Skip to content
ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ podcast artwork

PODCAST · news

ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ

by VOA

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

Publisher-supplied feed metadata · PodParley refreshed Sep 3, 2022 · Source feed

Episodes

  1. የሴት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሃገር አቀፍ የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ - ሴፕቴምበር 04, 2021

    ሴቶች በፖለቲካና በአመራር በብቃት እና በስፋት እንዲሳተፉ ያግዛል የተባለ የሴት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሃገር አቀፍ የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ። ነፃ እንደሆነ የተነገረው ይህ ምክርቤት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊዎቻቸው በሴቶቹ የፖለቲካ ቀጥተኛ ተሳፎ ላይ እንዲተባበሩ የማድረግ ዓላም እንዳለው ታውቋል። መለስካቸው አመሐ ዝርዝር አለው።

  2. ክፍያ ያልተጠናቀቀላቸው ምርጫ አስፈፃሚዎች ቅሬታ አሰሙ - ኦገስት 11, 2021

    በኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ላይ የሠሩ አንዳንድ የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ቦርዱ ሙሉ ክፍያ አልፈፀመልንም ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል። የቦርዱ የኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት ክፍያው ሙሉ በሙሉ ያልተፈፀመው “የንብረት ርክክብ ባለመጠናቀቁና በጀት በመዘጋቱ ነው" ብሏል።

  3. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ያሸነፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አስተያየት - ጁላይ 20, 2021

    ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተካሄደው ሃገር አቀፍ ምርጫ ከአማራ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ያሸነፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም የዴሞክራሲ ባህልን ለመገንባት ጅማሮው ጥሩ ነው ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ግምገማቸውን ገለፁ።

  4. ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፉ ተገለፀ - ጁላይ 11, 2021

    ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ዛሬ፤ ሐምሌ 3/2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት ከ436 የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች፣ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ 410ሩን አሸንፏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድምሩ 13 መቀመጫዎችን ማሸነፋቸው የተገለፀ ሲሆን በሦስት የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ቆጠራ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

  5. በጉጂ በ30 የምርጫ ጣብያዎች ተቋርጦ የነበረዉ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል - ጁላይ 09, 2021

    በአንድ የግል ተወዳዳሪ አቤቱታ ምክንያት ምርጫ ቦርድ ያቋረጠዉ የነጌሌ ምርጫ ዛሬ ተከናውኗአል። አቶ አማኑኤል ብርሃኑ የነገሌ የምርጫ ክልል አስተባባሪ የምርጫው ሂደት በ30 የምርጫ ጣብያዎች መከናወኑን ለአሜርካ ድምጽ ገልጸዋል። በምርጫዉ ከ150 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል ብለዋል፣ ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ አለዉ።

  6. ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የምርጫ ወቅት የሴቶች ጥቃት ምልከታና ውጤቱ - ጁን 24, 2021

    የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር (ኢውላ) በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ትንኮሳዎችን እና ጥቃቶችን ሲታዘብ ቆይቷል፡፡ በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱ ቅድመ ምልከታው ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

  7. 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የኢትዮጵያ ስርዓት የሚፈተሽበት ነው - ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ - ጁን 23, 2021

    ኢትዮጵያ ውስጥ ለ6ኛው አጠቃላይ ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚደረገው ዝግጅት ተጠናቆ ነዋሪዎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ባልደረባችን ስመኝኝ የቆየም በግሪንስቦሮ የሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ጋር ደውላ “ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያውያን ምን ትርጉም ይኖረዋል?” ስትል ጠይቃለች።

  8. የመጀመሪያው እንደሆነ ስለተነገረለት አካል ጉዳተኞች ላይ ያነጣጠረ የፖለቲካ ክርክር - ጁን 07, 2021

    ከጥቂት ሳምንታት በኃላ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የአካል ጉዳተኛ ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ እንደምን አድርገው እንደሚያስተናግዱ የሚመረምር ክርክር ከሰሞኑ ተደርጓል። ክርክሩን የመሩት በአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ ዳኛቸው ቦጋለ ናቸው። ከአቶ ዳኛቸው ጋር ዘለግ ያለ ቆይታ ያደረገው ሀብታሙ ስዩም ሲሆን ክርክሩ እንዴት እንደተዘጋጀ እና ፋይዳው ምን እንደሆነ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።ተያያዥ ሀሳቦች የተነሱበት ቃለ ምልልስ በመቀጠል ይደመጣል።

  9. የእናት ፓርቲ የምርጫ ዝግጅት - ሜይ 28, 2021

    በስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው እናት ፓርቲ በምርጫው ካሸነፈ ኢትዮጵያን “ከተጋረጠባት የህልውና አደጋ ለመታደግ እሠራለሁ” ብሏል። ፓርቲው የጥምር መንግሥት ምሥረታን እንደሚደግፍ አስታውቋል።

  10. የሃገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ፓርቲዎች ለሴቶች ምን ይዘዋል? ጠይቂ ዘመቻ - ሜይ 17, 2021

    በመጪው ሃገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ ፓርቲዎችን በመሰረታዊ የኢኮኖሚ፣ የጤና፣ የትምህርት ፖሊሲያቸው ውስጥ ለሴቶች ምን ይዘዋል የሚለውን ሴቶች እንዲጠይቁ የሚያበረታታ ጠይቂ የተሰኘ ዘመቻ በሴታዊት ንቅናቄ ተጀምሯል፡፡ በሴታዊት ንቅናቄ ውስጥ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ መርሃግብር ስራአስኪያጅ አበባዬ አስራት ጋር ቆይታ ያደረገችዋ ኤደን ገረመው ናት፡፡ አበባዬ ተቋማቸው ሴታዊት ንቅናቄ በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ስላለው ተሳትፎ ከምታስረዳበት ውይይታቸው ይጀምራል፡፡

  11. በሴት ምርጫ ተሳታፊዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መጠቆሚያ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ - ሜይ 17, 2021

    የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር ኢውላ ባለፈው ሳምንት ከምርጫ ጋር ተያይዞ በሴት መራጮች፣ አስመራጮች፣ ጋዜጠኞች፣ ታዛቢዎች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃቶችም ሆኑ ትንኮሳዎችን ሴቶች በነጻ በመደወል ምክር ሊያገኙበት ወይም ሊጠቁሙ የሚችሉበት ነጻ የስልክ መስመር ይፋ አድረጓል፡፡

  12. የተቀዛቀዘው የዜጎች የምርጫ ተሳታፊነት እና የሚያስከፍለው ዋጋ- ቆይታ ከበፍቃዱ ሃይሉ ጋር - ሜይ 12, 2021

    ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመካሄድ የሳምንታት እድሜ በቀረበት በአሁኑ ሰዓት ዜጎች የምርጫ ካርድ ለመውሰድ ያላቸው ተነሳሽነት እንደተጠበቀው አለመሆኑን የፖለቲካ ምሁራን እየተናገሩ ነው፡፡ የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ‘ካርድ ኢትዮጵያ’ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በፍቃዱ ሃይሉ ዜጎች ከደህንነት ስጋት፣ በምርጫ አስፈጻሚዎች ለውጥ እና ምርጫው አሸናፊው የሚታወቅበት የተበላ ዕቁብ ነው በሚሉ ሃሳቦች ምክንያት ተነሳሽነታቸው ተቀዛቅዟል ይላሉ፡፡

  13. ክፍል ሦስት - "ለምን ይመርጣሉ?" - ኤፕሪል 28, 2021

    የህዝብ አስተያየትና የባለሞያ ትንታኔ

  14. ክፍል ሁለት - "ለምን ይመርጣሉ?" - ኤፕሪል 27, 2021

    የህዝብ አስተያየትና የባለሞያ ትንታኔ

  15. በሀረሪ ምርጫ ጉዳይ ፍ/ቤት ወሰነ - ኤፕሪል 27, 2021

    ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከሀረሪ ክልል ውጪ የሚኖሩ የሀረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች በሀረሪ ክልል ምርጫ መሳተፋቸው ህጋዊ መሰረት የለውም ሲል ያስተላለፈውን ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድቤት የምርጫ ሂደትና ውጤትን የሚያየው ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውድቅ እንዳደረገው የሀረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አስታወቀ። የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስተት ተቆጥቧል።

  16. "ለምን ይመርጣሉ?" - ኤፕሪል 26, 2021

    የህዝብ አስተያየትና የባለሞያ ትንታኔ

  17. የድሬዳዋ ፓርቲዎች በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ - ኤፕሪል 19, 2021

    በድሬዳዋ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች ተቋቁመዋል። ምክር ቤቶቹ ከምርጫ ቅስቀሳ እስከ ድህረ ምርጫ ያሉ ሂደቶች ሰላማዊ ሆነው እንዲከናወኑ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በጋራ የሚመክሩባቸው ይሆናሉ ተብሏል።

  18. ምርጫዬ፦ የምርጫ ቅስቀሳ እና መረጃ አገልግሎት የሚሰጠው መተግበሪያ - ኤፕሪል 19, 2021

    ኢትዮጵያ ለስድስተኛ ጊዜ ሀገራዊ ምርጫ ለማከናወን እየተሰናዳች ትገኛለች ። የዘንድሮ የምርጫ ሂደት በዘመነኛ የምርጫ ቅስቀሳ እና የምርጫ መረጃዎች ስርጭት ይታገዝ ዘንድ የወጠነ ሀገር በቀል ተቋም አዲስ የስልክ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።

  19. የመራጮች ምዝገባ ተግዳሮት እንደገጠመው ተገለጸ - ኤፕሪል 15, 2021

    የመራጮች ምዝገባ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደገጠመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የሰላም እጦትና የመጓጓዣ ችግሮች ተጠቃሾች እንደሆኑም ተነገረ። የተቃዋሚዎች ፓርቲዎች ዕጩዎች በሚደርሰው ተፅዕኖ ለዕጩዎች ምዝገባ መቀዛቀዝ እንደምክንያት ተጠቅሷል። ለዕጩዎቹ መታሰር የገዥው ፓርቲ ተወካይ ይቅርታ ጠይቀዋል።

  20. የሐረሪ ጉባዔ ከምርጫ ቦርድ ጋር የያዘው ውዝግብ - ኤፕሪል 13, 2021

    ከሐረሪ ክልል ውጪ የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆች በሐረሪ ክልል ምርጫ እንዲሳተፉ ከክልሉ መንግሥትና ከሐረሪ ብልጽግና የቀረበለትን ጥያቄ እንደማይቀበል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ የሐረሪ ጉባዔ አልቀበልም አለ። የምርጫ ቦርድ ግን ውሳኔው ህገመንግሥቱ ላይ ተመስርቼ የወሰንኩት ነው ብሏል።

  21. በዘንድሮ ምርጫ የሲቪክ ማህበራትና ድርጅቶች ሚና - ኤፕሪል 13, 2021

    መጭው ሃገራዊ ምርጫ አሳታፊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን መንግሥታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለስቪክ ማህበራት ድጋፍ እንዲያደርጉ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል። በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት በባሕር ዳር ከተማ ከተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለምርጫና ስለሰብዓዊ መብቶች የግንዛቤ መስጫ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል።

  22. የመራጮች ምዝገባ መጓተትና የምርጫ ቦርድ ምላሽ - ኤፕሪል 09, 2021

    የስድስተኛው ብሄራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች እስካሁን ያልተጀመረው በትራንስፖርት እጥረት ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በትናንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም በየምርጫ ጣቢያዎቹ የመመዝገቢያ ስፍራ ቢዘጋጅም ምዝገባው ባለመጀመሩ ግን ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።

  23. የሶማሌ ፓርቲዎች ለምርጫ ዝግጁ ናቸው - ኤፕሪል 02, 2021

    በሶማሌ ክልል ለምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስፈላጊውን የምርጫ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አታወቁ። ከእጩ ምዝገባ ጋር በተያያዘ ምርጫ ቦርድ ላይ ሲያቀርቡት የነበሩ ቅሬታዎችም አብዛኞቹ መቀረፋቸውን አስታውቀዋል።

  24. በምርጫ ጉዳይ የተካሄደ ውይይት - ማርች 31, 2021

    የ2013 ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ደህንነቱ የተጠበቀ እንደዚሁም ታዓማኒ እንዲሆን የሚያግዝና ከልዩ ልዩ የመንግሥት አካላት የተወጣጣ ሀገር አቀፍ የምርጫ ኮሚቴ መቋቋሙን የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ። ኮሚቴው ዕለታዊ መረጃ ልውውጥ በማድረግ የሚናበብ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ወደ ሥራ መገባቱንም አመልክተዋል።

  25. በመራጭነት እና በተመራጭነት የሚሳተፉ ሴቶች ሚና - ማርች 31, 2021

    በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በመራጭነት እና በተመራጭነት የሚሳተፉ ሴቶች ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ታአማኒ እና ሰላማዊ እንዲሆን ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። በምርጫው የሚሳተፉ የተለያዩ ፓርቲዎች ሴት ዕጩ ተመራጮች በምርጫው በተመራጭነት የመሳተፍ እድል ማግኘታቸውን ገልጠው ማናቸውን እንዲሚወጡ ተናግረዋል።

  26. እነአቶ አራርሶ ቢቂላ ፍ/ቤት ሊሄዱ ነው - ማርች 31, 2021

    በአቶ አራርሶ የሚመራው ኦነግ ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ ውድቅ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መወሰኑን በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ ተቃውሞታል። ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስድ አስታውቋል።

  27. የፀጥታ ሥጋት እና የምርጫ ዝግጅት በምዕራብ ኦሮምያ - ማርች 30, 2021

    ከምርጫው በፊት በምዕራብ ኦሮምያ አንዳንድ ቦታዎች የሚታየው የፀጥታ ስጋት መወገድ እንዳለበት ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አሳስበዋል። የምርጫ ዓመት ድባብ ያልታየባቸው አካባቢዎችም እንዳሉ አስተያየት ሰጭዎቹ አመልክተው መንግሥት ህዝቡን እንዲያወያይ ጠይቀዋል። ፌዴራል ፖሊስ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ምርጫው ከትግራይ በስተቀር በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድና በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ እንደሚሠራ አስታውቋል።

  28. የምርጫ ካርታ ውዝግብ - ሶማሌ እና አፋር - ማርች 25, 2021

    ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የአፋር ክልል ቅሬታ ባቀረበባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምርጫ እንዳይካሄድ መወሰኑን እንደሚቃወም የሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ መንግሥት አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ ከምርጫው ራሱን እስከማግለል የደረሰ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችልም አስታውቋል። ከብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

  29. ከእጩዎች ጋር በተያያዘ ለቀረቡ አቤቱታዎች መፍትሔ እንደሰጠ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ - ማርች 18, 2021

    ከእጩዎች ጋር በተያያዘ ከተፎካካሪዎች ለቀረቡ 50 ያህል አቤቱታዎች መፍትሔ እንደሰጠ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ። ተፎካካሪ ፓርቲዎች ግን አሁንም መፍትሔ የሚሹ ስህተቶች አሉ ይላሉ። ቦርዱ ብሔራዊ በሚባሉ ጉዳዮች ክርክር ለማዘጋጀት መብትም ሆነ ሕጋዊ ግዴታ እንዳለበትም አስታወቀ።

  30. ኢዜማ በባሕር ዳር - ማርች 15, 2021

    የ2013 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት በመሆኑ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ኢዜማ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጥሪውን ያቀረበው በባሕር ዳር ከተማ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ባስጀመረበት ሥነ ስርዓት ነው።

  31. ከምርጫ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎች ለመፍታት የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች ዝግጅት - ማርች 15, 2021

    ከምርጫ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎችንና አለመግባባቶችን በፍጥነት ለመፍታት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ ከምርጫ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎች በክልሉ ከወረዳ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚገኙ 209 ችሎቶች ይታያሉ ነው የተባለው፡፡

  32. በአማራ ክልል የፓርቲዎች ዝግጅት - ማርች 06, 2021

    በኢትዮጵያ በመጭው ለሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ባልተሟላ መንገድም ቢሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን የተለያዩ ፓርቲዎች ገለፁ።

  33. የሲዳማ ክልል የምርጫ ዝግጅት - ማርች 04, 2021

    6ኛውን ክልላዊ እና ሃገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውንና የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጣቸውን የሲዳማ ክልል እንደራሴዎች አስታወቁ። በክልሉ በምርጫው ከሚወዳደሩ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የሲዳማ አንድነት ፓርቲ ከዝግጅት ይልቅ ዳተኝነት አለ ይላል።

  34. ኢዜማ ኮንሶ ላይ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው አለ - ፌብሩወሪ 25, 2021

    በደቡብ ክልል የኮንሶ ዞን የኢዜማ ፓርቲ አባላት የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን፤ ሲያዙም መደብደባቸውና መቁሰላቸውን ለሁለት ቀናት ከታሰሩ በኋላም ትናንት ማምሻውን ከእስር መለቀቃቸውን ኢዜማ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጠ። የኮንሶ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ በኢዜማ ምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት የታሰረ ሰው አለመኖሩን ጠቅሶ “መንግስት ፈርሷል” የሚል አሉባልታ በአደባባይ ሲያውጁ እና ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ የተያዙ ግለሰቦች መኖራቸውን ተናግሯል።

  35. የኦነግ ጠቅላላ ጉባዔ ጉዳይ - ፌብሩወሪ 23, 2021

    በአባላቱ ላይ “እየደረሰ ነው” ባለው እስራት እና የቢሮዎች መዘጋት ለምርጫ ተሳትፎው እንቅፋት እየደቀኑበት እንደሆነ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ገልጿል።

  36. የምርጫ 2013 ዘመቻ - ፌብሩወሪ 17, 2021

    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ለስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ተዋንያን ሁሉ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ። ቦርዱ በህግ የተጣለበትን ግዴታ እና ኃላፊነት እንደሚወጣም ማረጋገጫም ሰጡ። አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻውን ጀምረዋል።

  37. "ሁሉም በተሰኘው ዘመቻ በሁለት ሳምንት ከ200,000 ሰው በላይ መመርመር ተችሏል" ዶ/ር ኤባ አባተ - ኦገስት 25, 2020

    የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ሳይንስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ከ17 ሚሊየን ቤቶችን ለመድረስ እና ከ 200,000 በላይ ሰዎችን ለመምርመር ታቅዶ የነበረው ዘመቻ ግቡን መምታቱን እና እስከ ነሃሴ ማብቂያ ድረስ መቀጠሉንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ክልሎች እና እንዲሁም በእስር ቤቶች ስላለው የቫይረሱ ስርጭት እና ከለይቶ ማቆያ ጋር ተያይዘው ስለሚነሱ ቅሬታዎች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል፡፡

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

HOSTED BY

VOA

Produced by የአሜሪካ ድምፅ

CATEGORIES

Frequently Asked Questions

How many episodes does ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ have?

ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ currently has 50 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ about?

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

How often does ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ release new episodes?

ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ has 50 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ?

You can listen to ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ?

ምርጫ 2013 - የአሜሪካ ድምፅ is created and hosted by VOA.
URL copied to clipboard!