PODCAST · news
ዜና መጽሔት
by DW
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
-
100
የሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
የዛሬው የዜና መ።ፅሄት፤ ለአማራ እና ለትግራይ ምኁራን የቀረቡ የትብብር ጥሪዎችና ያላስማሙ ተቃርኖዎች፣በምስራቅ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የደረሰው ጥቃት፣የደቡብ አፍሪቃዉ መጤ ጠል ጥቃትሃገሪቱን ከአፍሪቃ ማቃረኑ እንዲሁም የኢትዮጵያ የፊልም ፌስቲቫል በፓሪስ የተሰኙ ርዕሶችን ያስተነትናል።
-
99
የዕለተ ዐርብ ሐምሌ 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
የዓለም ዜናን የሚከተለዉ የዜና መጽሔት፤ -በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ነው ያለው የዘር ማጥፋት እና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆም፣ ሲል ጥሪ ያቀረበዉ የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ -በትግራይ ክልል እየተደረጉ ያሉ ሰሞነኛ ስብሰባዎችና የነዋሪዎች ኹኔታ - በቀይ ባሕር በሁቲ ታጣቂዎች የተፈፀ የመርከቦች ጥቃትን የአፍሪካ ኅብረት ማዉገዙ -የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎትን ለማስተሳሰር ያለመ አዲስ ፍኖተ-ካርታ ይፋ መሆኑ - እንዲሁም ተግባራዊ የሆነው ተንቀሳቃሽ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና ፕሮግራም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሰኙ ርዕሶችን ይዟል።
-
98
የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፦ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በሚያቀርቡት ሐሳብ እንዳይጠየቁ ኃላፊነት እወስዳለሁ ማለቱ፤ የድሮን ጥቃት በአባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ስለመተባበር ምን አለ? ደቡብ አፍሪቃ፡ ኢትዮጵያውያን በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው የተመለሱ ነዉ፤ እንዲሁም የአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት፤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
-
97
የሐምሌ 15 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
ዜና መፅሔቱ፣ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሲቪል ማሕበራት ተሳትፎ እና የታዛቢነት ሚና፣ ደብረብርሀን መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮ ፣ የግብፅ የህዳሴ ግድብ ውንጀላና የኢትዮጵያዊው ተደራዳሪ ምላሽ፣ እንዲሁም በትግራይ የሰላሙ ተስፋ ምን ይመስላል? በተሰኙ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርቡበታል
-
96
-
95
የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፣ የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ጨፌ ስለክልሉ የፀጥታው ሁኔታ መምከሩን፣ -በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በአዲስ ጉባኤዉን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ መባሉን፣ -በደቡብና ሰሜን ወሎ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸም ዝርፍያ መባባሱ፣ -የአፍሪቃ ቀንድን የበለጠ ስጋት ዉስጥ የጣለዉ የአሜሪካ እና የኢራን ዳግም ግጭት የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ይዳስሳል
-
94
የሐምሌ 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
የዓለም ዜናን የሚከተለዉ የምሽቱ የዜና መጽሔት፤ በአማራ ክልል በሴቶች ላይየሚደርሰው ወሲባዊ አካላዊና ጥቃት ተባብሷል መባሉ፤ በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታ፣በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሰሜን ኢትዮጵያ ጉብኝቶች፣በትግራይ የሰላምና ለውጥ ም/ቤት በአዲስ አበባ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲሁም በአሜሪካ ምርጫ ቻይና ጣልቃ ገብታለች ሲሉ ቻይናን የከሰሱት ዶናልድ ትራምፕ የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ይዳስሳል።
-
93
የሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፦ ትናንት ስለተጀመረው የኢትዮጲያ ብሔራዊ የምክክር ጉባኤ የተሳታፊዎች አስተያየት ፣ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው መጀመር፣ አካሄድ እና ውጤቱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የላኩት ተፈናቃዮች ከጉባኤው የሚጠብቁት፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ የወደብና የቀይ ባህር ወሰን ጥያቄ ፣ አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በተመለከተ የወሰደችው የፖሊሲ ለውጥ የዓለም እግር ኳስ የግማሽ ፍጻሜና የፍጻሜ ጨዋታዎች የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።
-
92
የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ቀዳሚው ዘገባ ዛሬ በይፋ የተጀመረውን ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ ይመለከታል፤ የአየር ንብረት መዛባት በክረምቱ ግብርና ላይ የደቀነው ስጋት፤ የአሜሪካው አምባሳደር የመቀለ ጉብኝት፤ አሜሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በተመለከተ የወሰደችው የፖሊሲ ለውጥ እንዲሁም የትናንቱን የፈረንሳይ ስፔን ጨዋታ እና የዛሬውን የዓለም ዋንጫ ተጋጣሚዎች የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል
-
91
የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 7 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ
በዜና መጽኄት ስድስት ዘገባዎችን ይዟል- የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜን በተለመለከተ ቃለ መጠይቅ ነው ። ነገ ስለሚጀመረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሰዎች ምን ይላሉ?፣ ነገ ስለ ሚጀረው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ምን ተባለ?፣ በአማራ ክልል የተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አገራዊ ውይይት በጅግጅጋ እንዲሁም የጊምቢ- ኖሌካባ እና ሜቱ መንገድ ግንባታ መጓተት የሚሉ ዘገባዎችን ያስተነትናል።
-
90
-
89
የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዓለም ዜናን በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሄት ፣ በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭ፤ በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄ፤ የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን?፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽ፣ በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው መገለጹ እንዲሁም አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። የወጣቶች ዓለም መሰናዶ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፦ የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎች የንባብ ባህልን እያዳከሙ ይሆን? በሚል ርእስ ተቀናብሯል ።
-
88
-
87
-
86
የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነዉ ሲሉ፣ -የዚያዉ ከትግራይ ክልል ወጣቶች ደግሞ አፈሳና የጦርነት ዝግጅት እንዳሳሰባቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የዳግም ጦርነት ዝግጅት፣ ወቀሳና ሥጋቱን ዜና መጽሔቱ በሁለት ዘገቦች ያስተነትናል።የኢትዮጵያ ምርጫ የጥቃት ኢላማ እንደነበር፣ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ግን ዘንድሮም በ10.2 በመቶ አድጓል መባሉ ከወደ አዲስ አበባ ተሰምቷል።ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕስችን በሱዳንዋ ሥልታዊ ከተማ አል-ዑቤይድ የተፈፀመዉ የመብት ጥሰትና ይደርሳል የተባለዉ ተጨማሪ ጥፋት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ኮሚሽንን እያባተለ መሆኑን ይቃኛል።
-
85
DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋት፣ የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢ፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታ
-
84
የሰኔ 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢ ፣ በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ፣በድሬደዋ የተማሪ ህፃናት ምገባን በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ እንዲሁም የቀድሞ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
-
83
የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች 13 ሰዎች መግደላቸዉን የሚቃኝ ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን አስተማሪዎች ተማሪዎችን ላለመፈተን ማደማቸዉን ከዞኑ አስተዳደር መልስ ጋር ያሰባጠረ ዘገባም አለዉ።የአዉሮጳ የሙቀት መጠን ማየልና የፖለቲካዊ መርሕ ለዉጥ ጥያቄ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ 105ኛ ዓመት በአል፣ የዓለም የእግር ኳስ ግጥሚያ የአፍሪቃ ቡድናት ሽንፈት ያልናቸዉንም ርዕሶች ያስተነትናል።
-
82
የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት፤ አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናት፤ በጋምቤላ ክልል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስለሚኖራቸው ሚና፤ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጀመሩ እንዲሁም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እዚያ ስለሚወለዱ ልጆች ዜግነት ያሳለፈው ውሳኔን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
-
81
የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።
-
80
DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ
-
79
የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።
-
78
የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?
-
77
የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
በዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤ የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁን ከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።
-
76
የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
-
75
የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት
መጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።
-
74
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገ
ምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።
-
73
DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
በሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።
-
72
የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤ መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
-
71
የሰኔ 10 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
አሳሳቢው የጦርነት ስጋት በሰሜን ኢትዮጵያ ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ «የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ»ን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ፣ ዩናይትድ ስቴትሰና ኢራን ደረሱበት የተባለው ስምምነት አፍሪካን እንዳያዘናጋ ተንታኛች ማሳሰባቸው እንዲሁም ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች ዩክሬንን ለመደገፍ መስማማታቸው የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው
-
70
የጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ እስር
ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ከሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን ቤተሰቦቿ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።የጋዜጠኛዋ ታናሽ እህት ለዶይቸ ቬለ እንደገለፀችው፤ እህቷ ያለፈው ሰኞ ሰኔ አንድ ቀን፣ 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ ተብላ ነው የተያዘችው። ያም ሆኖ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበችም።
-
69
የሰኔ 9ቀን 2018 የዜና መፅሔት
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ዉድነት በደሞዝተኞች ላይ ያሳረፈዉን ጫና ችግር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በትግራይ ክልል አዲስ የወጣዉ የወታደራዊ አገልግሎት ሕግ ያስከተለዉ ተቃዉሞና ሥጋት፣ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ መታሰሯና የአፍሪቃ ሕብረት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ በተቀጣጠለዉ የዉጪ ጠል ጥቃትና ዛቻ ላይ ሊነጋገር ማቀዱን ዜና መፅሔቱ በየተራ ይተነትናል።
-
68
DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
በሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተና፣ የኢራን አሜሪካ ስምምነት እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ተካተዋል።
-
67
የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጥሪ ነዋሪዎች ከአሸናፊው ፓርቲ ምን ይጠብቃሉ ? ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች፤ 1655 ዜጎች ደግሞ በምህረት እንዲለቀቁ ተደረገ ለአሜሪካዉያን የኤቦላ ማገገምያ ማዕከል ኬንያ ዉስጥ መገንባቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረትና ደቡብ ኮሪያ፤ የሰሜን ኮሪይና ቻይና ጉባኤዎች
-
66
የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
በዜና መፅሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ መሆኑን መናገሩ፣ ሰቆጣ የተጠለሉ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ መጋለጣቸውን መግለፃቸው ፣ -ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ መቀጠሉ ፣ የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ መጠየቁ ፣ ዛሬ በሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው ። በባህል መድረክ ለህክምና ወደ በጀርመን በመጣበት አጋጣሚ እና የስዕል እግዚቢሽን ያቀረበውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላን እንግዳዉ አድርጓል።
-
65
የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዜና መፅሔት
ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት፣ ጋምቤላ ክልል ዳግም ያገረሸው የፀጥታ ስጋት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ24 የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ይፋ ማድረግ መጀመሩ፤ ለመጪው ዓመት ከ2,3 ትሪሊየን በላይ ብር የመንግሥት በጀት መታቀዱ እንዲሁም የዲጂታል ገቢ እና አዲሱ ፈተና የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
-
64
የዜና መጽሔት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
የዜና መፅሔት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ፈደ,ራዊ መንግሥትና በህወሓት መካከል የናረዉን ዉጥረት ለማርገብ የአፍሪቃ ሕብረትን ሚና የሚቃኝ ቀለ ምልልስን ያስቀድማል።የትግራይ ወጣቶች በብዛት ከክክልሉ መዉጣታቸዉንና ምክንያቱን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።የትራፊክ አደጋ መደጋገምና መፍትሔዉ ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የኤርትራና የግብፅ ወዳጅነት ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም የሚኖረዉን በጎ መጥፎ ዉጤት በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።
-
63
የሰኞ ሰኔ አንድ ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ስጋት በትግራይ የየደረሰዉ የድሮን ጥቃት እና አካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ያልሰጡ በሰሜንና ደቡብ ወሎ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ነገ ሰኔ 2 ቀን የምርቻ ድምፅ ሊሰጡ መሆኑ ፤ እንዲሁም ኢሰመኮ - አርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ምዕመናን እና ቤተክርስትያን ላይ የተፈፀመ ጥቃትን በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለፁ በሚሉ ርዕሶች የተቀናበሩት በስፋት ይተነተናሉ።
-
62
-
61
የግንቦት 27 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት
በዜና መጽሔት በአርሲ ዞን የተገደሉ ወገኖችን በሚመለከት የመንግሥት እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ምላሽ፤በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሔራዊ አስተዳደር የጻግብጂ ወረዳ በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል መባሉ፤ግንቦት 24 ቀን ስለተካሄደው ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት፤ ድኅረ ምርጫ በደቡብ ሕዝቦች ክልል ፤ በሰባተኛው ምርጫ የተሳተፈው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ድሬደዋ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ችግር ደርሶብኛል ማለቱ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMF ለኢትዮጵያ 468 ሚሊየን ዶላር ለመልቀቅ መስማማቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።
-
60
የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
ከምርጫ ማግሥት ማን ምን አለ? የተሰጡ አስተያየቶች፤ በአርሲ የተፈጸመው ግድያ እና የቀረበው አቤቱታ፤ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የኢጋድና የኅብረት-ለምርጫ የመጀሪያ ጊዜ ዘገባ፣ የአማራ ክልል ወጣቶች ጥሪ ከምርጫው ማግስት በኋላ፤ ብርን ያዳከመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሰኞው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ድህረ ምርጫ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ቃለ መጠይቅ
-
59
ልዩ ዝግጅት፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ዛሬ በየአካባቢው የወጡ ጊዜያዊ ውጤቶችን እንዲሁም የምርጫውን ሂደት፣ የፀጥታ ችግሮችና እና ተያያዥ ክስተቶችን የሚቃኙ ዘገባዎችን ያካተተ ልዩ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትናንት የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችንም ማጽደቁን መነሻ ያደረገ ዘገባም አለን።
-
58
በምርጫ ከሚያሸንፈው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?
ትናንት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በመጭው አመስት አመታት የሚያስተዳድራቸውን ለመምረጥ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል። ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊው አካል በቀጣይ አምስት አመታት ሀገሪቱን የማስተዳደር ሀላፊነት ይጣልበታል።ለመሆኑ ከመጭው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?
-
57
የግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ዛሬ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ለሚወዳደሩ እጩዎች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በበሻሻ ከተማ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ታዬ ዐፅቀ ሥላሴ ደግሞ በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት ድምጽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በጸጥታ ምክንያት ወደ 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ” አለመከፈታቸውን ዛሬ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ ችግር መቋረጡን ተናግረዋል።
-
56
የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጎሀፅዮን አካባቢ፤ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የጓሚዙ 12 መንገደኞች መገደላቸውን መጭው ምርጫ ከተሳታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከታዛቢዎች እና ከመራጮች አንፃር በአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በክልሉ ባለው ግጭት ሳቢያ ግድያ እና ዝርፊያ እየደረሰብን ነው ማለታቸው በደቡብ አፍሪቃ የሚታየውን የመጤ ጠል ጥቃት የሚያስቃኙ አራት ዘገባዎችን አካቷል።
-
55
DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ማስጠንቀቂያና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምላሽ፣ የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ድባብ በአዲስ አበባ፣ ''ምርጫው፣ አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው።''የጋራ-መድረክ፣ ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣
-
54
የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱንን የኢድ አል አድሀን በዓል የተመለከቱ ዘገባዎች ያስቀድማል፤ የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ እና የፓርቲዎች አስተያየት፤ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል። በትግራይ ክልል “የወጣቶች የግዳጅ ምልመላ” እየተደረገ መሆኑ መገለጹ፤ በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ከህወሃት ቃል አቀባይ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል።
-
53
የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በአማራ 8፣ በትግራይ 38 ምርጫ ክልሎች ላይ ግንቦት 24 ምርጫ አይደረግም መባሉ፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በአማራ ክልል፤ የምርጫ ቅስቀሳቃ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫ ዘመቻ እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት ባልተጠናቀቁ የቤት ስራዎቹ ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለፀ በሚሉ ርዕሶች ስር ተጠናቅረዋል።
-
52
የግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
በፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ክፋይ ምርጫ ቦርድ "የዜጎችን መሠረታዊ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊነጥቅ አይገባም" ሲል ማሳሰቡን፤ የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ " ስልታዊ የሆኑ የምርጫ ሕግ ጥሰቶች ካልታረሙ ከምርጫው እራሱን ለማግለል እንደሚገደድ ማሳወቁን፤ በትግራይ ስላለው የጦርነት ድባብ የባለሙያ አስተያየት
-
51
የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የዜና መጽሔት-1-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅት- 2-ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉ የድሪዳዋ ከተማ እጩ ተወዳዳሪና ሐረሪ ክልል የሚንቀሳሱ ሌላ እጩ ተወዳዳሪ ስለ ምርጫው ሂደት የሰጡት አስተያየት 3 -የንግድ ሱቆቻቸው የፈረሱባቸው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ-4-ወደ ውጭ የሚላክ የኢትዮጵያ ቡና ላይ የተጋረጠው ፈተና - 5 ቻይና በዓለም ኃያላን ተፈላጊ የሆነችበት ምክንያት በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርቡበታል ሳምንታዊው ከወጣቶች ዓለም ከምርጫ 2018፤ ወጣቱ በርግጥ ምን ይፈልጋል?- በሚል ርዕስ ጋር ከተቀናበረ ዝግጅት ጋር ይጠብቀናል ።
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
HOSTED BY
DW
Loading similar podcasts...