Skip to content
ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ podcast artwork

PODCAST · business

ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ

by VOA

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

Publisher-supplied feed metadata · PodParley refreshed Feb 8, 2023 · Source feed

Episodes

  1. ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ)አባል ሆና መቀጠል ይኖርባታልን? - ኦክቶበር 28, 2021

    በጎረጎሳዊያኑ 2000 ዓመተምህረት የተፈረመው የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ) ዩናትይድ ስቴትስ እና አፍሪካዊያን ሀገራትን በንግድ ዘርፍ ያጣመረ ሰነድ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጦርነት እና ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ደጋግሞ ስሟ የተነሳው ኢትዮጵያ ከዚህ የተጠቃሚነት ሰነድ ልትሰረዝ እንደምትችል ስጋት አይሏል። ሀብታሙ ስዩም ይሄ እንዳይሆን ዘመቻ ከጀመሩ ፣ በአንጻሩ ደግሞ እርምጃው እንዲወሰድ የሚፈልጉ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያንን ሀሳብ በመቀጠል ያሰማናል ።

  2. የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት በአዲስ አበባ - ኦገስት 31, 2021

    የዋጋ እጅግ እያሻቀበ መምጣትና የኑሮው መወደድ የየዕለት ፈተና እየሆነባቸው መሆኑን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የአዲስ አበባ ተናግረዋል። በሀገሪቱ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት መንስዔዎች የኮቭድ 19 ወረርሽኝና ሀገሪቱ የገባችበት ጦርነት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የምጣኔ ኃብት ባለሙያ ዶክተር ብርሃኑ ደኑ ገልፀዋል። ቀውሱን ለመቆጣጠር መንግሥት የተለያዩ ምጣኔ ኃብታዊ የእርምት እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

  3. የምግብ ዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ያሰጋል - ጁላይ 09, 2021

    ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የምግብ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት መንግስት መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ማድረጉ በህብረተስቡ ዘንድ የሚታየውን የኑሮ ውድነት እንዳላቃለለ፣ የምግብ ዋጋም ከበፊቱ ይበልጥ እየጨመረ እንደሄደ ሸማቾች ይናገራሉ። ፍራንኮ ቫሉታ ብቻውን የዋጋ ንረቱን አያስተካክልም የሚሉት የምጣኔ ሀብት ተንታኞችም በኢኮኖሚውና በፓለቲካው ዙሪያ አስቸኳይ ማሻሻያዎች ካልተደረጉ ግሽበቱ መመለስ ወደማይቻልበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

  4. ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በቦሳሶ - ጁን 19, 2021

    በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በፑንትላንድ ሶማሌ ቦሳሶ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም IOM በኩል ለመመለስ መወሰናቸውን ተሰምቷል፡፡የአሜሪካ ድምጽ እነዚህን ወጣቶችና በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም IOM ውስጥ የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ብሔራዊ መርሃግብር አባል የሆኑትን እከዳር ጤናዬን አነጋግሯል፡፡

  5. ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021

    ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡

  6. ከቀርክሃ እንጨት ካልሲ እና ምንጣፎች የምታመርተው ወጣት ይዲዲያ ዳምጠው - ኤፕሪል 01, 2021

    ይዲዲያ ዳምጠው ወጣት ስራ ፈጣሪ ስትሆን አክሊል የተሰኘ ተቋም መስራች ናት፡፡ ከተመሰረተ ሁለት ዓመት እድሜ ያለው አክሊል በዋናነት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት የሚጥር ተቋም ሲሆን ከቀርክሃ እንጨት ክር በማምረት የመጀመሪያ ምርቱ የሆነው ሳባ ካልሲ በማምረት ስራውን ጀምሯል፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም ልዩ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ንድፍ የያዙ ምንጣፎች እና ብርድልብሶችን ከቀርክሃ እያመረተ ይገኛል፡፡

  7. ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021

    የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

  8. ታዳጊ እናቶች እና ልጆቻቸውን ከጎዳና ላይ አንስቶ እራሳቸውን እንዲችሉ የሚረዳው መሰረት በጎ አድራጎት - ማርች 25, 2021

    ገና በለጋ እድሜዋ የቤተሰቧን ሕይወት ለማሻሻል ስትል ወደ ትዳር የገባቸው ወ/ሮ መሰረት አዛገ በልጅነቷ የልጅ እናት ብትሆንም ኑሮን ታግላ እራሷን አብቅታለች፡፡ ነገር ግን በለጋ እድሜ የልጅ እናት መሆን የሚያመጣውን ችግር ለመቅረፍ በጎዳና ላይ የወደቁ እናቶችን በመሰብሰብ እና መጠለያ በመስጠት የተሃድሶ መርሃግብር እንዲያገኙና በኋላም ቤት ተከራይተው እራሳቸውን ችለው እንዲወጡ ለመርዳት በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት በኩል እየጣረች ነው፡፡

  9. ጥቅሙ ሲያበቃ አትክልት ሆኖ የሚበቅለው ቦርሳ መስራች - ማርች 25, 2021

    ረድኤት ታደሰ ተጠቅመው ሲጨርሱት ለም መሬት ላይ አትክልት ሆኖ መብቀል የሚችል የወረቀት ቦርሳ ለገበያ አብቅታለች፡፡ አሁን ላይ 'ፕላንተብል ባግስ' ስትል የሰየመችው የሚበቅል ቦርሳ በትንሽ መጠን ብቻ እየተመረተ ሲሆን ስራውን ለማስፋትም በብሉሙን የስራ ፈጣሪዎች ውድድር ላይ ገብታ ለመጨረሻው ዙር ካለፉት መሃከል ሆናለች፡፡

  10. "ወጣቶች ዩኒቨርስቲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ስራ ማሰብ መጀመር አለባቸው" አቶ ኤፍሬም በቀለ - ማርች 11, 2021

    ከከፍተኛ የትምህርት እና የሙያ ተቋማት እየተመረቁ የሚወጡ እጅግ ብዙ ወጣቶች በስራ ገበያው ላይ ተመጣጣኝ ስራ ሲያገኙ አይታይም፡፡ በዚም ምክንያት የተማሩ ወጣቶች በስራ ፍለጋ ከወራት እስከ ዓመት ሲጉላሉ ይስተዋላል፡፡ በአንጻሩ ቀጣሪዎችም ተወዳዳሪ የሆኑ ወጣቶች በበቂ ሁኔታ ገበያው ላይ እንደሌሉ ሲያነሱ ይሰማል፡፡ የስነልቦና ባለሞያ እና የስራ ቅጥር አማካሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም በቀለ ወጣቶች ስለ ስራ ማቀድ ያለባቸው ሲመረቁ ሳይሆን ገና ትምህርት ሲጀመሩ ነው ይላሉ፡፡

  11. ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021

    በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡

  12. በስራ ቦታ እድገት እና የሴቶችን ፈተና ያካተተው የሕይወቴ ቅኝት - ማርች 08, 2021

    ፍጹም አጥናፈወርቅ ኪዳነማሪያም የጽኑ ሴቶች ማህበር አባል እና የሴቶች መብትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሃሳቧን በግልጽ በመናገር እና ሴቶችን በማስተባበር ትታወቃለች፡:በቅርቡም የሕይወቴ ቅኝት የተሰኘ እና በእውነተኛ የግል የሕይወት ተሞክሮዎቿ እና አጋጣሚዎች ዙሪያ ያተኮረ መጽሃፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡

  13. ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን መሸጥ ይችሉ ይሆን? - ማርች 03, 2021

    ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የተማረ ወጣት ሃይል እየተፈጠረ መሆኑን ተከትሎ ብዙዎች የራሳቸው የስራ ፈጠራ ሃሳብ እያመንጩ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ብዙዎቹ የስራ ፈጠራቸውን ለመሞከርም ሆነ ወደ ተግባር ለማምጣት የመነሻ ወረት እጥረትና በንግድ ክህሎት ማነስ ምክንያት ህልማቸውን ማሳካት ሲያቅታቸው ይታያል፡፡ ይህን በተመለከተ የአይስ አዲስ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማርቆስ ለማን ኤደን ገረመው አነጋግራዋለች፡፡

  14. በኢትዮጵያ የተመረቱ የተፈጥሮ ሽቶዎችን ለገበያ ያበቁት ወጣቶች ጉዞ - ፌብሩወሪ 23, 2021

    በኤዶም በቀለ እና ሰናይት ዳንኤል ሉሲ ፍራግራንስ አትዮጵያዊ የሆነ መዓዛ ያለው የሽቶ ማምረቻ ድርጅትን ስራ ካስጀምሩ ሶስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ ከዩኒቨርስቲ ከተመረቁ አራት ዓመታት ያስቆጠሩት ሁለቱ ጓደኛሞች ከተፈጥሮ ግብዓቶች የተመረቱ ሃይላንደር እና ኢቮልቭ የተሰኙ የወንድ እና የሴት ሽቶዎችን ለገበያ አብቅተዋል፡፡

  15. የኢትዮጵያ ሕክምና መረጃዎች ማዕከላዊ በሆነ መንገድ እንዲሰነዱ የሚያግዘው ወጣት - ፌብሩወሪ 09, 2021

    ኦርቢት ሄልዝ ከ4 ዓመታት በፊት በጳዚዮን ቸርነት የተቋቋመ የቴክኖሎጂ የጤና ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ስርዓት ማዕከላዊ በማድረግ የህሙማን መረጃ ሳይዘነጋና ሳይጠፋ እንዲሰነድ በተጨማሪም የታዘዙ መድሃኒቶች በተገቢው መልኩ እንዲከፋፍሉ በማድረግ ህሙማን በተለያዩ ህክምናዎች የሚያጠፏቸውን ጊዜና ገንዘብ እንዲሁም መጉላላት እንዲቀር እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡

  16. የማይስ ኮንቬንሽን ቢሮ ተስፋዎች እና የጸጥታ ስጋት ያጠላበት የኢትዮጵያ የቱሪዝም - ፌብሩወሪ 09, 2021

    ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ አውደ-ርዕዮች እና ሁነቶች ‘ማይስ ኮንቬንሽን’ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ከፍታለች፡፡ ይሄ ዘርፍም የቱሪዝሙን ዘርፍ ለማነቃቃት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ይሁንና ኮቪድ 19 ላለፈው አንድ ዓመት ለሚሆን ጊዜ በዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጫና ባላገገመበት በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚነሱ የጸጥታ ችግሮች ዘርፉ በቶሎ እንዳይንሰራራ ስጋት መጣላቸውን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለድርሻ አካላት አስታውቀዋል፡፡

  17. የኢትዮጵያ እዳ፣ ዩሮ ቦንድ እና ቡድን 20 - ፌብሩወሪ 03, 2021

    ኢትዮጵያ እኤአ በ2014፣ እንደ ፋይናንስ ምንጭና መበደሪያ ይሆናት ዘንድ የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሸጣለች፡፡ ለሽያጩም በየዓመቱ ከ62 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወለድ ትክፍልበታለች፡፡

  18. "ሴት የህክምና ባለሞያዎች ለስራቦታ ጾታዊ ጥቃት ተጋላጮች ናቸው" ዶ/ር ሰናይት በየነ - ጃንዩወሪ 29, 2021

    የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማህበር ከተመሰረተ 3 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ሴት የህክምና ባለሞያዎች በስራ ገበታቸው ላይ የሚደርስባቸውን መገለል፣ የጾታ ጥቃት ለማስቀረት በተጨማሪም ባለሞያ ሴቶችን በአመራር ለማብቃት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ ሴት የህክምና ባለሞያዎች በህክምናው ዘርፍ ውስጥ ስላላቸው ሚና እና እንዲሁም ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማኅበር ፕሬዘዳንት እና በጤና ሚኒስቴር አማካሪ ዶ/ር ሰናይት በየነ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

  19. "ቤት ለቤት አስቤዛ ማድረሻውን መተግበሪያ የሰራሁት ከራሴ ችግር ተነስቼ ነው" በረከት ታደሰ - ጃንዩወሪ 14, 2021

    በረከት ታደሰ የቴክኖሎጂ ባለሞያ ሲሆን አስቤዛ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ ፈጣሪም ነው፡፡ አስቤዛ ዶት ኮም ሰዎች የሚፈልጓቸውን እቃዎች ለአማራጭ ከቀረቡ ሱፐር ማርኬቶች መተግበሪያውን በመጠቀም እሚያዙበት እና እቤታቸው ድረስ እንዲመጣላቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ኤደን ገረመው ከበረከት ታደሰ ጋር የነበራትን ቆይታ እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡

  20. እቁብን ከብዙ ሰዎች ጋር በእጅ ስልክ አማካኝነት መጣል የሚያስችለው መተግበሪያ - ጃንዩወሪ 06, 2021

    ዮሃና ኤርሚያስ የ25 ዓመት ወጣት እና የቴክኖሎጂ ባለሞያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በባህላዊ መንገድ ሰዎች ገንዘብ የሚቆጥቡበት እና እቁብን በቀላሉ ለመሰብሰብ እና እና ለመክፈል የሚያግዝ መተገበሪያ ይፋ ለማድረግ ከከአጋሯ ጋር በሙከራ ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡

  21. "ሴቶች በመንግስት የልማት ተቋማት ቦርድ ውስጥ ሃምሳ በመቶ መቀመጫ እንዲያገኙ እየሰራን ነው፡፡" ናሁሰናይ ግርማ - ዲሴምበር 29, 2020

    የኢትዮጵያ ጽኑ ሴቶች ማኅበር (ኤውብ) ከ10 ዓመት በፊት በናሁሰናይ ግርማ እና በሮማን ክፍሌ አማካኝነት በጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ ባለፈው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥም እጅግ ብዙ ሴቶች የቋንቋ፣ የንግድ ክህሎት እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎች የሚያገኙበት፣ ትስስር የሚያደርጉበት፣ በስራቸው የበቁ እና የላቁ ሴቶች እውቅና እና ድጋፍ የሚያገኙበት እንዲሁም በፖሊሲ ደረጃ ተጽእኖ የሚያሳድሩበት ሆኗል፡፡

  22. የሃያ ዓመታት የትግል ጉዞ እና ስኬት- ዋስ ምጣድ - ዲሴምበር 09, 2020

    ዋሴ ሙሉጌታ የዋስ ምጣድ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ነው፡፡ ዋስ ምጣድ በኢትዮጵያ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በስዊድን እና በጀርመን ሃገር የሚሽጥ ሲሆን ከመደበኛው ምጣድ በሶስት እጅ ያነሰ ሃይል እንደሚጠቀምም ዋሴ ይናገራል፡፡ በዓመት ከአንድ ሚሊየን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ያለው የዋስ ምጣድ በአሁን ሰዓት በደብረብርሃን ከተማ የማምረቻ ፍቃድ ወስዶ ፋብሪካ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ኤደን ገረመው ከዋሴ ሙልጌታ ጋር የነበራትን ቆይታ በተከታዩ ዘገባ ታሰማናለች፡፡

  23. ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ - ዲሴምበር 05, 2020

    በካሊፎርኒያ ሶኖማ ግዛት የሚኖረው አየለ ሰለሞን የጠጅ ባህል በማጥናት የጠጅ ጣዕም እና ሽታ ያለው የማር ወይን መጥመቅ ችሏል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታትም ቢ ዲቫይን የተሰኘውን የማር ጠጅ በመሸጥ እና በዓለም ዙሪያ በማስተዋወቅ ላይ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ 19 ወረሽኝ ከፍተኛ ወደሆነ ኪሳራ እና የገበያ መቀስዛቀዝ ያደረሰበት ሲሆን ይህን ችግሩን ለመቅረፍም በአሜሪካ ግዙፉ በሆነው የንግድ ውድድር ሻርክ ታንክ ውስጥ በምሳተፍ 750,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡

  24. በአንድ የስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ብቻ 158 የሚሆኑ ከወላጆቻቸው ጋር የተጠፋፉ ሕጻናት አሉ - ዲሴምበር 03, 2020

    አንድ መቶ ሃምሳ ስምንት የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ከወላጅ እና ከቅርብ ዘምዶቻቸው ተንጥለው በሱዳን ኡም ራክባ የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ ለጥቃት እና ጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ በሆነ ሁኔታ ወስጥ መኖራቸውን ሴፍ ዘ ችልድረን አስታወቀ፡፡ ኤደን ገረመው በሱዳን የሴቭ ዘ ችልድረን ዳይሬክተር አርሻድ ማሊክን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

  25. ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ታሳቢ በማድረግ ለግቢ ጥበቃዎች በፌደራል ፖሊስ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ - ኦክቶበር 28, 2020

    ለፈው ግማሽ ዓመት ተፈጥረው የነበሩ የተማሪዎች ግጭት እና የትምህርት መስተጓጎል ተሞክሮ በመነሳት እና መጪው የምርጫ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለግቢ ጥበቃ አባላት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚነሱ የብሄር እና የፖለቲካ ግጭቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና በሃገር አቀፍ ደረጃ መስጠት ጀምሯል፡፡

  26. ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ ያላቸው ምላሽ ምን እንደሚመስል እና አመጋገባቸው አግዟቸው እንደሆን የሚያጠና ጥናት ይፋ ሆነ - ኦክቶበር 24, 2020

    የጤና ሚኒስተር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የምርምር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡ ኮቪድ 19 ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራቶች አንጻር በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ያለው ጉዳት እንዴት ሊቀንስ ቻለ? ባህላዊ ሕክምና? የዓየር ንብረት? አመጋገብ ወይስ ሌላ የሚለውን ጥናቱ እንደሚያካትት እና ከ6 ሺ በላይ ሰዎች ላይ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገረዋል፡፡

  27. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ አወጣ - ክፍል ሁለት - ኦክቶበር 13, 2020

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ባወጣው መመሪያ ለግለሰብ በቀን ማውጣት የሚፈቀደው ከፍተኛው የጥሬ ገንዘብ መጠን ወደ 50,000 ብር ዝቅ እንዲል ወስኗል። ለድርጅቶች የሚፈቀደው ደግሞ በቀን 75, 000 ብር ብቻ መሆኑ በመመሪያው ተመልክቷል።

  28. "የሕዋ ሳይንስ ትምህርት እና ኢንደስትሪው ትይዩ መገንባት አለባቸው" ትንሳኤ አለማየሁ - ኦክቶበር 11, 2020

    ትንሳኤ አለማየሁ የአራተኛ ዓመት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የመካኒካል ምህንድስና ተማሪ፤ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ማኅብረሰብ ምክትል ሊቀመንበር እና በተባበሩት መንግስታት የስፔስ ጄኔሬሽን አማካሪ ቢሮ የኢትዮጵያ ተጠሪ ነው፡፡ ከሰሞኑም ሃገሩን ወክሎ የአፍሪካ ወጣቶች በህዋስ ሳይንሱ በሰፊው እንዲሳተፉ ምን መደረግ እንዳለበት ረቂቅ ጽሁፍ የህዋ ጠበብት በሚያዘጋጀው ስብሰባ ላይ ሊያካፍል ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡

  29. ፈለክ የፊት ማስክ የብቃት ማረጋገጫ አገኘ - ሴፕቴምበር 26, 2020

    ፈለክ ኖትቡክ ባለፉት አራት ዓመታት ከማተሚያ ቤቶች የሚጣሉ ወረቀቶችን መልሶ በጥቅም ላይ በማዋል ስራ ላይ ያተኮረ ተቋም ነው፡፡ ኖት ቡኮቹ ተወዳጅ ቢሆኑም ኮቪድ 19 እንደማንኛው የስራ ዘርፍ የራሱን ጫና አሳርፎበታል፡፡ ይህንን ጫና ለመቋቋም እና ለኮቪድ 19 መከላከል ላይ የራሳቸውን አስተዋጻኦ ለማበርከት ማምረት የጀመሩት የፊት ማስክ የብቃት ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡ ኤደን ገረመው የድርጅቱን መስራች አቶ ሱሌማን ዳዊትን አነጋራለች፡፡

  30. "ወደ ውድድሮች የገባሁት ለስራ ማስኬጃ ገንዘብ ስላስፈለገኝ ነው" የፈጠራ ባለሞያ ቃለዳዊት - ሴፕቴምበር 05, 2020

    ቃለዳዊት እስመለዓለም በባህርዳር ከተማ የሚኖር ወጣት የኮምፒውተር ሳይንስ መምህር እና የፈጠራ ባለሞያ ነው፡፡ ከቃለዳዊት ፈጠራ ስራዎች መሃከል በዋናነት የሚነሱት የዶሮ እንቁላል ማስፈልፈያ ኢንኩቤተር፤ የትራፊክ መብራት እና ሙሉ ለሙሉ በሃገር ውስጥ የተመረተ የጸሃይ ሃይል መሰብስቢያ ሶላር ናቸው፡፡ ቃለዳዊት በተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ በውድድሮቹ ላይ የሚሳተፈውም ያለበትን የበጀት እጥረት ለሟሟላት እንደሆነ ይናገራል፡፡

  31. ኢትዮጵያዊቷ እድሜያቸው ከ30 በታች ሆነው በአፍሪካ ሕዋ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ያሉ ምርጥ 10 ዝርዝር ውስጥ ገባች - ሴፕቴምበር 03, 2020

    ሊዲያ ረዘነ በቱርክ እና በቻይና የሕዋ ምሕንድስና እንዲሁም በማላዊ የቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ የሰው አልባ በራሪ ድሮን መግጠም ስልጠና ለ 3 ወራት ወስዳለች:: በቅርቡም የአፍሪካን የሕዋ ሳይንስ መረጃ መተንተኛ ድረ ገጽ እድሜያቸው ከ 30 ዓመት በታች የሆኑ እና በአፍሪካ ሕዋ ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ካሉ ምርጥ አስሮች ውስጥ አካቷታል፡፡ ኤደን ገረመው ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

  32. ኢትዮጵያ በመጪው ጥቅምት ሁለተኛ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው፡፡ - ኦገስት 25, 2020

    ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከቻይና ጋር በመተባበር ሁለተኛ ሳተላይት ወደ ህዋ ለማመንጠቅ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቲክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ኤደን ገረመው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ አነጋገራ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች፡፡

  33. "ሁሉም በተሰኘው ዘመቻ በሁለት ሳምንት ከ200,000 ሰው በላይ መመርመር ተችሏል" ዶ/ር ኤባ አባተ - ኦገስት 25, 2020

    የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ሳይንስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ከ17 ሚሊየን ቤቶችን ለመድረስ እና ከ 200,000 በላይ ሰዎችን ለመምርመር ታቅዶ የነበረው ዘመቻ ግቡን መምታቱን እና እስከ ነሃሴ ማብቂያ ድረስ መቀጠሉንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ክልሎች እና እንዲሁም በእስር ቤቶች ስላለው የቫይረሱ ስርጭት እና ከለይቶ ማቆያ ጋር ተያይዘው ስለሚነሱ ቅሬታዎች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል፡፡

  34. የኢትዮጵያ የማዕድን እና የነዳጅ ሀብት እምቅ አቅም - ኦገስት 24, 2020

    የኢትዮጵያ የማዕድን እና የነዳጅ ሀብት እምቅ አቅም በተነገረበት መድረክ ላይ የሃገሪቱ የማዕድን እና ነዳጅ ዘርፍ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

  35. በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከምዝገባ እስከ ምረቃ ድረስ በድረገጽ ትምህርት መስጠት የሚያስችላቸው አሰራር ይፋ ሆነ፡፡ - ኦገስት 05, 2020

    በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሙሉ ጊዜ የድረገጽ (ኦን ላይን) ትምህርት ማካሄድ እንዲችሉ የሚፈቅድ መመሪያ በከፍተኛ የትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ እና በሳይንስ እና በከፈተኛ ትምህርት ሚኒስተር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ ኤደን ገረመው በከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ዲባይን ያደረገችው ቆይታ እንደሚከተለው ይሰማል፡፡

  36. ኢትዮጵያዊው የሃርማን ጄምነርን ሽልማት አሸነፈ - ኦገስት 01, 2020

    በኤስ ኦ ኤስ ማሳደጊያ ውስጥ ያደገው ኢትዮጵያዊው ገብረእግዚአብሄር ገብረ በዛሬው ዕለት የሃርማን ጄምነር ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡ገብረእግዚአብሄር ለውድድር የቀረበው በልኡል ግርማይ መታሰቢያ ድርጅት በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ለሚያደርገው የትምህርት ድጋፍ ነው፡፡ ኤደን ገረመው ገ/እግዚአብሔርን እና የኤስ ኦ ኤስ እናቱን ወ/ሮ መድህን መሃሪን አነጋግራለች፡፡

  37. በአሁኑ ሰዓት ከ10 ሺ በላይ ሰዎች የእኛን ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ - ያሬድ ሹመቴ - ጁላይ 25, 2020

    ባለፉት ሳምንታት በነብሩ ሁከቶች ሳቢያ ብዙዎች ከመኖሪያ ቤት ተፈናቅለው ንብረታቸውንም በማጣት አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍን ይሻሉ፡፡ ጥምረት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሃገር ፍቅር ትያትር ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት የቁሳቁስ ድጋፎችን ለማሰባሰብ ጥሪ አድርጓል፡፡

  38. በመጪው ነሃሴ ከኬኒያ ወደኢትዮጵያ በሚገባው አንበጣ ምክንያት እስከ 1 ሚሊየን ሰው ሊራብ ይችላል- ፋኦ - ጁላይ 25, 2020

    የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ)ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት፤ ደግሞ በቀጣዩ ነሃሴ ከኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ የበርሃ አንበጣ በቶሎ በቁጥጥር ስር ካልዋለ ከ1 ሚሊየን በላይ የሚሆን ህዝብ ሊራብ እንድሚችል አመላክቷል፡፡

  39. በአዲስ አበባ ከ65,000 በላይ መምህራን የሚሳተፉበት የክረምት ጥናት መርሃግብር ተጀመረ - ጁላይ 25, 2020

    የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በኮቪድ 19 ሳቢያ ትምህርት አቋርጠው የተቀመጡ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለማገዝ 65,000 የሚሆኑ በጎፍቃድኛ መምህራንን አስተባብሮ 'ት/ቤቴ በቤቴ' የሚል የክረምት የጥናት መርሃግብር መጀመሩን አስታውቋል፡፡

  40. በኢትዮጵያ የድንገተኛ አደጋዎች ቅድመ ማስጠንቀቂያ አገልግሎት ሊጀመር ነው - ጁላይ 16, 2020

    የኢትዮጵያ የሰላም በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለኅብረተሰቡ ለማሳወቅ የሚያስችል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ዝርጋታ እየጨረስኩ ነው ሲል አስታውቋል፡፡ ማስጠንቀቂያ ሲኖር በስልክ እንድሚላክ ተገልጿል፡፡

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

HOSTED BY

VOA

Produced by የአሜሪካ ድምፅ

CATEGORIES

Frequently Asked Questions

How many episodes does ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ have?

ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ currently has 50 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ about?

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

How often does ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ release new episodes?

ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ has 50 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ?

You can listen to ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ?

ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ is created and hosted by VOA.
URL copied to clipboard!