PODCAST · news
የዓለም ዜና
by DW
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
-
100
የመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና
የትግራይ ሰላም ሀይል ከመቀለ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለች ከተማን ተቆጣጠርኩ ማለቱን፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞት፣ መፈናቀልና ሰብአዊ ቀውስማድረሱን፣ግብፅ የኢትዮጵያን ዲፕሎማት ከሀገሯ ማስወጣቷን፣የአፍሪቃ ሕብረት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅ መካከል ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ ማቅረቡን እና ሌሎችን አካቷል።
-
99
የመስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ፍንዳታ መሰማቱን ሮይተርስን ጨምሮ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘገቡ። ኢትዮጵያ አስመራ ያለውን ኤምባሲ ለመዝጋት ወሰነች። በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ስጋቱ የሰብአዊ አቅርቦትን ማስታጎሉን የተmm,ድ ገለጸ። እስራኤል በፍላይ ዱባይ አውሮፕላን ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት ከመሠረቱ እንደምታጣራ ዛተች።
-
98
የመስከረም 20 ቀን 2019 የዓለም ዜና
-የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት የድርድርን መንገድ እንዲመርጡ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተማፀኑ።ዉጊያ እንደቀጠለ ነዉ።-- አዲስ አበባና አካባቢዋ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን እንዳይበር ታገደ።-ኢትዮጵያን ጨምሮ ለምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል የተባለ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ላሙ-ኬንያ ዉስጥ ተጀመረ።
-
97
የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና
ዋሽንግተን፥ ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን ውጥረት ለማርገብ አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ፣ አ.አ፥ በሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ፣ ወሎ፥ በተቀሰቀሰው ጦርነት የተፈናቃዮችን መከራ ማባሱ ተገለጠ፣ ካይሮ፥ የአፍሪቃ አገራት ለንድግ ግብጽ ውስጥ ይሰበሰባሉ፣ ፑንትላንድ፥ አንዲት ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከባሕር ላይ ዘራፊዎች ነጻ ወጣች
-
96
የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተለያዩ ከተሞች የበርክታ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፤የትግራይ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድሮን ተመታ ባሉን፣ ቀይመስቀል 161 ሰዎችን ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች ዛሬ ማስወጣቱን፣በሽብርተኝነት ተከሰው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የነበሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አስጊ ወደተባሉ እስር ቤቶች ተዛወሩ መባሉን አካቷል።
-
95
የመስረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦና አላማጣ አካባቢዎች ከባድ ውግያ ሲካሄዱ እንደዋሉ መረጃዎች አመላከቱ። አላማጣ፣ ጥሙጓና ሰሌን ውሃ በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ታውቋል። በመቐለ ከተማ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
-
94
DW Amharic የመስከረም 16 ቀን 2019 የዓለም ዜና
ሩሲያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ያሳስበናል አሉ። መከላከያ ሠራዊት በትግራይ አምስት ትምህርት ቤቶች እና በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ ላይ በፈጸማቸው ድብደባዎች ሰዎች መገደላቸውን የተመ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። በመቐለ መከላከያ ሠራዊት የፈጸመው ጥቃት እንደ “የጦር ወንጀል ሊመረመር እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።
-
93
የመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. የዶቼቬለ የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና -የኢትዮጵያ ጦርና የትግራይ ኃይሎች ዛሬ በተለያዩ ግንባሮች ከባድ ውጊያ መካሄዳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ -በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መታጎሉን ተጠቃሚዎች አስታወቁ ። -በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ።
-
92
የመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የትግራይ ኃይሎች ከፌድራል መንግሥት ጋር “ሙሉ ጦርነት” መግጠማቸውን ገለፁ። የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት “በአፋጣኝ ማርገብ” እንደሚያስፈልግ አሳሰበ። ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኝ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘጋ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ፑቲንን ለቡድን 20 ጉባኤ ጋበዘቻቸው
-
91
የመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ የፈደራል መንግሥትና ትግራይን የሚገዛዉ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይላት አዲስ ዉጊያ ገጥመዋል።የደቡብ ሱዳን ፕረዝደንት ሳልቫኺር የሐገሪቱን የሽግግር መንግስት አፈረሱ። ኢራን በአሜሪካና እስራኤል ጥቃቶች የወደመውን የነዳጅ ማምረቻ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ 50 በመቶ ማጠናቀቋን አስታወቀች።
-
90
News AMH_am Dienstag den 22.09.2026 - MP3-Stereo
የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። በሃገሪቱ ውጥረቶችን ለመቀነስ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በአፍሪቃ ኅብረት የሚመራውን ጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደገፉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ኒዮርክ ላይ በይፋ ጀመረ።
-
89
የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና -የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከስርጭት መታገዱን አስታወቀ። -የየመን ሁቲዎች ስልታዊ የተባሉ የየመን ከፍተኛ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ ናቸው - የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ ሜክለንቡርግ ፎር ፖመርን ግዛት ፓርላማ መግባት ሳይችል ቀረ
-
88
የመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና የተባለ ጥምረት መመሥረታቸውን አወጁ ። አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ከፈጸመች በመካከለኛ ምስራቅ ውስጥ የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿንና ጥቅሞቿ ላይ ጽኑ ሕመን የሚያስከትል ጥቃት እንደምትፈጽም ኢራን አስጠነቀቀች።
-
87
የመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ከተማ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን የክልሉን የመገናኛ ብዙኃን ጠቀሶ የትግራይ ቴሌቭዥን በፌስ ቡክ ገጹ ዘገበ። • በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ተገደሉ ። ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ። • ሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ ውስጥ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱ ተዘገበ ።
-
86
የመስከረም 8፣ 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
• የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት 300 ያህል የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች አባላት እጃቸውን መስጠታቸውን አስታወቀ። • የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” የተመሠረዉ “ፅምዶ” ተባለ ህብረት ውስጥ ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታወቀ፡፡
-
85
የዓለም ዜና፤ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም
አርስተ ዜና፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ከጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አደረሱት በተባለው ጥቃት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ።-የስምረት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ን እርምጃ አወደሰ። ሜሪካ ለደቡብ አፍሪቃውያን አዲስ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ ማዉጣትዋን አስታወቀች።
-
84
የመስከረም 6 ቀን 2019 የዓለም ዜና
-ሊቢያ ዉስጥ በየእስር ቤቱ የሚገኙ የኤርትራ ሥደተኞች ከፍተኛ ሥቃይ እንደሚደርስባቸዉ አስታወቁ።ሥደተኞቹ እንደሚሉት የየእስር ቤቱ ተቆጣጣሪዎችና ጠባቂዎች።ይደበድቧቸዋል።ሴቶቹን ይደፍሯቸዋል።---የየመን አንሳር አላሕ ተዋጊዎች የሙስሊሞቹን ቅድስት ከተማ መካን ለማጥቃት ሞከራዋል የሚለዉን የሪያድ ገዢዎችን ክስ አስተባበሉ።
-
83
የመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትናንት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአስራ ሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡ • የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመደቡ ተማሪዎችን ማመልከቻዎች መቀበል መጀመሩን አስታወቀ።
-
82
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ታጣቂዎቸ አደረሱት በተባለው ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ፤ 4 ደግሞ ቆሰሉ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥቢያ በሱዳኑ የብሉ ናይል ግዛት በአል-ዳማዚን ከተማ የድሮን ጥቃት ፈፀመ ። የሁቲ አማጽያን ዛሬ የሀኒሽ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ ።
-
81
የመስከረም 03 ቀን 2019 የዓለም ዜና
በየመን በሑቲዎችና የመንግሥት ኃይሎች ውጊያ 86,000 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,000 በላይ ጅቡቲ ገቡ። “በዓለም ዙሪያ የግጭቶችና ውጥረቶች ቁጥር እየጨመረ” በመሔዱ በሕዝቦች ሕይወት ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስጠነቀቁ። ሩሲያ ከዋርሶ ወደ ኪየቭ በተዘረጋ ባቡር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ፖላንድ አስታወቀች።
-
80
የመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች። ለብሪክስ ጉባኤ ሕንድ ኒውደልሂ ከተማ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢራን ፕረዚደንትን ጨምሮ ከተለያዩ ሐገራት መሪዎች መወያየታቸውን ገለፁ።ኢራቅ ከኢራን ጋር የሚያዋሱኗት ሦስት ድንበሮች ዛሬ መዝጋቷን አስታወቀች።
-
79
የመስከረም አንድ ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና
በአሜሪካን በኒውዮርክ፣ በፔንታገንና በፔንሲልቬንያ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት 25 ተኛ ዓመት ዛሬ በአሜሪካን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየታሰበ ነው። ነገ ህንድ ውስጥ በሚጀመረው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራት መሪዎች ኒውዴልሂ እየገቡ ነው። የሁቲ አማጻያን ዛሬ ስልታዊ የሚባለውን ፔሪም ደሴትንና የዱባብ ከተማንም ይዘዋል
-
78
የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
አ.አ፥ ከ600 እስረኞች በላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ዐሳወቀ፤ ጊምቢ፥ አልጄሪያ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋረጠች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን በቀይ ባሕር ቁልፍ የወደብ ከተማን ተቆጣጠሩ፤ ዋሽንግቶን፥ ዶናልድ ትራምፕ ፓርቲያቸው በአማካይ ዘመን ምርጫ ካሸነፈ ለእያንዳንዱ አዋቂ 5ሺህ ዶላር ሊሰጡ ቃል ገቡ
-
77
የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-- የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸዉ የኢሕአፓ መሪዎችና ጠበቃ በዋስ እንዲፈቱ የተላለፈላቸዉ ዉሳኔ ታገደ።-ብሪታንያ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኝ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን እንድትዘጋ እስራኤል ማሳሰቧን ብሪታንያ የሚጠበቅ፣ግን አሳዛኝና ግንኙነትን የሚያበላሽ በማለት ነቀፈችዉ።-የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።
-
76
የዓለም ዜና፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ
አርስተ ዜና፤ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች ሞቱ። -በትግራይ ክልል የሚገኙ አማፅያን የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ሌላ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል አሉ።-በሌላ በኩል በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የወጣቶችና የታዳጊ ልጆች አፈሳ ይቁም ሲሉ በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ እናቶች ለተቃዉሞ ወጡ።
-
75
የጳጉሜ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና
የትግራይ ክልል ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ገለልተኛ አይደሉም” በማለት ወነጀለ። በኢትዮጵያ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጥሪ አቀረቡ። መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ያስመዘገው የምርጫ ድል ፓርቲያቸውን ከመሠረቱ እንደነቀነቀ ተናገሩ
-
74
የጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
በየመን መንግስት ኃይሎችና «በኢራን ይደገፋሉ» የሚባሉት የሑቲ ደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ትላንት አገርሽቶ እስከ ዛሬ በተካሄደ ውግያ ከሁለቱም ወገን ከ140 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ተሰማ። በምሥራቅ ጀርመን በምትገኘው የዛክሰን አንሃልት ግዛት የአካባቢ ምርጫ እየተካሄደ ነው።
-
73
የነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ምስራቅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 20 ሰዎች ተገደሉ ። አስራ ስድስቱ የመንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ናቸው ። • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።
-
72
የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
በኢትዮጵያ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም ወደ 38,000 ኮምፒውተሮች እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።
-
71
የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሾመው የሱዳን ጉዳይ የምርመራ ቡድን፤ የውጭ ሐገራት ታጣቂዎች በሐገሪቱ ያለውን ግጭት እያባባሱት ነው ሲል ከሰሰ። የእስራኤል ጦር አባላት በምዕራባዊ ዮርዳኖስ የባሕር ዳርቻ 2 ፍልስጤማውያን ወጣቶችን ተኩሰው መግደላቸውን
-
70
የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-የጀርመንና የሩሲያ ተዘዋዋሪ ግጭት ወደ ቀጥታ ዉዝግብ፣ የጥቃት ሙከራ፣ ቅጣትና የአፀፋ ቅጣት ዛቻ ንሯል።---የቻይና መሪ ሺ ጂፒንግ የዉጪ መንግሥታት በመካከለኛዉ ምሥራቅ የዉስጥ ጉዳይ ጠልቃ እንዲገቡ የአካባቢዉ መንግሥታት መፍቀድ የለባቸዉም አሉ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን አንዳቸዉ የሌላቸዉን ተቋማትና ጥቅሞች መደብደባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።
-
69
የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማቸውን ማቋረጣቸው ተገለፀ ። የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ ። የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ ለያዘችው አቋም ፑቲንን አመሰገኑ። ፑቲንም ፔሽኬቭያንን ለተጋድሎአቸው አወደሱ
-
68
DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በአንድ ሣምንት 2,463 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት ከ6,000 በላይ ሰዎች በኢቦላ መያዛቸውን አረጋገጠ። በሱዳን የታቀደው ብሔራዊ ውይይት “የመጨረሻ ግብ በሕጋዊ ሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር” ያላት “የተባበረች፣ ሉዓላዊ እና ሰላማዊ” አገር መፍጠር ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መከረ። ሕንድ ከፓኪስታን ጋር የተፈራረመችውን የውኃ መጋራት ሥምምነት እንድታከብር በፍርድ ቤት የተላለፈባትን ውሳኔ ውድቅ አደረገች። የአሜሪካና ኢራን ጦርነት ዳግም ሲያገረሽ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።
-
67
የነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
የዛምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሐገር ክህደት ወንጀል እንደተከሰሱ የሐገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በወታደሮች ተቀስቅሶ የነበረው ዓመጽ በኒጀር መንግስት ታማኝ ወታደሮችና በሐገሪቱ ያሉ የሩስያ የአፍሪካ ጓድ ጦር አባላት ድጋፍ መክሸፉን ተከትሎ ከተማዋ በዛሬው ዕለት አንጻራዊ ሰላም ማግኘቷን ተነገረ። እስራኤል በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 2 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። ቱርክ፣ ሳውዲ ዓረቢያና ፓኪስታን በጋራ የመከላከያ ስምምነት ላይ ለመምከር ነገ በኢስታምቡል እንደሚገናኙ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
-
66
የነሐሴ 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ” ያላቸውን 32 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታወቀ። ሩሲያ ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 37 ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። ኔፓልና ቲቤት በሚዋሰኑበት ተራራማ አካባቢ በደረሰው የደራሽ ጎርፍ አደጋ መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 682 ደረሰ።
-
65
የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና ፤የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለስድስት ወራት ተቋርጦ የነበረውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪል ዘጋቢዎች የሥራ ፈቃድ ማደሱን መግለፁን ፣በደቡብ ሱዳን 49 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት መግለፃቸውን፣ኤስዋቲኒ አወዛጋቢ በሆነ የሶስተኛ ሀገር ስምምነት መሰረት ሁለት ስደተኞችን ከአሜሪካ መቀበሏን፣በሟቹ የኖሮዌ ንጉስ ሀኖርድ አምስተኛ ምትክ ልጃቸው ንጉሥ ሃኮን ስምንተኛ ተብለው መሰየማቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በሩ ጨርሶ አለመዘጋቱን መግለጿን እንዲሁም በኔፓል በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ህንዳውያን የደረሱበት አለመታወቁን አካቷል።
-
64
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ
አርስተ ዜና፤ -በያዝነዉ ነሐሴ ወር ብቻ ከ 60 በላይ ኢትዮጵያዉያን ፤ ከዕፅ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከሳዉዲ አረብያ የሚወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። -በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው አውዳሚ ድንገተኛ የጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ 300 በላይ ደረሰ። ከ 1300 በላይ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።-የአሜሪካው 9/11 ወይም የመስከረም 11 ዱ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ።-የበቦስኒያ የጦር ወንጀለኛ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
-
63
የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
የዛሬው የዓለም ዜና የኦባሳንጆን የሰሞኑን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፁን፣በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እና በስጋት እየተመለከቱት መሆኑን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የምዕራባዉያን ዲፕሎማቶች ማስታወቃቸውን፣የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸውን፣አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ የጣለችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምንም አይነት ግብ አያሳካም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መናገራቸውን፣የአሜሪካ የስለላ ኃላፊ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ን እንዲሁም በጀርመን አንድ የፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ሰራተኛ በወባ ህይወቱ ማለፉን አካቷል።
-
62
የነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ደቡብ ሱዳን ፤ ሁለት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ የመቀሌ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ። ኢትዮጵያ እ.ጎ.አ. በ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ሰነዷን በይፋ አቀረበች። የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች 79 ስደተኞችን ታደጉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትመልስ ነው። 1501ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ ተከበረ።
-
61
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና፤ በጫካ የሚገኙትና የፋኖ ንቅናቄ ተራ አባል ነኝ ሲሉ የገለፁልን አቶ እስክንድር ነጋ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከበርካታ የግድያ ሙከራ ማምለጣቸዉን ተናገሩ። እስክንድር ነጋ ጽምዶ የተባለዉን ጥምረት ን የኢትዮጵያ ጠላት ብለዉታል።-ዛሬ 35 ኛ ዓመት የነጻነት ቀንዋን ዛሬ ያከበረች ዩክሬይን መዲናዋ ላይ አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃምን ጨምሮ የአዉሮጳ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።- በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለዉን ግጭት ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፤ የአሜሪካን ከኢራን ጋር ስላለው ግጭት መፍትሄ ለማግኘት ከቴህራን ጋር በአክብሮት መነጋገር እንዳለባት አጽኖት ሰጡ።
-
60
የነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• በደቡባዊ ቱኒዚያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን አፍኖ ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ። • በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ቦርጉ ግዛት ታጣቂ ጂሃዲስቶች ትክክለኛውን የእስልምና አስተምሮ አልተከተሉም ባሏቸው ምዕመናን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። • ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የሚያስፈልጋትን የ30 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮጳ ህብረት እንደምትጠብቅ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። • አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ።
-
59
የነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
በዛሬው የዓለም ዜና ከአንድ ወር በላይ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁን ፣በናይጄሪያ በአክራሪ ቡድኖች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መታፈናቸው መገለፁን፣የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሃን ዋዴፉል ለጉብኝት ዛሬ ዩክሬን መግባታቸውን፣የስዊድን ፖሊስ በአሥራዎቹ ዕድሜ የምትገኝ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ መገደሏን ተከትሎ የበይነመረብ ትስስር መድረኮችን እየመረመረ መሆኑን ፣እንዲሁም በምስራቅ ስፔን በተከሰተ የሰደድ እሳት ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አካቷል።
-
58
የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
አንጎት፥ መንገድ ዳር የተጠመደ ፈንጂ ባለሦስት እግር ባጃጅ አጉኖ ጉዳት አደረሰ፤ ኦባሳንጆ ከአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ የማቅረቡ ምክንያት፤ ቡኒያ፥ ኢቦላ ዳግም ከተቀሰቀሰ 100ኛ ቀኑ ተቆጠረ፤ ፓሪስ፥ «ዩክሬንን ለመደገፍ የፈቃደኞች ጥምረት» የተባለው ቡድን ሰኞ ሊሰበሰብ ነው፤ ስቶኮህልም፥ ትምህርት ቤት በደረሰ የጎራዴ ጥቃት በርካቶች ቆሰሉ
-
57
የነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
ዛሬ ከቀትር በፊት መቀሌ ከተማ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 13 ሰዎች መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች አመለከቱ። ጥቃቱ የደረሰው በሲቪሎች መኖሪያ አካባቢ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የ4 ዓመት እስር ፍርድ አጸና። ኬንያ ውስጥ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ አብራሪውን ጨምሮ 7 ሰዎች ሞቱ። ስድስቱ ሀገር ጎብኚዎች ናቸው። ዶሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው M 23 የተሰኘው ታጣቂ ቡድን የኢቦላ ተሐዋሲ መዛመትን ለመቆጣጠር አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ደነገገ።
-
56
የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በስምንት አጀንዳዎች ላይ የመከሩባቸው ምክረ ሀሳቦች የተጠናቀረበት የመጨረሻ ሠነድ ነገ ለ 4 ሺህ ጉባኤተኞች እንደሚቀርብ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። በጎርጎሮሳዊው 2025 ዓ.ም. በዓለም ዙሪያ 350 የእርዳታ ሠራተኞች መገደላቸውን ያሳወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግድያዎች ተቀባይነት የሌላቸው ሲል ኮነነ የጀርመን አፍሪቃ ፋውንዴሽን የ35 ዓመቷን ወጣ ኬንያዊት ዋዊራ ንጂሩን ለዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት መረጠ። ንጂሩ የተመረጡት በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ኬንያውያን ተማሪዎች ምገባ በማደራጀታቸው ነው።
-
55
የነሐሴ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና
-የኢትዮጵያ የፈደራል መንግስት ጦር መቀሌ አጠገብ የሚገኝ ሥፍራን ዛሬ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል በማለት ህወሓት ወቀሰ።ህወሓት በድብደባዉ ሥለደረሰዉ ጉዳት አልገለፀም።አንድ የዓይን ምስክር ግን ቢያንስ አንድ ታጣቂ መገደሉንና ሌሎች ሁለት መቁሰላቸዉን አስታዉቀዋል።---የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያዉያን የተሰጠዉ አሜሪካ የመኖርና የመሥራት ጊዚያዊ ፈቃድ እንዲሰረዝ ወሰነ።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረግም፣ ሊደረግ የታቀደም ድርድር የለም አሉ።የኢራን ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ዩናይትድ ስቴትስ የገባችዉን ግዴታ ካላከበረች ሥልታዊዉ ወሽመጥ አይከፈትም።
-
54
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና --የሞሮኮ የጸጥታ ኃይሎች ድንበር አቋርጠዉ የስፔን ራስ-ገዝ ወደ ሆነችዉ ሴዑታ በየብስ እና በባህር አቋርጠዉ ለመግባት የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በቁጥጥር አዋሉ።-የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ኅልውና፣ ባለቤትነት እና የራስ-አስተዳደር መብት ዙሪያ "የክህደት ተግባር" ታይቷል ሲል እርምት ጠየቀ። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ባወጣዉ መግለጫ፤ የአብንን "ድምዳሜ የማይጋራው መሆኑን" ገልጿል።-የኢራን ጦር አንድ የአሜሪካ ወታደርን ለያዘ ወይም ለገደለ ሰው 30,000 ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታወቀ።
-
53
DW Amharic የነሐሴ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልል “የፖለቲካ መሪዎች የሕዝቡን ድምጽ እንዲሰሙ፣ ሰዎችን እየጎዱ ያሉ ችግሮችን የጋራ መግባባት በመፍጠር ለመፍታት እንዲሞክሩ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ አቀረበ። የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሱዳን ሊካሔድ ለታቀደው ብሔራዊ ውይይት ተሳታፊዎች “ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና የጸጥታ ዋስትና” ለመስጠት ቃል ገቡ። ለሊቱን በሩሲያና በዩክሬን በተፈጸሙ ኃይለኛ የድሮንና የሚሳይል ጥቃቶች በሁለቱም ሀገራት 12 ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
-
52
የነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው የቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሃት ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ “ በመንግስት የፀጥታ አባላት ተፈጸመ “ የተባለውን ግድያ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አወገዘ ፡፡ በኢትዮጵያ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች አሁንም "ከባድ" የሚባሉ ሥጋቶች መቀጠላቸውን የአውሮፓ ሕብረት ይፋ ባደረገው ኢትዮጵያን የተመለከተ የ2025 የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ገጽታ ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ይፋ ተደረገ።
-
51
የነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
• ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒ ጄ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ጋዜጠኞች የሽብር ወንጀል ፈጽመናል ብለው አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚደረግባቸውን ግፊት አወገዘ። • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በብሄራዊ ጦሩ ላይ መጠነ ሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት መክፈቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። • ዩጋንዳ በሶማሊያ የሚገኘውን የሰላም አስከባሪ ኃይሏን እዚያው እንደምታቆይ አስታወቀች። • የኢቦላ ወረርሽኝ ኮንጎ ውስጥ ተዋህሲው እስካሁን ባልደረሰበት ግዛት ውስጥ ተከሰተ • ፈረንሳይ የእስራኤል ሰፋሪዎች በኃይል በተያዘችው የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የሚፈጽሙትን ጥቃት በይፋ አወገዘች።
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
HOSTED BY
DW
Loading similar podcasts...