ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle

PODCAST · news

ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle

አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።

  1. 50
  2. 49
  3. 48

    ናይጄሪያ ወደቦቿ ከብሪታንያ ብዙ ያተርፋሉ ስትል አቅዳለች

    ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ናይጄሪያ፦ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት የብሪታንያ ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ የተገነባው የአገሪቱ ዋነኛ የንግድ ማሳለጪያ አፓፓን ጨምሮ የቲንካን ደሴት ወደቦችን ለማሻሻልም ከፍተኛ ተስፋ ሰንቃለች ። ሙሉ ዘገባውን በድምጽ እና በጽሑፍ ከገናኛው ማግኘት ይቻላል።

  4. 47

    በአፍሪቃ የኑክሌር ተቋምን ለመገንባት ሩጫ

    የግል የኒኩሌር ተቋም፦ ደቡብ አፍሪቃ የራሷ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አላት፣ ግብፅ በግንባታ ላይ ነች፣ ኬንያ፣ ጋና እና አንዳንድ ሌሎች አገራት እናም ቢኖረን ሲሉ ያልማሉ ። ስኬቱ ለየቅል ቢሆንም፤ የሕዝቡ ስጋት ግን ተመሳሳይ ነው ። ሙሉ ዘገባውን በድምጽ እና በጽሑፍ ከገናኛው ማግኘት ይቻላል።

  5. 46
  6. 45

    የአፍሪቃ የነዳጅ ምርት ቢጨመር የዓለም የነዳጅ ገበያን ያረጋጋ ይሆን? የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪቃ

    ናይጀሪያዊው ተንታኝ አዮዴሌ ኦኒ ከአፍሪቃ ነዳጅ ዘይት አምራቾች ናይጀሪያ ብዙ ነዳጅ ዘይት የማምረት አቅም እንዳላት ገልጸዋል። ይሁንና በርሳቸው አስተያየት በአሠራር ችግርና በነዳጅ ክምችት ማነስ ምክንያት ለአሁኑ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ቀውስ ግን መድረስ አትችልም

  7. 44

    ትኩረት በአፍሪቃ፣ የባሕረ ሰላጤዉ ጦርነት መዘዝ በሶማሊላንድ፣ ደቡብ አፍሪቃ-ወርሮበላን ለመምታት ጦር ሠራዊት

    ታዛቢዎች እንደሚገምቱት የእስራኤል ጦር ገና ካሁኑ ሶማሊላንድ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጦር ሠፈር ዉስጥ ሳይሰፍር አልቀረም።ጦሩ ሶማሊላንድ የሰፈረዉ የሁቲ አማፂያንን ከቅርብ ርቀት ለማጥቃት ነዉ

  8. 43
  9. 42

    ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል?

    የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፍ ንግድን እያስተጓጎለ ነው። የንግድ መርከቦች ከሱዌዝ ቦይ ይልቅ አፍሪካ ወደሚገኘው ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ለመሄድ ይገደዳሉ። ይህም ወጪን ይጨምራል፤በነዳጅ እና በሌሎች ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ ያስከትላል። ጦርነቱ በውጭ አገር ተቀጥረው ለሚሠሩ አፍሪቃውያንም የኢኮኖሚ መዘዝ አለው።

  10. 41

    ትኩረት በአፍሪቃ፤ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን ስጋት ገባት?

    ከ400,000 በላይ ኬንያውያን እንደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር ባሉ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ይሰራሉ። ብዙዎቹ በቤት ውስጥ ሥራ፣ በግንባታ፣ በእንግዳ ተቀባይነት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ተቀጥረው ይሰራሉ።የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እነዚህን ኬንያውያን ስጋት ውስጥ ከቷል።

  11. 40
  12. 39
  13. 38
  14. 37

    ፕሬዝዳንት ኪር ደቡብ ሱዳንን ማረጋጋት ይችሉ ይሆን?

    የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሰሞኑን ባለስልጣኖቻቸውን ከስልጣን ማባረር ይዘዋል። ተንታኞች እንደሚሉት የሰሞኑ የፕሬዚዳንቱ እርምጃ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት የሚያባባስ ነው። በሙስና፣ በጎሰኝነት እና በብልሹ አስተዳደር የሚተቸው የሳልቫኪር መንግስት ምክትላቸውን ሪክ ማቻርን ካሰሯቸው ወዲህ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ተባብሷል።

  15. 36

    በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚና

    በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ ጎረቤት ቻድም እየተቃረበ ነው። ያለፈው ሳምንት መጨረሻ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በድንበር ላይ ከሚገኙት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ የRSF ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል። የቻድ መንግስትም ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዘግቷል።

  16. 35

    ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ከአሜሪካ ወደ ቻይና አዙራ ይኾን ?

    በሁለቱ የዓለማችን ልዕለ ኃያላን የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ መሃል የገባችው ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ወደ ምሥራቅ ታዞር ይኾን? የሚለው ጥያቄ አሁን የበርካቶችን ትኩረት የሳበ መስሏል። ላለፉት 20 ዓመታት ደቡብ አፍሪካ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚገርም ብልሃት ሚዛኑን ጠብቃ ማቆየቷ ነው የሚነገርላት።

  17. 34

    አሜሪካ እጇን ያስገባችበት የኮንጎ የሰላም ስምምነት ይጸና ይኾን?

    በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓመታት የዘለቀው ደም መፋሰስ እንዲቆም አዲስ የተስፋ ጭላንጭል አሳይቷል። ባለፈው ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው የተኩስ አቁም ስምምነት፤ «ለመጨረሻ ጊዜ የተገኘ የሰላም ዕድል ይሆን?» የሚለው ጥያቄ የአለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ትኩረት ስቧል።

  18. 33
  19. 32

    የሱዳን ጦርነት ከኤል ፋሸር እስከ በኒ ሻንጉል፤ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤና የአሕጉሪቱ ሠላም

    የብሪታንያዉ ዜና አገ,ልግሎት ሮይተርስ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ተዋጊዎች የሚሰለጥኑበት ጦር ሠፈር ኢትዮጵያ ዉስጥ መግንባቱን ከዘገበ ወዲሕ ጉዳዩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ።

  20. 31

    ሩስያና አሜሪካ፥ አፍሪቃን ለመቆጣጠር ሩጫ

    ሩሲያ ቀድማ እግሯን ባደላደለችባቸው የሣኅል አገራት ጎዳና ላይ ዩናይትድ ስቴትስም መገስገስ ትሻለች ። ከማሊ፣ ከኒጀር እና ከቡርኪናፋሶ ላይ ያላትን አቀራረብም ከወታደራዊ ኹንታው ጋር ቢሆንም እንደገና እያስተካከለች ነው ።

  21. 30
  22. 29

    በአማጺው M23 ስር ያለችው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎዋ ከተማ ጎማ ከአንድ ዓመት በኋላ

    ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ጎማ ለጦርነት ክፍት የሆነች ከተማ አይደለችም። የጸጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል። ገበያዎች እንደገና ተከፍተዋል፣ትምህርት ቤቶችም ተከፍተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሁኔታው ​​አሁንም አስቸጋሪ ነው። ከተማዋ አሁንም በአማፂያን ቁጥጥር ስር ነች። ከሁሉም በላይ፣ ስነልቦናዊ መዘዞች በስፋት አሉ። ጭንቀት የብዙዎች የዕለት ተዕለት እውነታ ነው።

  23. 28

    የሱዳን ስደተኞች ብርቱ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል፦ ተመድ

    በርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ባፋጣኝ ካልቀረበ ክምችቱ የፊታችን መጋቢት ወር ማገባደጃ ላይ ሊሟጠጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል የተመድ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ፎልከር ቱይርክ ሱዳን ውስጥ ከ50 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አወያይተዋል ።

  24. 27

    የዩጋንዳ ምርጫ ወዴት?

    ከ40 ዓመታት በላይ ሐገሪቱን ያስተዳደሩት የ81 አመቱ የኡጋንዳ ፕረዚደንት ዩዌሪ ሙሰቨኒ ሐሙስ ዕለት በተካሄደም ምርጫ ማሸነፋቸውን የሐገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረጓል። ዩጋንዳ ውስጥ ሐሙስ በተከናወነው አገር አቀፍ ምርጫ ከ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ሰባት እጩዎች ተፎካክረው ነበር ።

  25. 26

    የጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ትኩረት በአፍሪካ

    ቻይና ለአፍሪካ ሐገራት ያለፖሊሲ ጫናና በቀላል የቢሮክራሲ ውጣውረድ በገፍ የምታቀርበውን ብድር የሐገራቱን መጻኢ ዕድል በቻይና ስር እንዲወድቅ ያደርጋል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ተንታኞችም ይደመጣሉ።

  26. 25

    የእስራኤል የሶማሊያ ላንድ አገርነት እውቅና የፈጠረው ውዝግብ እና የጊኒ ምርጫ

    ባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው ውዝግብ ቀስቅሷል

  27. 24

    ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት

    በሱዳን የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በሳተላይት የሚከታተለው የየል ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ ጉዳዮች ጥናት ላቦራቶሪ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሚሊሻያዎች የፈጸሟቸውን የጅምላ ግድያዎች ማስረጃዎች እያወደሙና እየደበቁ መሆናቸውን የሚያስረዳ ማስጠንቀቂያ የካተተ ዘገባ አቅርቧል።ሂዩመን ራይትስ ዋች በሱዳን ጦር እስር ቤቶች ሰዎች እየሞቱ ነው የሚሉ ዘገባዎች ደርሰውታል።

  28. 23

    ትኩረት በአፍሪቃ 201225 ዓለም አቀፍ ትኩረት የተነፈገው የሱዳን ጦርነት ፤ በአፍሪቃ የተካሄዱት መፈንቅለ መንግሥታት

    ትኩረት በአፍሪቃ በሱዳኑ ውጊያ ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ ቢሆንም ለነዚህ በዓለማችን እጅግ አስከፊ ለሚባሉ የሰብዓዊነትና እና የመፈናቀል ቀውሶች የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ትኩረት አሁንም አነስተኛ ነው። በቅርብ ጊዜያት በሁለት የአፍሪቃ ሀገራት መፈንቅለ መንግሥታት ፣በአንድ ሌላ ሀገር ደግሞ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጓል። ተከታታዮቹ መፈንቅለ መንግስታትና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ምን ያመለክታሉ? የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ኂሩትመለሰ አጠናቅራዋለች።

  29. 22
  30. 21
  31. 20

    የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍ

    በጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።

  32. 19

    ትኩረት በአፍሪካ፦ የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤልፋሺር ይፈጽማል የሚባለው ግፍ፤ በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ

    በጀርመኑ ዓለም አቀፋዊና እና አካባቢያዊ ጥናቶች ተቋም የሱዳን ጉዳዮች አዋቂ ሀገር አሊ እንደተናገሩት አሁን በአልፋሺር በሚካሄደው ጭፍጨፋ የጭካኔው መጠን በጣም አስደንጋጭ ወደሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በበቂ ሁኔታ በጋለ ስሜት የማይደግፋቸው፣ ከእነሱ ጋር መቀላቀል የማይፈልግ ወይም ማንኛውንም ተዋጊ የሚያደናቅፍ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል።

  33. 18

    በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ

    «ይህ የኦጎኒ ዘይት በእጁ ብዙ ደም አለው። እርስዎ እኔን ተረድተውኝ ከሆነ አላውቅም ። ይህ የኦጎኒ ዘይት ብዙ ደም አለው። ሕዝባችን ሞቷል፣ ብዙ ሰዎች፣ የኦጎኒዎች ሕይወት ብቻ አይደለም የጠፋው። በተቃውሞው ወቅት ከ4,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ታውቃላችሁ፣ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የፌዴራል መንግሥት በመጀመሪያ የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት። »

  34. 17

    በሱዳን፡ ጦርነቱን ያቀጣጠሉት የውጭ ኃይሎች ጦርነቱን ማስቆም ይችሉ ይሆን?

    የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ድጋፍ በውጭ ሀገራት ላይ የተመሰረተ ነው።በጄኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ሀይል የሚደግፈው በግብፅ፣ ቱርክ፣ ሩሲያ እና ኢራን መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ደግሞ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ይደገፋል። ለመሆኑ ሀገራቱ ከሱዳን ምን ይፈልጋሉ? ጦርነቱን ማስቆም ይችሉ ይሆን?

  35. 16
  36. 15
  37. 14

    ናይጄሪያ፤ “የክርስቲያን ዘር ማጥፋት” ወይስ የትርርክት ቀውስ?

    በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ላይ «የዘር ማጥፋት» ዘመቻ እየተካሄደ ነው መባሉ ሞቅ ያለ ክርክር አስነስቷል፣ ተንታኞች እንዲህ ያሉት ትርክቶች የሀገሪቱን የሰላም ግንባታ ጥረቶችን ሊያዳክሙ እና መለያየትንና አለመተማመንን ሊያባብስ ይችላሉ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ትራምፕ ግን አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ትወስዳለች ብለው እያስፈራሩ ነው።

  38. 13

    የኮትዲቫር ምርጫ እና የዴሞክራሲ ጥያቄ

    30 ሚሊዮን ነዋሪ ያላት ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ኮትዲቫር ቅዳሜ፤ ጥቅምት 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አካሂዳለች ። ለአራተኛ ጊዜ የተወዳደሩት ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራ ያሸንፋሉ የሚል ቅድመ ግምት ተሰጥቷል ። የ83 ዓመቱ አዛውንት የአገሪቱ ፕሬዚደንት አላሳን ዋታራን ጨምሮ አምስት ተፎካካሪዎች ለፕሬዚደንትነት ተፎካክረዋል

  39. 12

    ከ18 ዓመት በታች ስደተኞች የሊቢያና የባሕር ላይ መከራ

    ስደተኞችን ከመስጠም አደጋ የሚታደጉ የባሕር ላይ ነፍስ አድን ድርጅቶች የማንቂያ ደውሉን እያሰሙ ነው ። በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች በዓለም ላይ ካሉ አደገኛ የስደት መስመሮች አንዱ የሆነውን የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጠው እየፈለሱ ነው ። በባሕር ከመስጠም ከተረፉት መካከል አንድ አምስተኛው የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ።

  40. 11

    ትኩረት በአፍሪካ የጥቅምት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    አምስት ጊዜ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረው ባይሳካላቸውም ራይላ ኦዲንጋ የኬንያን ዴሞክራሲ እና ምርጫ የይስሙላ እንዳሆን ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል። በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦዲንጋ በተቃዋሚነታቸው ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ ተሰደዋል። ግን እስከ መጨረሻው አላፈገፈጉም። በማዳጋስካር ጦር ሠራዊት ውስጥ ካፕሳት ተብሎ የሚጠራው ልዩ ኃይል አዛዥ ኮሎኔል ሚካኤል ራንጄሬሪና ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። የ51 ዓመቱ የጦር መኮንን ሥልጣን የጨበጡት ለሦስት ሣምንታት ከተካሔደ የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጄሊና ከሥልጣን ተባረው ነው።

  41. 10

    የካሜሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ43 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩትን የፓል ቢያን ሥልጣን ያራዝም ይሆን ?

    ፎኩም «በምርጫው ቀን ለመምረጥ መውጣት መቻላችንን መጠየቅ ጀምሬያለሁ፣ሁሉ ነገር ከተዘጋጋ ድምጽ ለመስጠት ወደምርጫ ጣቢያ እንዴት እንሄዳለን» ይላሉ።«የመራጮች ቁጥር በፀጥታ እጦት ካነሰ ምርጫው የተሀድሶ መንገድ ሳይሆን “የይስሙላ” ነው የሚለውን ግንዛቤ ያጠናክራል ፤መራጮች እንቅፋቶችን ከተቃወሙ ግን ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።»

  42. 9
  43. 8

    ትኩረት በአፍሪካ፤ የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ፤ ኡጋንዳ 40 ዓመታት በዩዌሪ ሙሰቬኒ ሥር

    የማቻር ፍርድ ቤት መቅረብ ተጨምሮበት ደቡብ ሱዳንን እንደገና ወደ ግጭት ሊመልሳት ይችላል እየተባለ ነው። ለዛም ነው የሪክ ማቻር የፍርድ ሂደት የእሳቸውና እና የተባባሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የደቡብ ሱዳን የወደፊት እጣ ፈንታን የሚወስን ነው የሚባለው።

  44. 7
  45. 6

    የሳህል ግዛቶች ህብረት፤ አንድነት ወይስ እኩል ያልሆነ አጋርነት?

    የማሊ፣ ኒጀር እና የቡርኪናፋሶ መንግሥታ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተገረሱ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተመሰረተዉ የሳህል ግዛቶች ህብረት (AES) በያዘዉ ያልተሟሉ ግቦች እና የኢኮኖሚ ተስፋዎች ብሎም ሚዛናዊ ያልሆኑ ጥቅሞች በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ትችቶች ገጥሞታል። ህብረቱ ዛሬ እስከ ምን ድርሶ ይሆን?

  46. 5

    ስለደካማዉ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ምን ያዉቃሉ?

    ደቡብ ሱዳን አዲስ የእርስ በርስ ግጭት አፋፍ ላይ ያለች ይመስላል። ከጎርጎረሳዉያኑ 2018 ጀምሮ በሃገሪቱ የነበረዉን ከፍተኛ የእርስ በእርስ ጦርነት ያስቆመዉ የሰላም ስምምነት በተለይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በአገር ክህደት እና በሌሎች ወንጀሎች ከተከሰሱ እና እስር ላይ ከዋሉ በኋላ የሰላም ስምምነቱ ዳመና ያጠላበት ይመስላል።

  47. 4
  48. 3

    የኬንያው መሪ በጅምላ የፓርላማ አባላትን በሙስና መውቀሳቸው እያወዛገበ ነው

    የኬንያ ፕሬዝዳንት የፓርላማ አባላቱን ጉቦ እየተቀበሉ ነው ብለው በጅምላ ከወቀሱ ወዲህ፤ የኬንያን ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ነው። በሀገሪቱ የተደረገ አዲስ ጥናት እንዳመለከተው ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቻ ጎቦ ለመስጠት ይገደዳሉ። በኬንያ በየዓመቱ ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከዝርፊያ እና ከህገወጥ የገንዘብ ፍሰት እንሚጠፋ ይገመታል።

  49. 2

    በደቡብ ሱዳን በበረታ ግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ

    የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል።

  50. 1

    በአፍሪካ ክትባቶች በብዛት ለማምረት የተወጠነው ዕቅድ ከምን ደረሰ?

    የኮቪድ-19 ዓለምን ካመሰ በኋላ የተሠሩ ክትባቶች በፍጥነት እና በፍትኃዊነት አለመዳረሳቸው የአፍሪካን ጥገኝነት አጋልጦታል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ አፍሪካ ክትባቶች እና መድሐኒቶች በማምረት ከጥገኝነት እንድትላቀቅ በርካታ ዕቅዶች አሉ። ዕቅዶቹ በረዥም ጊዜ ምን ያክል ዘላቂ ናቸው?

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።

HOSTED BY

DW

CATEGORIES

URL copied to clipboard!