Great Truths Podcast (Amharic)

PODCAST · arts

Great Truths Podcast (Amharic)

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/ 

  1. 35

    መላእክት #6 | መላእክት በምድር ላይ ዋናው ተግባራቸው ምን ይመስላል?

    በምድር ላይ የመላእክት ዋናው ሥራቸው ወይም ተግባራቸው እግዚአብሄርን ማምለክና ማገልገል ነው፡፡ በሰማይ ያላቸው የተለምዶ ሥራቸውም እግዚአብሄርን ማመስገን ሲሆን በተለየና ባልተለመደ ሁኔታ ደግሞ ስናየው የእግዚአበሄርን ታሪካዊ የመዋጀትና የመታደግ ሥራውን ወደ ህዝቡ ዘንድ ማሳለጥ ነው፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ገና ከመጀመሪያው አካባቢ ጀምሮ የጌታ መላኣክ ወይም የእግዚአብሄር መልኣክ የሚሉ ሃሳቦች ከእግዚአብሄር ከራሱ ሥራና ተግባር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

  2. 34

    መላእክት #5 | መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?

    በተለምዶ መላእክት ለሰው ልጆች በሥጋ ዓይን የሚታዩ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ መላእክት በወንዶች መልክ የሚገለጡ ፍጥረታት ናቸው (ዘፍ. 18፡2፤ቁ. 16፤፤ 19፡1-22 መሳፍ. 13፡3-21፤ እብ 13፡2)፡፡ ከመለኮታዊ ሥልጣናቸው የተነሳ አንዳንዴ መላእክት የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው መላእክት በሚታይ መልኩ ሲገለጡ የሚያስፈራ ሳይሆን በልዩ የእግዚአብሄር ክብርና ግርማ የተሞሉ እና በሚያስደንቅ ሁኔታም የሚገለጡ ናቸው (ዘኁ. 22፡31፤ 2 ነገስት 6፡17፤ ዳን. 10፡4-9፤ ማቴ. 28፡3፤ ሉቃ. 2፡9 እና ራእይ 10፡1-3)፡፡ በጥቂቱ ሊያስደንቀን የሚሞክረው ነገር ቢኖር ዮሃንስ ሁለት ጊዜ የእግዚአብሄርን መልእክት ወደርሱ ያመጣውን መልኣክ ሊያመልከው ወይም ሊሰግድለት ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ራሱ ይህንን ጉዳይ እንደተቃወመው እንመለከታለን (ራእይ 19፡10 እና 22፡8)[1]፡፡ ይህም ማለት መላእክት ለእግዚብአሄር የሚገባውን ክብር ለራሳቸው ለማድረግ እንደማይፈልጉ ነው፡፡

  3. 33

    መላእክት #4 | በአጠቃላይ የአቋማቸው ሁናቴ ምን ይመስላል?

    መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እና ያለምንም ማመንታት እንደሚነግረን መላእክት ከእግዚአብሄር በታች የሆኑ ፍጥረታትና በእርሱ እቅድና ፈቃድ ብቻ የሚመላለሱና የሚመሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በመላእክትና በእግዚእበሄር መሃል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡ ምክኒያቱም እነርሱ የእርሱ ናቸውና (መዝ. 104-4)፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግላቸውና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሄር በራሱ፤ ለእርሱም ክብር ለሚሆን አገልግሎት የተመረጡ ናቸውና (1 ጢሞ. 5፡21)፡፡ እንዲሁም እንደ እግዚአብሄር ያለ ማን ነው; የሚል ትርጉም ያለው የሚካኤል እና እግዚአብሄር ኃያል ነው የሚል ትርጉም ያለው የገብርኤል የስሞቻቸው ትርጉም በመላእክቱና በእግዚአብሄር መሃል ያለውን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቆረጠውን ግንኙነት ያሳያል፡፡

  4. 32

    መላእክት #3 | በሰማያዊ ሥፍራ መደራጀታቸውና ልዩ ሚናቸው

    መላእክት የሚኖሩት በሰማይ ነው (ሉቃስ 2፡15)፡፡ በሰማያዊው ዙፋኑም ፊት ለፊት እግዚአብሄር የሚያዛቸውን ሁሉ ይታዘዙታል፡፡ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ፈቃዱንም ለማድረግ እንዲሁም እርሱን ለማመስገንና ለማምለክ ሁልጊዜ የተዘጋጁ ናቸው (መዝ. 103፡2021)፡፡ የእግዚአብሄርንም ፊት እያዩ ያመልኩታል (ማቴ 18፡10)፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ የመላእክት ሥራቸው በሰማያት ሆነው እግዚአብሄርን መታዘዝ፤ ማምለክና ማመስገን ነው፡፡

  5. 31

    መላእክት #2 | የተፈጥሮ ችሎታና አቅም

    መልኣክ የሚለው ቃል መጽሃፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው በሁለቱ ቋንቋዎች የሚለውን ለመረዳት መሞከር ይጠቅመናል፡፡ በእብራይስጥ ቋንቋ (mal’ak) ማልኣክ የሚል ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ (angelos) አንጅሎስ ይላል፡፡ ይህም የሚያመለክተን የመላእክት ዋናው አገልግሎታቸው እና ተግባራቸው  ዜና ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች፤ አዋጅ ነጋሪዎችና መልእክተኞች  እንደሆነ ነው፡፡

  6. 30

    መላእክት #1 | መንፈሳዊው ዓለምና የመላእክት መገኛ ሥፍራ

    በመጽሃፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን እንደ ፈጠረ ይነግረናል። ይህም የሚያሳየን እኛ የምንኖርበት ዓለም ሁለት ዓይነት እንደሆነ እና የእግዚአብሄር ዓለም በሁለት ክፍል የተከፈለ እንደሆነ ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች ሁላችን ማንም ሊያየንና ሊረዳን በሚችልበት ሁኔታ የተፈጠርን በቁሳዊ ዓለም የምንገኝ ፍጥረታት ስንሆን መላእክት ግን ሙሉ በሙሉ ከኛ በላይ ሆነው በሰማያዊ ሥፍራዎች የሚገኙ መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ስለዚህ ስለ መላእክት ትክክለኛውን ግንዛቤ ሊሰጠን የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ይህንንም እግዚአብሄር የሚያደርገው በሰማይና በምድር ባለው በጌትነቱ ሥልጣን የቃሉን (የመጽሃፍ ቅዱስን) እውነት በመጠቀም ነው፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ብቸኛው የዚህ እውቀት ምንጩ ሊሆን ይገባል፡፡

  7. 29

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#6 | በወንጌል ያለ አንድነት

    በዘር፤ በጾታ፤ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ከመለያየታችን ባለፈ እኛ ክርስቲኖች ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት እንድንኖረና ለሌሎችም መልካም ምሳሌዎች እንድንሆን ታዘናል (የዮሃንስ ወንጌል 13፡34-3፤ ገላቲያ 3፡28-29)፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቻለ መጠን ሁሉ በአእምሮኣችን አስተሳሰብና በመሳሰሉት ነገሮቻችን ሁሉ አንድ እንድንሆን ተጠርተናል (ዮሃንስ 17፡20-21፤ ፊልጵስዩስ 2፡2፤ ሮሜ 14፡1-15፡13)፡፡ በክርስቲኖች መሃል ክፍፍል ሲፈጠር ለዓለም የምንመሰክረውን ምስክርነታችንን እንደደሚያደናቅፍብን ልናውቅ ገባናል፡፡ በክርስቲናዊ አስተምህሮችም መሃል በተለያዩ ዓይነት ክርክሮች አማካኝነት የሃሳብ ልዩነቶች ሲፈጠሩ የጋራ እምነቶቻችን እተሸረሸሩና  ልዩነቶቻችን እየሰፉ ሲሄዱ የህይወታችን ዋናው ዓላማ የሆነው አንድነታችን እየተዳከመ በመሄድ ለሁለተኛና ለሦሥተኛ ጉዳዮቻችን ሥፍራችንን እየለቀቅን እንሄዳለን ማለት ነው፡፡

  8. 28

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#5 | የወንጌል ምንነት ማጠቃለያ

    በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል ለየት ያለ ቃል ነው፡፡ ቃሉ አጭርና ውስን ቢመስልም በብዙ መንገዶች ሊገለጹ የሚችሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችንና መልእክቶችን የያዘ ቃል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- በመጀመሪያ ደረጃ በብሉይ ኪዳን ዋና እምብርት ላይ የተጠቀሱትን የድነትን ተስፋዎች ሁሉ አቅፎ በመያዝ ጉዳዩን በሚገባ ያብራራል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ያዘጋጀውን መልካም ዜና ግልጽ አድርጎ ይነግረናል፡፡ እንዲሁም  ሰዎች ስለ ክርስቶስ የተነገረውን እውነት እና የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራውን በሚገባ እንዲረዱ ለአድማጮች ሁሉ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በመጨረሻም፡- ይህ “ወንጌል” የሚለው ስም ራሱ በቀደመቺው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩ ሥፍራ ተሰጥቶት የኢየሱስን ታሪክና ድንቅ ሥራዎቹን መናገር ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለውም ትውልድ ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ በአዲስ ኪዳናችን ውስጥ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል በተለየ ሁኔታና መልክ የምንረዳው ቃል ቢሆንም ለሁሉም ሰው ሊሆን በሚችል መልኩ በቀላሉ ሊገለጽ የሚችል የእግዚአብሄር መልእክት ነው፡፡ 

  9. 27

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#4 | አምስት ማጣፈጫዎች ክፍል 3

  10. 26

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#3 | አምስት ማጣፈጫዎች ክፍል 2

  11. 25

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#2 | አምስት ማጣፈጫዎች ክፍል 1

  12. 24

    የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#1 | መቅደም

    ልናውቀው የሚገባን ትልቅ ነገር ቢኖር ሞት በጣም አስጨናቂ ነገር እንደሆነና በዚህች ምድር ምንም ዓይነት ነገር ዘላለማዊ እንዳልሆነ ነው፡፡  ይሁን እንጂ ማንም ሞትን ቢጠላና ቢቃወም እንኳን ከሞትና ሞት ከሚያስከትለው የጋራ ጉዳት ማምለጥ የሚችል አይኖርም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ከኃጢኣትና ከሰው ልጆች ክፋት የተነሳ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ዘር ሁሉ በሚያሳዝን ሁኔታ የመከራና የጭንቀት ሸክም የበዛበትና ጥልቅ የሆነ ምህረት የሚያስፈልገው ፍጥረት ሆኖ ሊቀር ችሎአል፡፡ ከነዚህ ከባባድ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች የተነሳ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መልካም ዜና ሆኖ በመቅረብ ከዘለዓለም ጥፋትና ሞት ሊያድነንና ሊታደገን ወርቃማ መጽናናትን፤ ንጹህ ተስፋንና ለሁሉም ዓይነት ችግር ልዩ መፍትሄ ሆኖ እንደቀረበልን እንረዳለን፡፡

  13. 23

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #23 | የኢየሱስ ትንሣኤ ውጤቶች

    የክርስቶስ ቤዝዎት ሥራ፣ ትምህርቱ፣ ፈውሱ፣ መከራው፣ ሞቱና ትንሣኤው ፍጻሜ የሚያገኝበት ጊዜ አለ። ይሁን እንጂ የኢየሱስ ሥራ ቀጣይነት ላይ ግራ የሚያጋባ ነገር ሊኖር አይገባም። ከሞት የተነሣው የትንሣኤው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ “እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜም ከእናንተ ጋራ ነኝ” እንዳላቸው ማለት ነው (ማቴ. 28፥20)።

  14. 22

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #22 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 6)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶችን የያዘ ነው።

  15. 21

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #21 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 5)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶችን የያዘ ነው።

  16. 20

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #20 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 4)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶችን የያዘ ነው።

  17. 19

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #19 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 3)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶችን የያዘ ነው።

  18. 18

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #18 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 2)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶች የያዘ ነው።

  19. 17

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #17 | የኢየሱስ ትንሣኤ ፋይዳዎች (ክፍል 1)

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ እግዚአብር ለሰው ልጆች የሕይወት ተሐድሶ ያቀደውን ዕቅድ በተግባር እንዳበሰረው መገንዘብ ይቻላል። የእርሱ ትንሣኤ የኛን የሕይወት ተሐድሶና ያም መታደስ ያመጣውን ለውጥ ወክሎታል። ምክንያቱም የሕይወታችን ለውጥ ወይም ተሐድሶ ውጤት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ የመጽቅን፣ ዳግመኛ የመወለድንና ከእርሱ ጋራ ከሙታን የመነሣትን ዋና ዋና ትሩፋቶችን የያዘ ነው።

  20. 16

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #16 | የኢየሱስ ትንሣኤ አስፈላጊነቱ (ክፍል 3)

    ጌርሃርደስ ቮስ የተሰኘ ምሁር እንደገለፀው የክርስቶስን ትንሣኤ ከሦስት የተለያዩ ጥቅሞች አንጻር ማየት እንችላለን፣ 1)     ዐዋጃዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ የመታወጅ ባሕርይ ያለው ሲሆን፣ እርሱ ከሞት በመነሣት ምክንያት በማንነቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው የሠራቸው ሥራዎች ወደ ሌሎች ሰዎች ይደርሳል ማለት ነው። 2)    ምሳሌያዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ ሥራው የሚከወንበት መንገድ ለሌሎች የክርስቶስ ተከታይ አማኞች ትልቅ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው።3)    መሣሪያዊ ፋይዳው፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ መሠረቱና ጥቅሙ የርሱ አማኞች የሆኑ በሙሉ ያንኑ መንገድ ተከትለው ለሙታን ስለሚነሡ እንደ ቀዳሚ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው (ቮስ 3.5.47-48; Single-Volume Edition, 582-83)። 

  21. 15

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #15 | የኢየሱስ ትንሣኤ አስፈላጊነቱ (ክፍል 2)

    ጌርሃርደስ ቮስ የተሰኘ ምሁር እንደገለፀው የክርስቶስን ትንሣኤ ከሦስት የተለያዩ ጥቅሞች አንጻር ማየት እንችላለን፣ 1)     ዐዋጃዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ የመታወጅ ባሕርይ ያለው ሲሆን፣ እርሱ ከሞት በመነሣት ምክንያት በማንነቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው የሠራቸው ሥራዎች ወደ ሌሎች ሰዎች ይደርሳል ማለት ነው። 2)    ምሳሌያዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ ሥራው የሚከወንበት መንገድ ለሌሎች የክርስቶስ ተከታይ አማኞች ትልቅ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው።3)    መሣሪያዊ ፋይዳው፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ መሠረቱና ጥቅሙ የርሱ አማኞች የሆኑ በሙሉ ያንኑ መንገድ ተከትለው ለሙታን ስለሚነሡ እንደ ቀዳሚ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው (ቮስ 3.5.47-48; Single-Volume Edition, 582-83)። 

  22. 14

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #14 | የኢየሱስ ትንሣኤ አስፈላጊነቱ (ክፍል 1)

    ጌርሃርደስ ቮስ የተሰኘ ምሁር እንደገለፀው የክርስቶስን ትንሣኤ ከሦስት የተለያዩ ጥቅሞች አንጻር ማየት እንችላለን፣ 1)     ዐዋጃዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ የመታወጅ ባሕርይ ያለው ሲሆን፣ እርሱ ከሞት በመነሣት ምክንያት በማንነቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው የሠራቸው ሥራዎች ወደ ሌሎች ሰዎች ይደርሳል ማለት ነው። 2)    ምሳሌያዊ ፋይዳ፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ ሥራው የሚከወንበት መንገድ ለሌሎች የክርስቶስ ተከታይ አማኞች ትልቅ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው።3)    መሣሪያዊ ፋይዳው፥ ይህ ማለት የክርስቶስ ትንሣኤ መሠረቱና ጥቅሙ የርሱ አማኞች የሆኑ በሙሉ ያንኑ መንገድ ተከትለው ለሙታን ስለሚነሡ እንደ ቀዳሚ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው (ቮስ 3.5.47-48; Single-Volume Edition, 582-83)። 

  23. 13

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #13 | የኢየሱስ ትንሣኤ እውነተኝነት (ክፍል 4)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የተለመዱ ታሪካዊ ክሥተቶችንና የተፈጥሮ ሕጎችን ሁሉ ዐልፎ የሚሄድ ታሪካዊ እውነት ነው። ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር የተለመዱ ተፈጥሯዊ ሕጎችንና ደንቦችን በሙሉ በመጣስ በክርስቶስ ትንሣኤ ድንቅ ተኣምራዊ ሥራውን ሠርቷል። የክርስቶስ ትንሣኤ ከሰዎች ጥበብና መረዳት፣ እንዲሁም ከተፈጥሮ ሂደት በላይ የሆነ ክሥተት ነው። በተጨማሪም ክሥተቱ ከእግዚአብሔር የማዳንና ፍጥረትን የማደስ ሥራ ጋራ የተቆራኘ ነው። 

  24. 12

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #12 | የኢየሱስ ትንሣኤ እውነተኝነት (ክፍል 3)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የተለመዱ ታሪካዊ ክሥተቶችንና የተፈጥሮ ሕጎችን ሁሉ ዐልፎ የሚሄድ ታሪካዊ እውነት ነው። ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር የተለመዱ ተፈጥሯዊ ሕጎችንና ደንቦችን በሙሉ በመጣስ በክርስቶስ ትንሣኤ ድንቅ ተኣምራዊ ሥራውን ሠርቷል። የክርስቶስ ትንሣኤ ከሰዎች ጥበብና መረዳት፣ እንዲሁም ከተፈጥሮ ሂደት በላይ የሆነ ክሥተት ነው። በተጨማሪም ክሥተቱ ከእግዚአብሔር የማዳንና ፍጥረትን የማደስ ሥራ ጋራ የተቆራኘ ነው። 

  25. 11

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #11 | የኢየሱስ ትንሣኤ እውነተኝነት (ክፍል 2)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የተለመዱ ታሪካዊ ክሥተቶችንና የተፈጥሮ ሕጎችን ሁሉ ዐልፎ የሚሄድ ታሪካዊ እውነት ነው። ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር የተለመዱ ተፈጥሯዊ ሕጎችንና ደንቦችን በሙሉ በመጣስ በክርስቶስ ትንሣኤ ድንቅ ተኣምራዊ ሥራውን ሠርቷል። የክርስቶስ ትንሣኤ ከሰዎች ጥበብና መረዳት፣ እንዲሁም ከተፈጥሮ ሂደት በላይ የሆነ ክሥተት ነው። በተጨማሪም ክሥተቱ ከእግዚአብሔር የማዳንና ፍጥረትን የማደስ ሥራ ጋራ የተቆራኘ ነው። 

  26. 10

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #10 | የኢየሱስ ትንሣኤ እውነተኝነት (ክፍል 1)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የተለመዱ ታሪካዊ ክሥተቶችንና የተፈጥሮ ሕጎችን ሁሉ ዐልፎ የሚሄድ ታሪካዊ እውነት ነው። ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር የተለመዱ ተፈጥሯዊ ሕጎችንና ደንቦችን በሙሉ በመጣስ በክርስቶስ ትንሣኤ ድንቅ ተኣምራዊ ሥራውን ሠርቷል። የክርስቶስ ትንሣኤ ከሰዎች ጥበብና መረዳት፣ እንዲሁም ከተፈጥሮ ሂደት በላይ የሆነ ክሥተት ነው። በተጨማሪም ክሥተቱ ከእግዚአብሔር የማዳንና ፍጥረትን የማደስ ሥራ ጋራ የተቆራኘ ነው። 

  27. 9

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #9 | ትንሣኤ ሁሉን ቻይነትን መሠረት ያደረገ ነው (ክፍል 2)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የእምነታችንን ቁልፍ ስፍራ ይይዛል። በክርስቶስ ትንሣኤ ሞት ማመናችን በእግዚአብሔር መታመናችንና በርሱ መተማመናችንን የሚያረጋግጥ ልዩ መገለጫ ነው። ያለ ክርስቶስ ትንሣኤ ክርስቲያናዊ ትምህርቶች ምንነትና ትርጒም አይኖራቸውም። ክርስቶስንም ሆነ የአማኝን ተስፋ ያለ ኢየሱስ አካላዊ ትንሣኤ ለማወጅ መጣር፣ የእምነትን መሠረታዊ እውነት ወደ ሚንድ ደረጃ የሚያደርስ ነገር ሲሆን የክርስቶስ ወንጌል የሞቱና የትንሣኤው ወንጌል ነው። 

  28. 8

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #8 | ትንሣኤ ሁሉን ቻይነትን መሠረት ያደረገ ነው (ክፍል 1)

    የክርስቶስ ትንሣኤ የእምነታችንን ቁልፍ ስፍራ ይይዛል። በክርስቶስ ትንሣኤ ሞት ማመናችን በእግዚአብሔር መታመናችንና በርሱ መተማመናችንን የሚያረጋግጥ ልዩ መገለጫ ነው። ያለ ክርስቶስ ትንሣኤ ክርስቲያናዊ ትምህርቶች ምንነትና ትርጒም አይኖራቸውም። ክርስቶስንም ሆነ የአማኝን ተስፋ ያለ ኢየሱስ አካላዊ ትንሣኤ ለማወጅ መጣር፣ የእምነትን መሠረታዊ እውነት ወደ ሚንድ ደረጃ የሚያደርስ ነገር ሲሆን የክርስቶስ ወንጌል የሞቱና የትንሣኤው ወንጌል ነው። 

  29. 7

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #7 | የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ባሕርይ (ክፍል 2)

    የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፣ ግልጽ ያልሆነ ስውር ምስጢር ወይም በንግግር ደረጃ ብቻ ሊገለጽ የሚቻል ነገር ሳይሆን፣ በእውን የተደረገ አካላዊና ታሪካዊ ሀቅ ነው። ትንሣኤው በተግባር የተከናወነ፣ በበርካቶች በስፋት የተመሰከረ፣ ለብዙዎች ፊት ለፊት የታየና እውነት ስለ መሆኑ የተረጋገጠ ክሥተት ነው። የክርስቶስ ትንሣኤ ከታሪካዊ እውንነቱም በላይ፣ የርሱን መለኮታዊ ኀይል ከወቅታዊው ታሪካዊ ክሥተት ጋራ አቆራኝቶ የሚያሳይ ነው።

  30. 6

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #6 | የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ባሕርይ (ክፍል 1)

    የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፣ ግልጽ ያልሆነ ስውር ምስጢር ወይም በንግግር ደረጃ ብቻ ሊገለጽ የሚቻል ነገር ሳይሆን፣ በእውን የተደረገ አካላዊና ታሪካዊ ሀቅ ነው። ትንሣኤው በተግባር የተከናወነ፣ በበርካቶች በስፋት የተመሰከረ፣ ለብዙዎች ፊት ለፊት የታየና እውነት ስለ መሆኑ የተረጋገጠ ክሥተት ነው። የክርስቶስ ትንሣኤ ከታሪካዊ እውንነቱም በላይ፣ የርሱን መለኮታዊ ኀይል ከወቅታዊው ታሪካዊ ክሥተት ጋራ አቆራኝቶ የሚያሳይ ነው። 

  31. 5

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #5 | የትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንበያና ታሪካዊ ዳራ (ክፍል 2)

    በሉቃስ 24፥26-27 ባለው ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በርሱ ላይ ሊደርስ ስላለው መከራና ሥቃይ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ ሊሆን ስላለው ክብር ተግባራዊነትና አስፈላጊነት በሙሴ፣ በነቢያትና በመጻሕፍት ሁሉ አስቀድሞ ስለመነገሩ ከትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ተናግሮ ነበር። 

  32. 4

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #4 | የትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንበያና ታሪካዊ ዳራ (ክፍል 1)

    በሉቃስ 24፥26-27 ባለው ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በርሱ ላይ ሊደርስ ስላለው መከራና ሥቃይ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ ሊሆን ስላለው ክብር ተግባራዊነትና አስፈላጊነት በሙሴ፣ በነቢያትና በመጻሕፍት ሁሉ አስቀድሞ ስለመነገሩ ከትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ተናግሮ ነበር። 

  33. 3

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #3 | የክርስቶስ ትንሣኤ ቀዳማዊ አስፈላጊነት

    የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የማይነጣጠሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች፣ እንዲሁም የወንጌል መሠረትና ማእከል ቢሆኑም፣ ትንሣኤው ግን ቁልፍ ክሥተት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ክርስቶስ በሕይወቱና በሞቱ የሠራቸው ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መልኩ የሚታዪቱና በአማኞች ሕይወት ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉት በክርስቶስ የትንሣኤ አካል አማካኝነት ስለሆነ ነው። በመሆኑም፣ ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረትና ማእከል ሲሆን፣ የክርስትና እምነት የመሠረት ድንጋይም ጭምር ነው። 

  34. 2

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #2 | ሞቱ ትንሣኤውን ይቀድማል

    የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የነበረው ሕይወቱና አገልግሎቱ ማብቂያ ያገኘበት ክሥተት ስለመሆኑ ከወንጌላት ዘገባ መረዳት እንችላለን። በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ የዚህ እውነት ታሪካዊ ዳራውና ቀጥተኛ ዐውዱ የሰው ልጆች ሁሉ ሞት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት የሰውን ልጆች ክፋትና ዐመፀ ጥግ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ሲታይ ደግሞ የክርስቶስ መስቀል የሚያሳየው በሰዎች ኀጢአትና ዐመፅ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍትሓዊ ፍርድ ነው።  

  35. 1

    የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #1 | የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የእግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው

    የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ታሪክ በከፍተኛ ደረጃ የተገለጠ ተኣምራዊ ክሥተት ሲሆን፣ አስፈላጊነቱና ጥቅሙም እጅግ ከፍ ያለ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በአንድ አገር ወይም አህጉር ብቻ በተወሰነ መልኩ ሳይሆን፣ የክርስቶስን ማንነት የሰው ልጆችን ምንነት፣ የፍጥረታትን ሁኔታ እና የሰማይንና የምድርን አፈጣጠር ሁሉ ባጠቃለለ መልኩ ትርጉም ሊሰጥ በሚችልበት መንገድ ነበር። በዚህ ፖድካስት እንደምንመለከትው ክርስቶስ ራሱና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች የክርስቶስ ትንሣኤ፣ ክርስቶስ የራሱን መለኮታዊ እና ሰብአዊ ማንነቱንና ያሳካቸውን ተግባራት በሙሉ በትንሣኤው ኀይሉ እንዳረጋገጠ እንገነዘባለን። 

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/

HOSTED BY

ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን

CATEGORIES

URL copied to clipboard!