Continental Drift

PODCAST · news

Continental Drift

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.

  1. 21

    "ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ

    በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው አለመረጋጋት—ከአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ እስከ ቀይ ባሕር የጸጥታ ስጋት በአፍሪካውያን ማዕድ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። እንዴት ? "እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ በዕርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው። [...] ይህ ለእኛ ሌላ የዝግጅት ጊዜ ሊሰጠን ይገባ ነበር። እውነቱን ለመናገር፣ የዓለም ሥርዓት ወዴት እየሄደ እንደሆነ በጥንቃቄ ብንከታተል ኖሮ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችል ነበር።" — ሲሉ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ተጽዕኖ በመውጣት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከሥነ-ምግብ ባለሙያና ተመራማሪው አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአፍሪካን መጻኢ ዕድል በመቅረጽ ረገድ ያለውን የወጣቶች ሚና እንቃኛለን። ለዚህም የኢንተርናሽናል ዩዝ ኮኔክት (IYC) ዳይሬክተር ዳንኤል ዚንያማ እና የፓን-አፍሪካኒዝም ተሟጋቿ ኒያሻ አዶር ጋዚምቢ በእንግድነት ቀርበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

  2. 20

    የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች

    በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዓለምን የኢነርጂ ፍሰት እና ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፍ እየቀየረ ነው ። በተለይም በሆርሙዝ የባህር በር ላይ የሚፈጠር አለመረጋጋት በአፍሪካ የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው ። "አፍሪካ አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር ተጋላጭነቷን እና ጥገኝነቷን ለመቀነስ መሞከር ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ምሳሌ ናት። ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአንድ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮቿን በማባዛት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታለች።" ሲሉ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በአጠቃላይ በደቡባዊው የዓለም ክፍል ላይ የሚያሳድረውን ዘለቄታዊ ተጽዕኖ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች እንቃኛለን ። ለዚህም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ፣ በዱባይ ይኖር ከነበረው ተማሪ አናኦል ሚካኤል እና ከስትራቴጂክ ተንታኙ ሚካኤል ገዛኸኝ ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

  3. 19

    የባህረ ሰላጤው የኢነርጂ ቀውስ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት

    በመካከለኛው ምስራቅ የሚከሰት ግጭት እንዴት በአፍሪካውያን የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ በትራንስፖርት እና በምግብ ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥራል? የዓለም የነዳጅ ገበያ መናጋት አፍሪካ የራሷን የኢነርጂ መሠረተ ልማት እንድትገነባ እና በውጭ ገበያ ላይ ያላትን ጥገኝነት እንድትቀንስ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል? "በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ የሚታየው ከፍተኛ መዋዠቅ፣ በተለይም እንደ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ባሉ ማዕቀፎች ውስጥ ጠንካራ የአህጉር አቀፍ የኢነርጂ ትብብር እንዲኖር እንደ ማነቃቂያ ሊያገለግል ይችላል። እዚህ ላይ አንድ ዋና ነጥብ መጥቀስ እንችላለን፤ ምክንያቱም ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ አስፈላጊ ነው፤ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ዓለም አቀፍ የዋጋ ድንጋጤዎች በእነዚህ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆኑ ሀገራትን ተጋላጭነት ጎልቶ እንዲወጣ ያደርጋሉ። በመሆኑም በጋራ ቀጠናዊ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት እና ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ትስስር አማካኝነት ቀጠናዊ የኢነርጂ ትብብርን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪው መሐመድ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በዓለም የነዳጅ አቅርቦት እና በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪው መሐመድ ኢብራሂም ጋር በጥልቀት እንመረምራለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

  4. 18

    መካከለኛው ምስራቅ ፦ የዓለም አቀፍ የሕግና ሥርዓት ዕጣ ፈንታ ነጋሪ

    በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለው ቀውስ የአንድ ቀጠና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት ታላቅ ፈተና ነው። በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን እና የሉዓላዊነት መርሆዎችን አደጋ ላይ ጥሏቸዋል። "ሩሲያና ቻይና ሁነቶቹን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውና ከትዕይንቱ በስተጀርባ የራሳቸውን ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው በጣም ግልጽ ነው። ከሚታየው ነገር ባሻገር ጠልቀን ማየት አለብን። በአንድ በኩል በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኢራን መካከል በመካከለኛው ምስራቅ እየተከሰተ ባለው የፖለቲካ ቀውስ ቻይና እና ሩሲያ በዝምታ ተቀምጠዋል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ይህ ቀጠና ለዓለም አቀፍ ፖለቲካ በጣም ስሜታዊ ስፍራ ነው።" ሲሉ አብዱ መሐመድ (ዶ/ር) ፣ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትን እና የዓለም አቀፍ ሕግጋት መሸርሸርን በተመለከተ ከሁለት ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያዎች — አብዱ መሐመድ (ዶ/ር) የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ እና ከዳዊት መዝገበ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  5. 17

    የዓድዋ ድልና የዘመኑ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት፦ ያልተቋረጠው የሉዓላዊነት ትግል

    የዓድዋ ድል ከጦር ሜዳ ስኬት በላይ፤ አፍሪካውያን የሉዓላዊነት ድርድር የማይደረግበት መሆኑን ለዓለም ያወጁበት የታሪክ ምዕራፍ ነው። ዛሬስ ሉዓላዊነት ሲባል ግዛትን ከመጠበቅ ባለፈ የኢኮኖሚ ፣ ባህል ጥንካሬን እና በሌሎችም ሉዓላዊ ነን ? ወይስ አሁንም በ"ስልጣኔ" ስም በሚቀርቡልን የዲፕሎማሲ ወጥመዶች ውስጥ ተይዘናል? "ጤነኛ አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚያ የአውሮፓውያን ዲፕሎማሲ ውስጥ እንዳይዘፈቅ። እንዳትዘፈቁ! ምክንያቱም አባቶቻችን በምኒልክ ዘመን ያለ ጫማ፣ ያለ ሱፍ ልብስ፣ ያለ ከረባት የአውሮፓውያንን፣ የምዕራብ አውሮፓውያንን ተንኮል ማየት ይችሉ ነበር። እኛ ግን በዚህ ሁሉ ዲግሪ፣ በዚህ ሁሉ ሱፍ እና ዘመናዊ መኪና እነዚህ ሰዎች የሰለጠኑ ስለሚመስሉን ተንኮላቸውን ማየት ተስኖናል። አይደለም፣ እነሱ አረመኔዎች ናቸው። እውነቱን እንጋፈጠው፤ ይህ አረመኔነት ነው።" ሲሉ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ፣ ደራሲ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ ዐቢይ ጥላሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የዓድዋን ድል ትርጉም ከወቅታዊው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል ጋር በማገናኘት፤ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ፣ ደራሲ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ ዐቢይ ጥላሁን ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

  6. 16

    ዓድዋ:- የሉዓላዊነት መሠረትና የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አቀጣጣይ

    የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የተመዘገበው የዓድዋ ድል ጣሊያንን በጦር ሜዳ የማሸነፍ ጉዳይ ብቻ አይደለም።አፍሪካውያን በራሳቸው መደራጀት እና ማሸነፍ እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት የታሪክ ምዕራፍ ጭምር እንጂ። ዛሬም ግን የሉዓላዊነት ጥያቈ መልኩ ብዙ ሆኖ እያየነው ነው። "አፍሪካ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳትጠይቅ በጠንካራ አቋም ወደ ድርድር ጠረጴዛው መምጣት አለባት። እነዚህን ሐሳቦች ስላስተዋወቅን ብቻ ‘ባህላዊ’ ጉዳዮች ሊባሉ አይገባም፤ ምክንያቱም ይህ ማንነታችን በመሆኑ ወሳኝ ነው።[...]‘ጭራው ውሻውን እንዲያወዛውዝ’ መፍቀድ የለብንም።" ሲሉ ፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ለስፑቲክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የዓድዋን ድል ከወቅታዊው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል ጋር በማገናኘት ከፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  7. 15

    አዲሱ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ንቅናቄ፡ የሳህል ቀጠና፣ ሩሲያ እና የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ፍጻሜ

    ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በምዕራባውያን ላይ ያነሱት የሉዓላዊነት ጥያቄ የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካ ቀይሮታል። ለዘመናት "ፀረ-ሽብር" በሚል ሽፋን የተካሄደው የሀብት ዘረፋ እና ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ፣ ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ሞስኮ አዙረዋል። ለመሆኑ ይህ የሽግግር ወቅት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት እና ለባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓት ምን ትርጉም አለው? " የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የሚወሰነው በሩሲያና በአፍሪካ መሪዎች ነው። እና ይህ መሰረታዊ ነገር ነው። የሁለቱ ማለትም ሩሲያ እንደ አንድ ሀገር፣ አፍሪካ እንደ ብዙ ሀገር—የሚሰጡት፣ መሪዎቻቸው የሚወስኑት ነገር ወደፊት የሁለቱን ግንኙነት... የሚወስን ይመስለኛል።" — ፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ፣ በሩሲያ የኢትዮጵያውያን ማህበር ፕሬዝዳንት እና በሩሲያ የስቴት ዱማ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አማካሪ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን (AES) ምስረታን፣ የሩሲያን የ"ያለ ጣልቃ-ገብነት" የአጋርነት መርህ እና የአፍሪካን አዲሱን የነጻነት ትግል ከፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ ጋር በሰፊው እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  8. 14

    የገንዘብ ህትመት በሀገር ውስጥ፡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አዲሱ ምዕራፍ

    ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ ኖት በሀገር ውስጥ የደረሰችው ውሳኔ፣ ከውጭ ኩባንያዎች ጥገኝነት የመላቀቅ እና የገንዘብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ውሳኔ ከዶላር ጥገኝነት ለመውጣት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በሌላ በኩል Make Africa Borderless Now ''አሁን አፍሪካን ንብር የለሽ እናድርጋት ንቅናቄ'' አህጉሪቱን ትስስር ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው። "የራስን ገንዘብ ማተም ካልተቻለ ፣ በራስ ገንዘብ መበደር ፣ መገበያየት እና መቆጠብ ካልተቻለ ፤ ሉዓላዊነት እንደ ሀገር አደጋ ላይ ይወድቃል።[...] የራስን ገንዘብ ማተም የራስን ሀገር በራስ አቅም ከማስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።" ሲሉ መርዕድ ፍቅረዮሐንስ፣ የፕራግማ ኢንቨስትመንት አማካሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ኢትዮጵያ ገንዘቧን በሀገር ውስጥ ማተም የመጀመር ዉጥኗን ትርጓሜ ከኢንቨስትመንት ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ጋር እንፈትሻለን።እንዲሁም አፍሪካን ለትስስር ማነቆ የሆነውን የድንበር ሀሳብን ስለሚታገለው ንቅናቄ ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ባን ዴንግ (ዶ/ር)ጋር እንወያያለን ። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  9. 13

    የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ነፃ ንግድ ቀጣና ፡- ኢትዮጵያ የአፍሪካ እድገትና ሉዓላዊነት ማዕከል የመሆን ውጥን

    ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ለማንቀሳቀስ ስታቅድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ የአፍሪካን የአቪዬሽን ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የኤርፖርት ፕሮጀክት ጀምሯል። እነዚህ የአየር እና የየብስ መሰረተ ልማቶች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና ለአፍሪካ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ነው፣የኢኮኖሚ ዞኖችም ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ። "ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከላዊ ሚና መጫወት አለባት። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ይረዱናል።[...] የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በመጠቀም ያለንን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር አለብን።" ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ዝግጅታችን፣የኢትዮጵያን የኢንደስትሪ ልማትና ከአህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ተጠቃሚነት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ጋር እንመለከታለን። አዲሱ የኤርፖርት ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ያለውን ፋይዳም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ያስተላለፉትን መልእክት እንቃኛለን። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  10. 12

    የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ በአፍሪካ፡- 'ኢትዮ ፔይ' ከዶላር ጥገኝነት ነጻ ለመሆንና ለፋይናንስ ሉዓላዊነት

    የ'ኢትዮ-ፔይ' መጀመር ኢትዮጵያ በዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥናል። በሌላ በኩል፣ ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ብርሃን ባልታደሉበት አፍሪካ፣ የኢነርጂ አቅርቦትንና ብቃትን ማሳደግ ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል።"በዶላር ላይ ጥገኝነት አይኖርም... ቴክኖሎጂው ክፍያዎች በቀላሉ እንዲተላለፉ ያስችላል። ነገር ግን ወደ ተግባራዊ ትግበራው ስንመጣ፣ የሕግ ማዕቀፍ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል። በህግ በኩል፣ ሁለቱ ሀገራት ክፍያው እንዴት እንደሚፈጸምና የገንዘብ ምንዛሪው እንዴት እንደሚሆን መስማማት አለባቸው።" ሲሉ የኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዝግጅታችን፣ 'ኢትዮ-ፔይ' ስለሚፈጥረው ዕድል ከኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ጋር እንወያያለን። ቀጥለን የአፍሪካን የኢነርጂ እንቅፋቶችን ከ'ሰስተነብል ኢነርጂ ፎር ኦል' የኢነርጂ ብቃት ባለሙያ ኤልዛቤት ዋንጌሲ ቼጌ እና ከደቡብ አፍሪካ የኤሌክትሪክ እና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ሳማንታ ግራሃም-ማሬ ጋር እንፈትሻለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  11. 11

    ፋይዳ በለውጥ መንገድ፡ ዲጂታል ማንነት፣ የመረጃ ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ "ፋይዳ" ከሙከራ ደረጃ አልፎ አሁን ላይ መላውን ሀገራዊ ሥርዓት እያስተሳሰረ ይገኛል። ባንኮችና የክፍያ ሥርዓቶች ከፋይዳ ጋር መገናኘታቸው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ የዜጎች የግል መረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ስልቶች እየተተገበሩበት ነው ። "የግል መረጃችሁ በትላልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች እጅ ሆኖ በየትኛው የሕግ ሥልጣን ሥር እንደሚገኝ እንኳን ማወቅ[አይቻልም]፤ ምክንያቱም ይህ የኩባንያዎች ምስጢር ነው። ፋይዳን በሚመለከት ግን አንድ ያደረግነው መልካም ነገር የመረጃ ቅነሳ ወይም 'ዳታ ሚኒማይዜሽን' የተሰኘውን መርህ መከተል ነው ፤ ስለዚህ ስለ አንድ ሰው ብዙ መረጃዎችን አንወስድም።" ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ፋይዳ እንዴት የዲጂታል ኢኮኖሚው መሠረት እየሆነ ነው? የመረጃ ደኅንነትና ግልጽነትስ እንዴት ይረጋገጣል? የሚሉትን አንጋቢ ጉዳዮች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ጋር በጥልቀት እንመረምራለን ።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  12. 10

    ኃይል፣ ወደብ እና ቅርስ፡- የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ እና የሉዓላዊነት ትግል

    የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ዕውቅና፣ የሁቲ አማጽያን ዛቻ እና ከእስራኤል ጋር የገብበት ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ከብሪታኒያ ሙዚየም "በብድር" ሳይሆን በክብር የመመለስ ትግል የአፍሪካዊያን ሌላ ሜዳ ሆኗል። "እስራኤል ለሶማሌላንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ እና አስፈላጊነት ትኩረት እየሰጠች ነው፤ ምክንያቱም ሁቲዎች በእስራኤል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው። ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ የሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅናና ትርጓሜውን ከፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር እንፈትሻለን። ተዘርፈው ለእይታ የሚቀርቡበት የብሪታኒያ ሙዚየም ቅርሶችን "በውሰት" ለአፍሪካ ሀገራት የመስጠት እቅድና የተዘረፉ ቅርሶችን የማስመለስ ሂደት የትግል መልክን በተመለከተም ከቅርስ አስተዳደር እና ጥበቃ ከፍተኛ ተመራማሪ ተስፋዬ አራጌ ጋር እንወያያለን።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  13. 9

    የአፍሪካ የሉዓላዊነት ትግል፡ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የአስተሳሰብ ነጻነት

    አፍሪካ በአሁኑ ወቅት የዓለም የኃይል ሚዛን በሚቀያየርበት ባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የራሷን ድምፅ ለማሰማት እና የፖለቲካ ተጽዕኖዋን ለማሳደግ እየጣረች ትገኛለች። "እንደሚታየው አፍሪካ እና እስያ በተለይም ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ነው። በትምህርት ረገድም ሰፊ ግንኙነት አለን። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አፍሪካ ውስጥ ከሩሲያ ትምህርትን እና ሌሎች ድጋፎችን ለማግኘት የሚያስችሉ የዳታ ማኔጅመንት ዕቅዶች አሉን።" ሲሉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ይመር አሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያላትን ስልታዊ ቦታ እና ከሩሲያ ጋር ያላትን ተግባራዊ ግንኙነት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ከሆኑት ይመር አሊ ጋር እንፈትሻለን። በመቀጠልም፣ የአስተሳሰብ ሉዓላዊነትን እና አፍሪካዊ የሆኑ የንድፈ-ሀሳብ እውቀቶችን የማዳበር አስፈላጊነትን የ"ካፒታል ቫዮለንስ " መጽሐፍ ጸሐፊ ዋቪንያ ማካይ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

  14. 8

    የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ምርት አዲስ መልክ

    የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ዘርፍ ባለው ከፍተኛ እምቅ አቅም ልክ ተገቢውን ዋጋ አላገኘም። በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስፈን በደቡብ-ደቡብ ትብብር እና በሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ላይ እየሰራች ነው። የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅድስት አምዴ "እኛ ጋር ወደ 23 የሚደርሱ የምግብ ቅመሞች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ አንዳንዶቹን አናውቃቸውም። ወደ 800 የሚጠጉ የመድኃኒት ዕፅዋትም አሉን። ይህ በጣም ሰፊ የልዩ ልዩ ዝርያዎች ሀብት ነው። በየቦታው አይገኝም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ዕድል አለ ብዬ አስባለሁ።" ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የጉዋሮ ማይክሮ-ፋብሪካዎች የአርሶ አደሩን ገቢ እና የሀገርን የግብርና ዘርፍ መዋቅር እንዴት እየቀየሩ ነው? የሚለውን እንመለከታለን። ለዚህም የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅደስት አምዴን ጋብዘናል። እንዲሁም፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ዘሪሁን ደምረው (ዶ/ር) እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በትብብር እንዴት ታረጋግጣለች? በሚለው ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት እንፈትሻለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  15. 7

    ኃይል፣ ትብብር እና ምርት፡ የአፍሪካ አዲሱ የሉዓላዊነት መንገድ

    "[...] የብሪክስ ቁልፍ መርህ የሉዓላዊነትን ማስከበር፣ የሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ነባራዊ እውነታዎችን ማክበር ነው። በኢነርጂ ዘርፉም ቢሆን የምናደርገው ትብብር ይህንን ያገናዘበ ነው።" ሲሉ የሩሲያ የኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ሶስት የተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮችን እንመለከታለን በቀዳሚነ የብሪክስ የኢነርጂ ትብብር ለኢትዮጵያ ምን ይዞ መጥቷል ፣ ለአፍሪካ የኢነርጂ ሉዓላዊነትስ ምን ማለት ነው ስንል የሩሲያ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ አነጋግረናቸዋል፡፡ በሁለተኛው ክፍል ከታህሳስ 2 እስከ 3 በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ መነሻ አድርገን አፍሪካንና የሃይል ትስስርን እንዲሁም የብሪክስ ጥምረትን ሚና ከኬንያ ኢነርጂ ሚኒስቴር የታዳሽ ኃይል ረዳት ዳይሬክተር ጆርጅ ኒዮንጋዮ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የኢነርጂ ብቃት ባለሙያ ጃሌል ቻብቹብ እና ከሌሎች የጉባዔው ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ጠይቀናል። የሀገር ውስጥ አምራቾች የገበያውን ክፍተት እንዴት እየሸፈኑ ነው? የ ቅመም ዕፅዋት ውጤቶች መስራች መቅደላዊት ያሬድ እና ዲዛይነት ቤተልሄም ጌታቸው ያነጋገንበት ጉዳይም በዚሁ መሰናዶ ውስጥ ተካትቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  16. 6

    ከፖሊሲ አውጪነት ወደ ፖሊሲ ተቀባይነት :- በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የተደቀኑ ፈተናዎች በአፍሪካ

    አፍሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለእዳ ክፍያ በማውጣት፣ ከጤናና ትምህርት በለጠ የፋይናንስ ጫና ውስጥ ወድቃለች ። " አለምዓቀፉን የገንዘብ ተቋም በተቀበልክ ጊዜ፣ የማክሮ ፖሊሲህን በሙሉ አሳልፈህ ትሰጣለህ። እኔ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነኝ፤ ሁሉንም ፖሊሲዎች አውቃለሁ። ከአይ.ኤም.ኤፍ. ጋር ስምምነት ስትፈጽም፣ የማክሮ ፖሊሲ የመወሰን አቅምህን በጠቅላላ ታጣለህ። የፊስካል ፖሊሲ ታጣለህ፤ የገንዘብ ፖሊሲ ታጣለህ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ታጣለህ። በመሠረቱ ራስን በራስ የማስተዳደር አቅምህን ታጣለህ።" ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ማን ነው? በሚለው ሀሳብ ዙሪያ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡ የኢትዮጵያ የወይን ዘርፍ በአለምአቀፍ ገበያ እንዴት ተወዳዳሪ መሆን ይችላል ? የብሪክስና የደቡብ ለደቡብ ትብብሮችስ ምን አይነት እድልና አቅሞች ይፈጥሩለታል ስንል ከወይን ባለሙያ ዳዊት ዳንኤል ጋር ሰፊ ውይይትን አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  17. 5

    ፍትህ በችሎት ላይ : የአፍሪካ ድምፆች ከአለምዓቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባሻገር

    ፍትህ የውጭ ተጽዕኖን ሲከናነብ ፣ ማን ይዳኛል ? ማንስ ደግሞ በነጻ ይለቀቃል? '' የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምስረታን ስንመለከት፣ አብዛኞቹ ለክስ የሚቀርቡ ጉዳዮች የአፍሪካ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ለጦርነቶች አስተዋጽኦ የሚያደርጉት አብዛኞቹ ሀገራት ግን የአፍሪካ ሀገራት አይደሉም። ስለዚህ እንደ አፍሪካውያን የዉስጥ ጉዳዮቻችንን የምናይበት የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምናቋቁምበት ጊዜ አሁን እንደሆነ አምናለሁ። ራሳቸውን ከአይሲሲ ቻርተር ያገለሉትን የአፍሪካ ሀገራትንም ማድነቅ ወይም ማመስገን እወዳለሁ '' ስትል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች። በዚሁ የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን እናያለን ፣ አፍሪካዊያን ለምዕራባዊያ ባደሩ የ'ፍትህ ተቋማት ስለሚፈጸምባቸው በደልና እና የአፍሪካ ሀገራት አማራጮች ምንድን ናቸው ስንል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች የቀድሞ ተመራቂዎች ኮሚሽን ፌዴሬሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር አልፍሬድ ኤሊ ፣ የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲን እና የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን የሰሜን አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ራታኒያ ዳዊን ጠይቀናል፡፡ በሌላኛው ጉዳያችን ደግሞ የአፍሪካ የግብርናና ገጠር ልማት ጦችን ለማስመዝገብ አፍሪካ ምን ማድረግ አለባት ስንል የኢንተር አፍሪካ ፊቶሳኒተሪ ካውንስል አስተባባሪ ዶ/ር ሳሊዩ ኒያሲ፣ የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቫላካቲ እና ሌሎችንም አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  18. 4

    የባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የዉዝዋዜዎች ኃይል - ማንነትን ለመግለጥና ለምጣኔ ኃብታዊ እድገት

    ኢትዮጵያ የብዝሃ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ተፈጥሮ ካደላት መገለጫዎቿ እኩሌታ ብዙኃ ቋንቋና ባህል ያላት መሆኑ የልዩ መልካነቷ ማሳያ ነው፡፡ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎቿም ትናንቷን የሚዘክሩ ፣ የነገን መልክ ዛሬ ላይ ለመቅረጽ በብዙ የሚጥሩ ናቸው፡፡ እንዴት ? “ አንደኛ የስራ እድል ምንጭ ይሆናል። የሚጫወቱ ሰዎች ቢበዙ የስራ እድል ነው ብዙ ሙዚቀኛ በዚህ ሙያ ላይ ያሉ ሙዚቀኞች እንደመኖሪያቸው ይሆናል። ሁለተኛ ደግሞ የሀገር ሀብት ነው። እንደ ሀገርም መሸጥ ይቻላል ሙዚቃን መሸጥ ይቻላል ፣ በነገራችን ላይ ያው [ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር] በተለያየ መንገድ ገቢ ማግኘት አለብን ብዬ አስባለሁ። እና አንደኛው ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃ በትልቁ ገቢ ማምጣት ይችላል ብዬ አስባለሁ ፤ ከሌላው አለም። ሙዚቃችንን ብንሸጠው እንደ ሀገር እንጠቀማለን። ዋናው ደግሞ የኢትዮጵያን ጥሩ ገጽታ ታስተዋውቂበታለሽ። ” ሲል የሙዚቃ አጥኚው እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያዊያንን ማንነት ለመላዉ ዓለም ስለሚያንጸባርቁ ባህላዊ ዉዝዋዜዎች እና በኢትዮጵያዊያን መገለጫ ስለሆነው ዋሽንት አንስተን ስለባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ሁሉንአቀፍ አቅማቸው በሰፊው እንነጋገራለን ፤ ለዚህም የፈንዲቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ጋብዘናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  19. 3

    መጭውን ጊዜ መቅረጽ፡ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ፈጠራ ኢኮኖሚ

    ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ170 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውጪ ለምታስገባው የእንጨት ዉጤቶች ወጪን ታወጣለች ።  [...]መንግሥት የእንጨት ሥራ ውጤቶች ከውጭ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ቢያንስ ለመቀነስ ዉሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በውስጡ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ምክንያት ይህ ውሳኔ ተሰርዟል፣ የእንጨት ውጤቶች እንደገና ለማስገባት ተፈቅዷል። ነገር ግን ክልከላው በተጣለበት አስር ወራት ጊዜ ውስጥ እንኳን በሀገር ውስጥ ገበያው ፍላጎት ምክንያት ብዙ ሀገር በቀል የእንጨት ሥራ ውጤት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየአቅጣጫው መጥተው አይተናቸዋል።” ሲሉ የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለሀገሪቱ የፈጠራ ኢኮኖሚ ያላቸውን ሚና ፣ ፈተናና እድሎች በሰፊው እንመለከታለን፡፡ ለዚህም የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ እና የፓራዳይዝ ፋሽን ባለቤትና ዲዛይነት ገነት ከበደን ጋብዘናቸዋል፡፡ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.

HOSTED BY

Eden Teshome

URL copied to clipboard!