PODCAST · news
የዓለም ዜና
by DW
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
-
100
DW Amharic የግንቦት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት የትብብር ሥምምነት ዛሬ ቅዳሜ በአስመራ ተፈራረሙ። ሥምምነቱ የተፈረመው የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተገኙበት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት በኢቦላ ወረርሽኝ ቢያንስ 80 ሰዎች ሞቱ። የቦኮ ሐራም አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከፈጸሙት ጥቃት በኋላ ቢያንስ 42 ልጆች ደብዛቸው መጥፋቱን የአካባቢው ተመራጭ ተናገሩ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ኢዚዲን አል-ሐዳድ ተገደሉ።
-
99
የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -በደቡብ አፍሪካ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ጋብ አያለ ቢመጣም «ሕገ ወጥ ግንባታ» በሚል ምክንያት ሱቆቻቸው እየፈረሱባቸው እንደሚገኙ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያዊያውያን ለዶቼቬለ ተናገሩ ። -በኮንጎዋ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር በተከሰተ አዲስ የኤቦላ ወረርሽኝ 65 ሰዎች መሞታቸውን መታወቁን የአፍሪቃ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል አስታወቀ። -የብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሁለት ቀናት ኒው ዴልሂ ህንድ ውስጥ ያካሄዱትን ጉባኤ የጋራ መግለጫ ሳያወጡ ዛሬ አበቁ።
-
98
የዓለም ዜና፤ ግንቦት 6 ቀን 2018 ሐሙስ
አርስተ ዜና -የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና በፕሬዚዳንት ዢ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸዉ። ትራምፕ አስደናቂ መሪ ሲሉ ዢ ጂንፒንግን አሞካሽተዋቸዋል። የሁለቱ ሀገራት "የተረጋጋ" ግንኙነት ለዓለም ፋይዳ እንደሚሆን የተናገሩት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸዉ፤ የታይዋን ጉዳይ በአግባቡ ካልተያዘ ግን ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።-ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ በዩናይትድ ስቴትስ ከ4 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ መነሳቱ ተገለፀ። ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችዉን ማእቀብ ለማንሳት እያሰበች እንደሆን ያስታወቀችዉ በዚሁ ሰሞን እንደሆን የሚታወስ ነዉ።
-
97
የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ትናንት ከአሶሳ ወደ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ይጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የበርካቶች ሕይወት አለፈ። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማኑዌል ማክሮ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፈረንሳዩ መሪ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል። ጋና ከደቡብ አፍሪቃ 300 ዜጎቿን ልታወጣ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከቀትር በኋላ ቻይና ገብተዋል። የትራምፕ ጉዞ በ9 ዓመት በአሜሪካ ፕሬዝደንት ወደ ቻይና የተደረገ የመጀመሪያ ጉብኝት ነው።
-
96
የግንቦት 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-አርዕስተ ዜና -በጅቡቲ ወይም በሶማሊያ በኩል የአደን ባሕረ-ሠላጤን አቋርጠዉ ወደ አረብ ሐገራት ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቢሞቱም፣ ሌሎች መሰደዳቸዉን አለማቆማቸዉን ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ድርጅት አስታወቀ።-የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶችን ለማስወገድ ኢትዮጵያ «ጠቃሚ» ያሉትን ሚና እየተወጣች ነዉ በማለት አደነቁ።--ፈረንሳይ ከአፍሪቃ ሐገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት በአ,ዲስ መልክ እንደምታጠናክር አስታወቀች።ፈረንሳይ ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶችዋ ከፈረንሳይኛ ተናጋሪ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ጋር ከተቃቃረች ወዲሕ ፊቷን ወደ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ አዙራለች
-
95
የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ፣የክስ ሂደታቸው "በኘላዝማ" እንዲታይ ተወስኖባቸው የነበሩ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር ያሉ የሽብር ተከሳሾች ጉዳያቸውን በአካል እንዲከታተሉ ዛሬ ብይን ሰጠ። ሱዳን ውስጥ በተፈጸሙ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮኖች) ጥቃቶች ከጥር እስከ ሚያዚያ ቢያንስ 880 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የተመድ አስታወቀ። በተመድ የአፍሪቃ ውክልና እንዲጨምር የተሀድሶ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ አሳሰቡ ።
-
94
የግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በሰሜናዊ ምስራቋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት ኢቱሪ 69 ሰዎች በሚሊሺያዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች እና የጸጥታ አካላት ተናገሩ። • በማዕከላዊ ማሊ በተመሳሳይ ጂሃዲስቶች አደረሱ በተባለ መጠነ, ሰፊ ጥቃት በ,ርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የጸጥታ ምንጮች ትናንት ቅዳሜ አስታወቁ። • ኢራን አሜሪካ ላቀረበችላት የሰላም ስምምነት መልስ መስጠቷን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ ። • ሩስያ በዩክሬን የምታደርገው ጦርነት በፍጥነት እንዲያበቃ ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች። • በሃንታ ቫይረስ በተመታች የመዝናኛ መርከብ ላይ ያሉ ተጓዦችን የማስወጣት ስራ በይፋ ተጀመረ።
-
93
የቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አከባቢ ባለፈው ሓሙስ «በአንድ የፖሊስ አባል የተገደለ» ወጣት ትናንት ዓርብ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን ፤የናይጄሪያ ጦር በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል 50 ፅንፈኛ ያላቸውን ታጣቂዎች መግደሉን ማስታወቁን፤የዓለም ጤና ድርጅት ሀላፊ የሃንታ ቫይረስ የተከሰተበት መርከብ ከመድረሱ በፊት ስፔን መግባታቸው መገለፁን፤ ሂዝቦላህ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት ማድረጉን መግለፁ፣ሞስኮ በጠንካራ ጥበቃ ስር ዛሬ የድል ቀን በዓልን ማክበሯን፣ኢራን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ማስታወቋን አካቷል።
-
92
የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መቐለ፥ሕወሓት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ዛሬበይፋ ሥራ መጀመሩን ዐሳወቀ፤ ናይሮቢ፥ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ሦስት የአፍሪቃ አገራትን ሊጎበኙ ነው፤ ሞቃዲሾ፥ ሶማሊያ ውስጥ ብርቱ የረሐብ አደጋ እልቂት እንዳይፈጥር አስግቷል፤ ሪያድ፥ በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ ዘመቻዋ ዩናይትድ ስቴትስ የዓየር ክልሏን እንዳትጠቀም ሣዑዲ ዓረቢያ አገደች፤ ቴህራን፥ ኢራን መርከቦቼ ላይ ጥቃት አደረሰችብን ያለቻት ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቀች፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራን መርከቦች ላይ ተኩስ ከፈተች
-
91
የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የሐሙስ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና -ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ይበልጥ እንዳሰጋቸው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናገሩ። -የናፍጣ እጥረት ባናረው የጭነት መጓጋዣ ዋጋ ምክንያት፣ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውንና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑንም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶ አደሮች ዐሳወቁ። -ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ የኢራኑን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም እቅድ እየገመገመች መሆኑን ኢራን አሳወቀች።
-
90
ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን ጥቃት) እጄ የለበትም ስትል አስተባበለች ። • የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በቻድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 23 ወታደሮች ተገደሉ ፤ ሌሎች 26 ቆሰሉ ። • አሜሪካ እና ኢራን የባሕረ ሰላጤውን ጦርነት ለማቆም ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ። • በገዳዩ የሀንታ ተሐዋሲ የተጠረጠሩ ሦስት ተጓዦች ከመንገደኞች መርከብ ተለይተው ወደ ኔዘርላንድስ መወሰዳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
-
89
የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መቀለ፥ ሕወሓት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን የትግራይ ክልል ፕረዚደንት አድርጎ መረጠ፤ ናይሮቢ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን አንዱ ሌላኛውን በማጥቃት እየተካሰሱ ነው፤ አስመራ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ልታነሳ ነው መባሉ፤ ዋሽንግተን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ ሠርጥ መርከቦችን ብታስተናብርም የተኩስ አቁሙ ግን እንደተጠበቀ ነው አለች፤ ዬርቬና፥ የአውሮጳ ኅብረት የትራምፕ የቀረጥ ዛቻ ለሚያስከትለው ማንኛውም ነገር ዝግጁ መሆኑን ዐሳወቀ፤ ለንደን፥ ዩክሬንን ለማጥቃት ለሩስያ ተዋጊዎችን የሚመለምሉ ላይ ብሪታንያ ማእቀብ ጣለች፤ ላይፕትሲሽ፥ በተሽከርካሪ ግድያ የፈጸመው ግለሰብ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው
-
88
የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና--የጀርመን መራሄ መንግሥት ፍሬድሪክ መርስ ፤ ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 5,000 የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን ጦር ሰፈር ለማዉጣት ማቀዳቸዉ የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ተናገሩ። ኔቶ በበኩሉ አውሮጳውያን፤ የአሜሪካኑን ፕሬዝዳንት የብስጭት መልእክትን «ሰምተው» ቁርጠኝነታቸዉን እያጠናከሩ ነዉ ሲል መልስ ሰጥቷል።-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ኢሶዴፓ) ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያቀረባቸውን 309 ዕጩዎች ከውድድሩ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ። -በእስር ላይ የሚገኙ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርበት ያላቸው ሰባት ሰዎች መካከል እስካሁን ፍርድ ቤት በቀረቡት ሁለቱ ላይ ፖሊስ የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቋል።
-
87
የሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በመዲናዪቱ ካርቱም (RSF) ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት አምስት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች አስታወቁ። • በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ሌላ የነዳጅ መርከብ በባሕር ላይ ወንበዴዎች ተጠለፈች • ኢራን በ30 ቀናት ውስጥ ግጭቱ እንዲቆምና የአሜሪካ ማዕቀቦች እንዲነሱ የሚጠይቅ የ14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ አቀረበች። • ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ወንድሙ ዛሬ የተካሄደውን 31ኛው የፕራግ ዓለም አቀፍ ማራቶን አሸነፈ።
-
86
የሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በኬንያ ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፋና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 10 ሰዎች ሞቱ። ታይዋን ፕሬዝዳንት ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ዲፕሎማሲያዊ አጋር ሀገር ኤስዋቲኒ ገቡ።3,000 የሚጠጉ የየመን ስደተኞች ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳይባረሩ አንድ የፌዴራል ዳኛ ከለከሉ። የነዳጅ ዘይት የጫነ አንድ መርከብ ከየመን የባህር ዳርቻ ተጠለፈ። ዩናይትድ ስቴትስ 5000 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ ነው። የአውሮፓ ህብረት እና የጀርመን ኢንዱስትሪዎች የትራምፕን አዲስ የታሪፍ ዕቅዶች ተቹ።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ክልሉ ሙሉ በሙሉ ለመደበኛ በረራዎች ክፍት እንደሚሆን አስታወቁ።
-
85
የሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የአውሮጳ ሕብረት ትግራይ ክልል ውስጥ ሌላ አውዳሚ ጦርነት ከሚያስከትል እርምጃ ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ አሳሰበ። ኢትዮጵያዊን ጨምሮ ዘጠኝ አፍሪቃውያን ስደተኞችን የአሜሪካ መንግሥት ወደ ካሜሮን ማባረሩን ጠበቃቸው ተናገሩ። የተመድ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር ጁጉ ግዛት በደረሰ ጥቃት ምክንያት ወደ 200 ገደማ ነዋሪዎች ተፈናቅለው መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው አመለከተ። የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያሰማራውን የሰላም አስከባሪ ኃይል ቁጥር ለመቀነስ ወሰነ። የሰላም አስከባሪውን የቆይታ ጊዜም እስከ መጪው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2027 ሚያዝያ 30 ቀን ድረስ አራዝሟል።
-
84
የዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
መስቃን፥ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ናይሮቢ፥ በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊውን ለጥቂት ቀድሞ ክብረወሰን ያስመዘገበው ኬኒያዊው አትሌት የጀግና አቀባበል ተደረገለት፤ ብራስልስ፥ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ ፕሬዚደንቶች መካከል የተደረገው የስልክክ ንግግር አውሮጳን ግራ አጋብቷል፤ ቴሕራን፥ የአሜሪካ የፍኖተ ሆርሙዝ የመርከቦች ፍሰት ክልከላ በአካባቢው አደገኛ አለመረጋጋት ይፈጥራል አለች፤ ቤርሊን፥ የኢራን ጦርነት ዓለምን ቢያስጨንቅም ጀርመን ያልተጠበቀ የኤኮኖሚ እድገት ዐሳይታለች፤ ለንደን፥ ብሪታንያ አይሁዶችን ከጥቃት ለመከላከል ተጨማሪ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ለመመደብ ቃል ገባች
-
83
የሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ሳውድ አረቢያ ውስጥ ቢያንስ 65 ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተገናኘ ወንጀል የሞት ቅጣት እንደሚያሰጋቸው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች ዐሳወቀ። ለሁለት ሳምንታት የደረሰበት ያልታወቀው የአዲስ ስታንዳርድ አርታኢ ሚሊዮን በየነ ትናንት ወደ ቤቱ መመለሱን አሠሪው ድርጅት ገለጸ። የዩጋንዳ ባለሥልጣናት ከሕገወጥ የሰዎች ሽግግር እና በበይነ መረብ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በርካታ የውጭ ዜጎች ማሰራቸውን አስታወቁ። ሥር ለሰደደ የምግብ እጥረት የተጋለጠችው ሶማሊያ በማያባራው ግጭት እና የገንዘብ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት የተመድ አመለከተ።
-
82
የሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ62 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ታውቋል። ኢትዮጵያዊያኑ ትናንት የተገደሉት በአንድ ምግቤት ውስጥ በመመገብ ላይ እንዳሉ ነው ፡፡ባሕሬይን አስፈላጊ ተቋሞቿን ፎቶ በማንሳት ለኢራን አስተላልፏል ያለቻቸውን 5 ሰዎች የዕድሜ ይፍታህ እስር ውሳኔ አስተላለፈች። አሜሪካ፤ ኢራን ያቀረበችው የመደራደሪያ ሐሳብ እያጤነችው መሆኗን አስታወቀች።
-
81
የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉና በልዩ ሁኔታ የሚመዘገቡ መራጮች ምዝገባ ማከናወን ዛሬ መጀመሩ አስታወቀ። በደቡብ ሱዳን አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ 14 ተሳፋሪዎችና የበረራ ሰራተኞች በሙሉ አለቁ። የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎች በሶማሊያ የባሕር ክልል ስትጓዝ የነበረችው ስሚንቶ የጫነች መርከብ አገቱ። ሒዝቦላህ፤ ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር የምታካሂደውን ቀጥታዊ ውይይት ውድቅ አደረገ።የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ሐገራቸው የኢራንና በቀጠናው ያሉ ሐገራትን ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚቻላትን ሁሉ ታደርጋለች» አሉ።
-
80
የሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ በጂሃዲስቶች ጥቃት ተገደሉ። በማዕከላዊ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቻድ ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ ዘጠኝ የተቃዋሚ ንቅናቄ ቡድን ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተገኙበት የእራት ግብዣ ስነ ሥርዓት ላይ ተኩስ መከፈቱ እንዳስደነገጣቸው በመግለጽ በርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች ዛሬ ድርጊቱን ኮንነዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ እሁድ ዩናይትድ ስቴትስን እና ኢራንን ወደ ምታደራድረው ፓኪስታን መዲና ኢስላማባድ ተመለሱ። ኬንያዊው ሴባስቲያን ሳዌ በማራቶን ታሪክ ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ።
-
79
የሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመሬት ናዳ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ ። • የሶማሊያ የባህር ላይ ወንበዴዎች በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ የባህር ዳርቻ ላይ አንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ጠለፉ። • በማሊ መዲናዪቱ ባማኮን ጨምሮ ታጣቂዎች በቅንጅት ጥቃት መፈጸማቸውን ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናገሩ። • በጋዛ እና የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ፍልስጤም ግዛቶች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ የአከባቢ አስተዳደር ምርጫ እየተካሄደ ነው። • አሜሪካ እና ኢራን ለተኩስ አቁም ድርድር ባለስልጣናቶቻቸውን ወደ ፓኪስታን መላካቸውን አስታወቁ ።
-
78
የሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። በሶማሊያ በተከሰተው ድርቅ በ 5 ወረዳዎች ብቻ ወደ 62,000 የሚጠጉ ሶማሊያውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት አስታወቀ። እስራኤልና ሊባኖስ ከዚህ ቀደም የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ለሦስት ሳምንታት ማራዘማቸውን የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ማምሻውን ወደ ኢዝላማባድ እንደሚገቡ ኢራን አረጋገጠች።
-
77
የሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ደቡብ ኮርዶፋን ላይ የአየር ጥቃት መጀመሩ ተነገረ። የኢራን ጦርነት መዘዝ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደድህነት ሊመልስ እንደሚችል የተመድ አመለከተ። የአሜሪካ ጦር በዛሬው ዕለት የኢራንን ነዳጅ ዘይት በሕገወጥ መንገድ ጭኗል ያለውን ሌላ መርከብ መያዙን አስታወቀ። በኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል መካከል በመካከለኛው ምሥራቅ የቀጠለው ውዝግብ እንዲያበቃ ፓኪስታን የጀመረችውን ጥረት ቀጥላለች። የዋና ከተማ ኢዝላማባድ መንገዶች መዘጋጋት ሀገሬውን አማርሯል። የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ችሎት ዳኞች የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዝደንት በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ክስ እንደሚቀርብባቸው አስታወቁ።
-
76
የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በአማራ ክልል የዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ጦርነት የአካባቢው አስተዳደር ሰራተኞች መታገታቸው እና ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) አባል የአቶ ታዬ ደንደዓ አዲሱ ክስ ተቋረጠ።የኒጀር መንግሥት 2900 የሀገር ውስጥ እና የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንቅስቃሴን አገደ።ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ መርከቦች ላይ መተኮሷን ቀጥላለች።ሉፍታንዛ 20,000 የአጭር ርቀት በረራዎችን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።
-
75
የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና የህወሐት ውሳኔ የፕሪቶሪያ ውልን ውድቅ ያደርጋል»ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለፁ፤ተቃዋሚው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግሬስ ወደ ትጥቅ ትግል መሸጋገሩን ማስታወቁን፤ናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን አከሸፍኩ ማለቷን፤ በሁለተኛው ዙር የአሜሪካ-ኢራን ውይይት ቫንስ እና ቃሊባፍ እንደሚገኙ መገለጹን በ2025 8000 የሚጠጉ ሰደተኞች ጎዞ ላይ ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ሲል የተመድ መግለፁን ፤ ኢራን ፤ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከ3,600 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች መባሉን እንዲሁምየአውሮፓ ህብረት የኃይል እጥረትን ለመፍታት የኑክሌር ማብላያዎች እንዳይዘጉ ሊያስጠነቅቅ ነው መባሉን አካቷል።
-
74
DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ህወሓት ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት በተካሔደ ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ወደ ሥራ እንዲመለስ” ወሰነ። ፓኪስታን ለሱዳን የጦር መሣሪያዎች እና ተዋጊ ጀቶች ለማቅረብ የገባችውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በይደር ማቆየቷን የሀገሪቱ የደሕንነት የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። የናይጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች በአቡጃ እና በኒጀር ግዛቶች እስላማዊ ታጣቂዎች በመንግሥት መሠረተ-ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዐቅደዋል በሚል ሥጋት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናቸው ተባለ። አሜሪካ የኢራንን መርከብ ከሖርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ መያዟ ዓለም አቀፍ ሕግ እና ሁለቱ ሀገሮች የተስማሙበትን የተኩስ አቁም እንደሚጥስ ኢራን አሳወቀች።
-
73
የሚያዚያ11 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ለመነጋገር የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ነገ ሰኞ ፓኪስታን እንደሚገቡ መግለፃቸው፤የኢራን አጋር የሆኑት የየመን ሁቲ ሚሊሻዎች ቁልፉን የንግድ መስመር ባብ ኤል ማንዳብን እንደሚዘጉ በድጋሚ ማስጠንቀቁ፤ሶሪያ በሂዝቦላህ እና በቀድሞው መሪ አሳድ ቅሪቶች ሊፈፀም ነበር ያለችውን ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ማክሸፏን መግለጿ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና ሃንጋሪ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለመልቀቅ የሚያስችል 'ቴክኒካዊ' ውይይት ማድረጋቸው መግለፃቸውን አካቷል።
-
72
የሚያዝያ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
ስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሠላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የምትቀጥል ከሆነ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን መልሳ እንደምትዘጋ ዛሬ አስጠነቀቀች። እስራኤል የደህንነት ስጋትን ተጨማሪ ቦታ ለማስፋፋት እየተጠቀመችበት ነው ሲሉ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሰሱ።
-
71
የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ኮሬ፥ ደቡብ ኢትዮጵያ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፍተው ነዋሪዎችን ገደሉ፤ ኪንሻሳ፥ ከዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ የተሰናበቱ 15 ደቡብ አሜሪካውያን ኮንጎ ደረሱ፤ ቤሩት፥ እሥራኤል እና የሊባኖሱ ሒዝቦላህ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ፤ ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍኖተ-ሆርሙዝ ከእንግዲህ «መቼም» አይዘጋም አሉ፤ ቴሕራን፥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ተኩስ አቁሙ ተጥሶ ጥቃት ቢደርስበት እንደሚበቀል አስጠነቀቀ፤ ናይፒይዳው፥ ምያንማር በዓመታዊ ልማዷ 4,000 እስረኞችን ነጻ ለቀቀች
-
70
የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም
ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ እና ሲቪል የለበሱ በተባሉ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው የአዲስ ስታንዳርድ ማኔጂንግ ኤዲተር ሚሊዮን በየነ እስካሁን ያለበት ቦታ እንዳልታወቀ ተገለፀ። -ትራምፕ «እስራኤል እና ሊባኖስ ለ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል»-የኬንያ ፍርድ ቤት አንድ ቻይናዊ ህገ-ወጥ የጉንዳን አዘዋዋሪ ላይ የአንድ ዓመት እስራት ፈረደ።-የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በካሜሩን የሚገኙ ባለስልጣናት ሕሊናቸውን እንዲመረምሩ እና "የሙስና ሰንሰለትን" እንዲሰብሩ ጥሪ አቀረቡ።
-
69
የሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
አራተኛ ዓመቱን በያዘው የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በረሐብ እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን ለመርዳት ጀርመን 20 ሚልዩን ዩሮ እንደምትለግስ አስታወቀች። አሜሪካ ከኢራን ወደቦች የሚወጡና የሚገቡ መርከቦችን ማገዷን ከቀጠለች በቀይባሕር፣ የፐርሺያ ባሕረሰላጤና በኦማን የባሕር ሰርጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ እንደምታግድ ኢራን አስጠነቀቀች። እስራኤል በአለፉት 24 ሰዓታት በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ከ200 በላይ «የሒዝቦላሕ ወታደራዊ ይዞታዎች» ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።
-
68
የሚያዚያ 6 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና ፤የናይጄሪያ ፖሊስ በምዕመናን እገታ የተሳተፉ 33 አባላት ያሉት የወሮበሎች ቡድንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለፁ፤የቤኔን የምርጫ ኮሚሽን የዘንድሮውን ሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ይፋ ማድረጉን፤ሊባኖስ እና እስራኤል ቀጥተኛ የዲፕሎማሲ ውይይት ዛሬ በዋሽንግተን ማካሄዳቸውን፣በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የዓለም አቀፍ የእድገት ትንበያ መቀነሱን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለፁን፤ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ንግግራቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ ፈረንሣይ ጥሪ ማቅረቧን እንዲሁም የጀርመን መራሄ መንግስት አውሮጳ በማንኛውም የዩክሬን የሰላም ስምምነት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባት ማለታቸውን ያስቃኛል።
-
67
የሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሱዳናውያን ሕይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ቅጠላ ቅጠልና የእንስሳት መኖ ጭምር ለመመገብ መገደዳቸውን 5 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታወቁ። በናይጄርያ ሰሜን ምስራቅ በምትገኝ አንዲት መንደር የሐገሪቱ አየር ሃይል በገበያ ቦታ ፈጸመው በተባለው የአየር ድብደባ ቢያንስ 200 ሰላማዊ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ወደቦች በሙሉ እንዲዘጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ኢራን ፈጣን የዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።
-
66
የሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትንሳኤ በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በመላው ዓለም መከበሩን ፣በቤኒኒናውያን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ መዋላቸውን፣አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን፣ኩዌት በሐገር ደሕንነት ላይ ያነጣጠረ የሽብር ሴራን አከሸፍኩ ማለቷን እና ሳውዲ አረቢያ በድሮንና በሚሳይል ጥቃቶች ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የሓይል መሰረተ ልማቶችን ጠግና ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጓን ያስቃኛል።
-
65
የሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ኢትዮጵያ ውስጥ የከርቤ ዛፍ በድርቅ ምክንያት እየተመናመነ እንደሆነ አሶሺየትድ ፕረስ ዘገበ። የጅቡቲው ፕሬዝደንት ጉሌሕ 97.81% የመራጭ ድምፅ በማግኘት አሸነፉ። የእስራኤል ጦር ባለፉት 24 ሰዓታት ሊባኖስ ውስጥ ከ200 በላይ የሂዝቦላ ኢላማዎች መደብደቡን አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚደረግ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት እንዲቆም ጠይቁ። የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ የፊት ለፊት ድርድር ዛሬ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ጀምሯል። ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ አቅራቢያ የነበሩት የጠፈር ተመራማሪዎች በሰላም ወደ ምድር ተመለሱ።
-
64
DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በዎላይታ ዞን ከባድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 7 ሰዎች ሲሞቱ 6 ተጎዱ። ኢሕአፓ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅትን ወክለው ለድሬደዋ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ አባሉን እስር አወገዘ። የጅቡቲ ዜጎች ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ያሸንፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ጄድ ቫንስ በኢዝላማባድ ድርድር ኢራን ዩናይትድ ስቴትስን "ለማታለል" እንዳትሞክር አስጠነቀቁ። የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት በሊባኖስ የተኩስ አቁም መደረግ እንዳለበት ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል።
-
63
የሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ባገረሸው የመጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ተሰማ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በመጪዉ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ10 የኢትዮጵያ ከተሞች የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያከናውን አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተረዥ ኢራን በሊባኖስ ስቪል ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በጥብቅ አወገዙ።
-
62
የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቀዬያቸው ተፈናቀሉ። የጅቡቲ ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ ዓርብ የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚያሸንፉ እየተጠበቀ ነው። እስራኤል በኢራን የሚደገፈውን የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ለማጥቃት በሚል ሊባኖስን ደብድባለች። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ዛሬ በዋይት ሀውስ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢራን እና በአዘርባጃን የባህር ዳርቻዎች ዛሬ በሬክተር ስኬል መለኪያ 5.6 የነበረ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።
-
61
የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-ከ80 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንደሚለለዉ 120 ስደተኞች አሳፍራ ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ ትቀዝፍ የነበረች አነስተኛ ጀልባ ባለፈዉ ዕሁድ ሰጥማለች።32ቱ በሕይወት ተርፈዋል።-----የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላዉን ተቋማትና ይዞታዎች በደብደባቸዉን ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።የቃላት ጦርነቱም እንደናረ ነዉ።---ጦርነቱ የእርዳታ ምግብ፣መድሐኒትና ቁሳቁስ እንዳይንቀሳቀስ ወይም እንዲዘገይ ማድረጉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች አስታወቁ።
-
60
የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና እሥራኤልና አሜሪካ ዛሬ በኢራን ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከ25 ሰዎች በላይ ተገደሉ። ከመካከላቸው የኢራን ፈጥኖ ደራሽ አብዮታዊ ዘብ የስለላ ክፍል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ማጃድ ክሀዴሚ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ዛሬ በእሥራኤል ላይ ዛሬ ከኢራን ከሂዝቦላ እና ከየመን በተመሳሳይ ጊዜ ጥቃቶች ተፈጽመውባታል ኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ ለ45 ቀናት የተኩስ አቁም እንዲያደርጉና የሆርሙዝ ሰርጥም እንዲከፈት የቀረበውን ረቂቅ ምክረ ሃሳብ ኢራን እንደማትቀበለው አስታወቀች የናይጀሪያ ጦር ት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተፈፀሙ ሦስት ጥቃቶች ቢያንስ 26 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቁ ።
-
59
የመጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም። ሰሜንናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ ታጣቂዎች ትናንት ቅዳሜ በፈጸሙት ጥቃት አራት የፖሊስ መኮንኖች ተገደሉ ። ኢራን በዛሬው ዕለት በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟን የየሐገራቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
-
58
የመጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና፤ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከአንድ ሺ ለሚበልጡ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ፤ሴኔጋል ከኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን የነዳጅ ወጭ ለመቀነስ የባለስልጣናትን የውጭ ጉዞ መገደቧን፣ የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች ኢራን ውስጥ ዛሬም በርካታ ቦታዎችን ኢላማ ማድረጋቸውን፣ የተባበሩት መንግስታት የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለማስከፈትን በተመለከተ ለዛሬ ታቅዶ የነበረው ድምጽ አሰጣጥ ለሌላ ጊዜ መገፋቱን ፤አሜሪካ በኢራን ተመቶ ከወደቀ አውሮፕላን አንድ አብራሪዋን መታደጓን ባለስልጣናት መግለፃቸውን እና ኔዘርላንድ በሚገኝ አንድ የእስራኤል ደጋፊ ማዕከል ላይ ፍንዳታ በመከሰቱን ያስቃኛል።
-
57
የመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ፤የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና፤ በሀዋሳ ከተማ በመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን፤የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሀገራቸው ላይ የጣለችው ማዕቀብ «ለሩዋንዳ ስድብ» ሲሉ መግለፃቸውን፤በኢራን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ማስታወቁን፤ኢራን እና እሥራኤል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት መቀጠሉን፤ ኢራን ዉስጥ አንድ የአሜሪካተዋጊ ጄት ተመትቶ ወደቀ መባሉን እንዲሁም ፈረንሳይ እና ደቡብ ኮሪያ የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት በጋራ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ያስቃኛል።
-
56
የመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የጣሊያን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የ19 ተሰዳጆችን አስከሬን ማግኘታቸው ተገለጸ። ሌሎች 58 ተሰዳጆችን በሕይወት አትርፈዋል። ከአሜሪካን የተባረሩ 12 ወደየትውልድ ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ስደተኞች ዩጋንዳ መግባታቸውን የዩጋንዳ የሕግ ማኅበረሰብ ዛሬ አስታወቀ። ኢራን በዛሬው ዕለትም በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው የአረብ ሃገራት ላይ የሚሳኤል ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች። ፕሬዝደንት ትራምፕ ኢራን ከእንግዲህ የሚያሰጋ ኃይል የላትም እያሉ ነው። ፈረንሳይ የሆርሙዝን መተላለፊያ ለማስከፈት ኃይል መጠቀሙ አዋጪ እንዳልሆነ አሳስባለች። ሩሲያ ቡሼር ከተሰኘው ከኢራኑ የኒኩሊየር የኃይል ተቋም ዜጎቿን ማስወጣት ጀምራለች።
-
55
የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል "አስቻይ ኹኔታ" የለም በሚል አጀንዳ የማሰባሰብና የጉባኤ ተሳታፊ ልየታ ሥራ ዛሬ አዲስ አበባ ከሚኖሩና ከክልሉ መጡ ከተባሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር ማካሄድ በጀመረበት በዛሬው መድረክ ሥራው በክልሉ ውስጥ እንዲደረግ ተጠየቀ ። ሁለተኛው ወሩን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት አሜሪካና እሥራኤል የኢራን የብረታ ብረት ማምረቻዎችን ደበደቡ። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚካሄድ ምንም ዓይነት ድርድር የለም ሲሉ አስታወቁ።
-
54
DW Amharic የመጋቢት 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና
አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት ምክንያት ለኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያቀርቡ ሀገራት በውላቸው መሠረት ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ተናገሩ። የሶማሊያ ጦር የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት ትልቅ ከተማ የሆነችው ባይዶዋን ተቆጣጠረ። እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራን አፀፋ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ሐገራትን ማዉደሙን ለሁለተኛ ወር እንደቀጠለ ነዉ። ጦርነቱ እንዲቆም ፓኪስታን እና ቻይና ጠይቀዋል እስራኤል በጦር ፍርድ ቤቶች ጥፋተኛ የተባሉ ፍልስጤማውያን ሁሉ በስቅላት እንዲቀጡ ያጸደቀችው ሕግ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ሥጋቱን ገለጸ።
-
53
-
52
DW Amharic የመጋቢት 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና
የሶማሊያ ፌድራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ከማባባስ እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ አሳሰቡ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የሚያካሒዱት ውጊያ የሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የቀጠናው ቁልፍ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በፓኪስታን ተሰበሰቡ። ጦርነቱ ዓለም አቀፍ ሕግ እንደሚጥስ ቡንደስታግ ተብሎ የሚጠራው የጀርመን ምክር ቤት የምርምር አገልግሎት ይፋ ያደረገው ሪፖርት አሳየ። በአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ፖሊሲዎቻቸውን ለመቃወም በተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች ቢያንስ 8 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሎ እንደሚገመት አዘጋጆቹ አስታወቁ።
-
51
የመጋቢት 19፣ ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ያስከተለው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለከፋ እንግልት እያጋለጠ ነው ተባለ። • በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በተጠረጠሩ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት ባለቤቶች ላይ ክስ ተመሰረተ። • በኢራን የሚደገፉ የየመኑ ሁቲ አማፂያን በእስራኤል ላይ የሚሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቁ። • በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተዘገበ። • በሜድትራንያን ባህር ላይ በአነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 22ቱ በግሪክ የባሕር ጠረፍ መሞታቸው ተሰማ።
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
HOSTED BY
DW
Loading similar podcasts...