ ቅላፄ ቃኝቶ ነው።

  10. 36

    "ከሕክምና ወደ ምክር ቤት አባልነት ለመሸጋገር አስቤያለሁ" ሰላም ፈለቀ ተገኝ

    ሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ቀደም ባለው የግለ - ሕይወት ትረካዋ እንደምን ከዕድገት ቀዬዋ በቅሎ ቤት ተነስታ ከወላጆቿና ታናሽ ወንድሟ ጋር ለስደት እንደተዳረገችና ወደ አውስትራሊያ ከእነ ቤተሰቧ እንደዘለቀች አውግታለች። ቀጣይ ትረካዋ የአውስትራሊያ ምክር ቤት አባል የመሆን ትልሟ ዙሪያ ነው።

  11. 35

    የእኔ ታሪክ፤ "አገርን ለመለወጥ፤ እኛ መለወጥ አለብን" - ሰላም ፈለቀ

    ሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ውልደቷ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ዕድገቷ በቅሎ ቤት ነው። ትውልድ አገሯን ኢትዮጵያን ለቅቃ ለስደት ሕይወት የበቃችው 10 የልደት ሻማዎችን እንኳ 'እፍ' ብላ ሳታጠፋ ነው።

  12. 34

    ሰናይትና ኤልቪስ

    ኤልቪስ ፕሪስሊ በትወናው ማለፊያ ተዋናይ፤ በዘፈኖቹ "King of Rock and Roll" ተብሎ ተሞካሽቷል። የጥበብ ሥራዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት ሆነውታል። ለሙዚቃ አፍቃሪዎቹም ዋጋ የማይተመንባቸው የውብ ጊዜያት ውድ ትዝታዎች ሆነው አሉ። የጥበብ ባልደረቦቹም "Elvis" በሚል መጠሪያ የሙዚቃ ሥራዎቹንንና ግለ ሕይወቱን ነቅሰው በፊልም ሞገስ አላብሰውታል። ተዋናይት ሰናይት መብራህቱም በትወናው ዓለም የኤልቪስን ዘመን ከኤልቪስ ጋር በአጃቢ ድምፃዊነት የታሪክ ታዳሚ አድርጋናለች።

  13. 33

    ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ

    ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ከውልደት ቀዬዋ ተንስታ፣ የካርቱም የስደት ሕይወቷን አጣቅሳ፣ የአውስትራሊያ የሠፈራና ምዕራባዊ የሥነ ጥበብ ሕይወት ጅማሮዋን አውግታለች። በቀጣይነትም እንደ ፅጌረዳ አበባ ውበትና እሾህን በተላበሰው የጥበብ ሕይወት ጉዞዋ ውስጥ የተፈተነችባቸውን ተግዳሮቶችና በሐሴት የተመላችባቸውን ስኬቶች ታነሳለች።

  14. 32

    ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከአገር ቤት እስከ አውስትራሊያ

    ሰናይት መብራህቱ፤ የሥነ ጥበብ ሕይወት ሕልሟ ከአገር ቤት ውዝዋዜና እንጉርጉሮ እስከ ኤልቪስ ፕሪስሊ የፊልም ትወና የዘለቀ ነው። ከውልደት እስከ ስደት ያለ የሕይወት ጉዞዋን አሰናስላ ታወጋለች።

  15. 31

    የኔ ታሪክ፤ ጋዜጠኛ ማርታ ፀጋው - ከኮልፌ ወደ አውስትራሊያ

    ጋዜጠኛ ማርታ ፀጋው ምንዳ - ትውልድና ዕድገቷ ኮልፌ - አዲስ አበባ ነው።በጢያራ የአፍሪካን አየር ሰንጥቃ ከአገረ ኢትዮጵያ ወደ አውስትራሊያ ከዘለቀች ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ አስቆጥራለች።

  16. 30

    የኔ ታሪክ፤ከያዮ እስከ አውስትራሊያ - ዶ/ር ሸሪፍ ሰዒድ

    ዶ/ር ሸሪፍ ሰዒድ፤ የአውስትራሊያን ምድር ረግጠው፤ ዓለም አቀፍ ደረጃን ከጠበቀ ዩኒቨርሲቲዋ የPhD ካባ ከመደረባቸው ዓመታት ርቆ መነሻቸው የቀድሞዋ ኢሉባቦር የአሁኗ ኢሉ አባቦር ናት። ዕትብታቸው የተቀበረው ያዮ ቀዬ ውስጥ ነው።

  17. 29

    የኔ ታሪክ፤ "ባልሰልጠነ ዘመን የሰለጠነ ሃሳብ ሰጥተውን ያለፉ አባቶቻችን ዕዳ አለብን" ሰብለወርቅ ታደሰ

    የዛሬ “የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ” እንግዳችን ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ናቸው። የግለ-ታሪክ ትረካቸው መነሻ የትውልድ ሠፈራቸው የሆነችው ቤልኤይር ናት። የኢትዮጵያ መዲና ከሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ነው የምትገኘው።

  18. 28

    አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሰው አገርም ብንሆን ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን እንመኝ።” - አሰፋ በቀለ - የእኔ ታሪክ፤ “ሰው አገርም ብንሆን ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን እንመኝ።” - አሰፋ በቀለ

    አቶ አሰፋ በቀለ ቤተሰባቸውን ጨምሮ ነዋሪነታቸው በሲድኒ - አውስትራሊያ ነው። አጭር ግለ-ታሪካቸውን ከትውልድ ቀዬአቸው ድሬ-ወሊሶ ጋር አጣቅሰው፤ የአገረ ግሪክ ቆይታና የአውስትራሊያ ሠፈራቸውን አያይዘው ያወጋሉ። - አቶ አሰፋ በቀለ ቤተሰባቸውን ጨምሮ ነዋሪነታቸው በሲድኒ - አውስትራሊያ ነው። አጭር ግለ-ታሪካቸውን ከትውልድ ቀዬአቸው ድሬ-ወሊሶ ጋር አጣቅሰው፤ የአገረ ግሪክ ቆይታና የአውስትራሊያ ሠፈራቸውን አያይዘው ያወጋሉ።

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።

HOSTED BY

SBS

Produced by SBS Audio

Frequently Asked Questions

How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ currently has 18 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ about?

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች...

How often does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ release new episodes?

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ has 18 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ?

You can listen to የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ?

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ is created and hosted by SBS.
URL copied to clipboard!