Drum of Changes podcast artwork

PODCAST · society

Drum of Changes

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

  1. 32

    85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት

    ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዚህ የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የፋሺስት ጣሊያን ዳግም ወረራ ምክንያቶች፣ የአውሮፓ ኃያላን በአፍሪካ የነበራቸው የተዛባ ፍላጎት፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ የዲፕሎማሲ ውድቀት እና የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት ያሳዩትን ጽናትና በድል የተጠናቅቀውን ድል አስመልክቶ ፣ የታሪክ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው እና በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህን አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  2. 31

    የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ

    "ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከአንግዶቻችን ጋር በዝርዝር እንቃኛለን፦  • ዓለም አቀፍ ፍትህ ወይንስ የምዕራባውያን የበላይነት መጠቀሚያ? — ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ ጋር። • የአፍሪካ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታና የቤት ልማት ፈተናዎች — ከዩኤን-ሀቢታት (UN-Habitat) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር።  • የመድኃኒት ዋስትና እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት — ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  3. 30

    የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ?

    ትልቁ የሩሲያ የመገበያያ መድረክ ‘ዋይልድቤሪስ’ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን አሳውቋል። “ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።” ሲሉ የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ ትልቁ የሩሲያ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ዋይልድቤሪስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀሉን መነሻ በማድረግ ይህ ስርዓት በኢትዮጵያ እንዴት እየተዋወቀ እንደሆነ እና ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለሸማቾች ምን ማለት እንደሆነ፣ ሰፊ አቅም ካለው የአፍሪካ ገበያ ተደራሽነት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስሳለን። የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ደግሞ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየሰጡ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ  ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  4. 29

    ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ

    “ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በፈርጆቹ መጋቢት 7፣ 2026 በሆርሙዝ ሰርጥ የመጓጓ ነፃትን ለማስከበር የኃይል አማራጭን ለመውሰድ የጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በሩሲያና ቻይና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት  ውድቅ መሆኑን እንመለከታለን። ይህ ሁኔታ አቅሙ እየተዳከመ ስለመጣው የምዕራቡ ዓለም ሁኔታ ምን ይነግረናል? የእዮብዘር ዘውዴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  5. 28

    አፍሪካን የመበየን አባዜ፤ የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት

    “የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሁለተኛ ጉዳያችን ደግሞ 10ኛው የኢትዮ ጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንግረስ 2026 ላይ የሚያተኩር ይሆናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  6. 27

    የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነረው ውጥና የኢትዮጵያ ምላሽ

    “እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥን እና የኢትዮጵያን ምላሽ ያስቃኘናል። በቀደመው ጊዜ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ባለሙያ እና ምሁር እንዲሁም ተመራማሪ የሆኑትን ኃይሉ ታምሩን (ዶ/ር) አነጋግረን ሰው ሰራሽ አስተውሎ በአፍሪካ የጤና ምርምርን ከማገዝ አንፃር የሚኖረዉን ሚና ቃኝተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  7. 26

    የፈውስ ክር:- በሚገባው ልክ ያልታወቀው በገና

    በገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው። “ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከል በገና እንቃኛለን። በገና ለመንፈሳዊ ፈውስ መዋል ስለመቻሉም እናነሳለን። ለዚህም ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሓላፊ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ጠባቂ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ግዛው የድምፅ ኢንጅነር፣ አቶ ካሳሁን ሓይለማሪያም የማሕበረቅዱሳን ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ብሌን ዮሴፍ የሙዚቃ መምህርት እና ባለሞያን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራምን ያዳምጡ: 

  8. 25

    የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ እንደ ጂኦፖለቲካ መሣሪያ፡- ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ እና የደቡቡ ዓለም እውነታ

    “የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት የተዘጋጀውንና ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ በመባል የሚታወቀውን ሰነድ በማዳሰስ ላለፉት አስርት ዓመታት የምዕራቡ ዓለም በተለይም በተመረጡ 13 የደቡቡ ዓለም ሀገራት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የህዝብ ቁትራቸው እንዳያድግ ሲከተለው የነበረውን ስትራቴጂ እንፈሻለን። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ጋር ቆይታ በማድረግ ይህንን ሰነድ ፈትሸነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  9. 24

    ካሳ እና ፍትህ፡ በፓን አፍሪካዊ ማህደረ ትውስታ እና በዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካ መካከል

    “አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን የትግል ጉዞ እንመለከታለን። በዚህ ጉዞ ውስጥም ለጥቁር ሕዝቦች የቆሙ ተቋሟት ዛሬም ድረስ ከቀጠለው የቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ግብዝነት ጋር የሚያደርጉትን ትግል እንፈትሻለን። ለዚህም ታዲያ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉት ጥቁር አሜሪካዊቷ ፓናፍሪካኒስት፣ ደራሲ እና ወደ አፍሪካ የመመለስ ንቅናቄ አንቂ ጃኔል ሆይሌትን ጋብዝን በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  10. 23

    በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግል

    የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለጠው እውነታ ቢኖር አፍሪካ ዛሬም ድረስ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎቷ በምዕራባውያን መድኃኒት አቅራቢ ኩባንያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው። “የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ትንቅራችን በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አጣዳፊ ጉዳይ ስለመሆኑ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ደቡብ አፍሪካዊቷ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያዋ ሻኪራ ቹናራን አነጋግረናል። ተከታዩ ጥንቅራችን ደግሞ፣ በአፍሪካ ሌላኛውን የሉዓላዊነት ገፅታ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ምስጋናው እያሱ፣ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ፋይናንስ አማካሪ እንዲሁም ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ፣ በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል ። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  11. 22

    የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄ

    ኩባ ለአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ትግል የከፈለችው መስዕዋትነት የአህጉሪቱ የማይረሳ የታሪክ አንዱ ገጽ ነው። “ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ። ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል።  “ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። በዛሬው የ ድሪም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ስለ ግላኮማ በሽታ ከስፔሻሊስትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ጋር እንመክራለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ስለ ኩባ የታሪክ መስዋዕትነት ከኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ጋር እንቆያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  12. 21

    የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ:- የአፍሪካ አገራትን እንዴት ሊጎዳ ይችላል ?

    የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነዳጅ ዋጋን ብሎም የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ባለብት ሁኔታ አፍሪካ ቆማ መመልከት አትችልም። አማራጭ የኃይል አቅርቦት ላይ ማተኮር፣ ቀጣናዊ ትስስርን ማፋጠን ግድ ይላታል። “ለአፍሪካ ይህ በጣም መጥፎ ዜና ነው። የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አብዛኞቹ አገራት እንዲህ ዓይነቱን ጫና ለቋቋም እጅጉን ይቸገራሉ። [...] ስለዚህ የአፍሪካ አገራት ስለ አማራጭ የኃይል ምንጮች የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።እንደሚታወቀው አፍሪካ ብዙ አማራጮች አሏት”ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን የጦር ዘመቻ ተከትሎ በአፍሪካ ላይ የሚመጣውን ሁለንትናዊ ጫና እና መፍትሄዎቹን በተመለከተ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግርናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ መጋቢት 17-18 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አራተኛውን “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረምን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ቆይታ ታደምጣላችሁ። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  13. 20

    የሩሲያ ቀይ መስመር :- የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ዩክሬንን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ የማሰታጠቅ ፍላጎት

    ፈረንሳይ እና ብሪታኒያ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መንቀሳቀሳቸውን የሩሲያ የውጭ መረጃ ደህንነት ይፋ አድርጓል። "ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ አቅም አልባ ትንንሽ ግዘቶች የመከፋፈል እቅዳቸው የቆየ ነው […] ከሰሞኑ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ማሰባቸው ይህ እቅዳቸው በመክሸፉ ተስፋ የመቁረጣቸው ማሳያ ነው" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መዘጋጀታቸው ምን ዓለም አቀፍ ትርጓሜ አለው ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  14. 19

    የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን መንቃት፣ የራስ እውነታን ከራስ እይታ አንፃር የመንገር የትብብር ጉዞ

    የዓለም አቀፉ ደቡብ ጋዜጠኞችም ዓለም አቀፍ ክስተቶችን ከራሳቸው ታሪክ፣ ፍላጎት እና እውነታዎች አንፃር በመቃኘት የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቅናት የጋራ ጥረቶችን ጀምረዋል። "ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፍ ዜናዎች ከአንድ አቅጣጫ የሚመጡ እና የአንድ ወገን ሐሳብን የሚያንቀባርቁ ነበሩ … በአንፃሩ ደግሞ አሁን ያለንበት ወቅት የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ንቃት ጎልቶ ይስተዋላል … የዓለም ታሪክ ርዕሰ አንቀጽ እንጂ የማንኛውም ታሪክ ዳራ መሆንን እምቢኝ ያሉበት ወቅት ነው" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለሚያደርጓቸው ትብብሮች በቀዳሚነት እንቃኛለን። ለዚህም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) አብረዉን ቆይታ አድርገዋል። በሁለተኛው ጥቅራችን ደግሞ በአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ ስረዓት እጣፈንታን በተመለከተ፣ በቴንድኤክስ አዲስ አበባ 2026 ጉባኤ ላይ ተገኝተን ኮምፑሊንክስ የተሰኘ ኩባንያ ቢዝነስ ዳይሬክተር የሆኑትን ቻውላ ጋናትራን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ

  15. 18

    የሰው ልጅ ታሪክ አዲስ መልክ፦ በኢትዮጵያ የተገኘው 2.6 ሚሊዮን ዓመት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ስለማንነታችን ምን ይነግረናል ?

    “ ከቆዳችን በታች ሁላችንም አንድ አይነት መሆናችንን እናያለን … ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓለማ ከዚህ የተለየ ኃቅ ሊያሳዩን የመቻል አቅማቸዉን አሳንሼ ግን ማየት አልፈልግም … ነገር ግን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ሩሲያ ወይት ሌላ ቦታ ብንኖር ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር ነን” ሲሉ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ ተመራማሪ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እጅግ የተሟላ እና ጥንታዊ የሆነችውንና ከ3.3 ሚሊየን በላይ እድሜ ያላት የሰላምን (አውስትረሎፒቲከስ አፋረንሲስን) እና በቅርቡ የተገኘውን የ 2.6 ሚሊየን እድሜ ባለቤት ፓራንትሮፐስ ጨምሮ የብዙ ግኝቶች እና ምርምሮች ባለቤት፣'ምድረ ቀደምት (ላንድ ኦቭ ኦሪጅን)' የሚለውን መጠሪያ ያስተዋወቁ እና በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ተመራማሪ መምህር፣ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።በቅርቡ ያገኙትን ቅሪተአካል (ፓራንትሮፐስ) መነሻ በማድረግ ስለሰው ዘር አመጣጥ ፣ኢትዮጵያ ስላላት ማዕከላዊ ስፍራም እናወጋለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  16. 17

    በአውሮፓ እስረኛ የሆኑ ቅርሶች፡- ኢትዮጵያ ቅርሶቿን የማስመለስ ትግል

    የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው። "ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አባተ ጎበና (ዶ/ር) በበኩላቸው "በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጡ እንግሊዛውያን፣ አስቀድመው ስለኢትዮጵያ ውድ ቅርሶች ያውቁ ነበር። ቅርሶቹን ለመዝረፍ በጀት ተመድቦላቸው የመጡ ባለሞያዎችም የሀገሪቱ ቅርሶች ዘርፈዋል።[...] ምዕራባዉያን [በማንኛውም መልኩቢመጡ] ባዶ እጃቸውን ግን አይመለሱም ነበር።" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በምእራቡ ዓለም እስረኛ የሆኑ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቅርሶችን ጉዳይ እንመረምራለን። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  17. 16

    የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ንግድና ምጣኔ ሐብት አኳያ ሲቃኝ

    ''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ በተመለከተ ከአሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶክተር ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ጉዳይን በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት ፊት ስለማቅረብ ከያዛቸው ውድነህ የኢንቫይሮመንታል ጂዮግራፈር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና አዳፕቲሽን ባለሙያ፣ መምህርና ተመራማሪ ጋር ቃኝተነዋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ

  18. 15

    የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ

    "አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከራከሪያ ከሚያቀርቡት እና በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደርጋል። በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የከንቲባዎች ምክክር መነሻ በማድርግ የአፍሪካ ከተሞችን እና የእድገት ጉዟቸዉን ይዳስሳል። ለዚህም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ እንግዶች ጋር ቆይታውን ያደርጋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  19. 14

    ሩሲያን የመነጠል ሙከራዎች መክሸፋና ከአፍሪካ ጋር የተጠናከረው ሁለንተናዊ ግንኙነት

    "በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ 2025 ዲፕሎማሲያዊ ግምገማ እና ለ2026 የተያዘውን ውጥን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ዳዊት መዝገበ ምልከታቸውን ያጋሩናል። በሁለተኛው ክፍል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአህጉሪቱን የግብርና ዘርፍ ለማበልፀግ ስለተነደፈ እቅድ እንዳስሳለን። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ማንደፍሮን (ዶ/ር) አነጋግረናል።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  20. 13

    ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩ፦ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ምን ዋሉ ?

    "አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ፣ በቅርቡ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጉዳዩ አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክ እና ማህበረሰብ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዘላለም ተፈራን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  21. 12

    አፍሪካ የቆዳ ማንጫ ቅባቶን የመጠቀም ልማድ ማሻቀብ፣ መንስኤዎቹ እና ማህበራዊ መዘዞቹ

    “አፍሪካውያን የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን እንዲጠቀሙ ከሚገፋፉ ምክያቶች መካከል የምዕራቡ ዓለም የውበት መስፈሪያ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል[…]ምርቶች እንዲሸጡላቸውም በማህበራዊ ሚዲያ የውበት መስፈርትን የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሉ” ሲሉ በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በመላው አፍሪካ፣ የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መማጣቱን በማንሳት ጤና እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ቀውስ እንቃኛለን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ዙሪያ ሞያዊ ምልከታቸዉን እንዲያጋሩንም በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ ከ 12,000 ዓመታት በኋላ እንደፈነዳ የተነገረለትን የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የጠፈር ሳይንስ እና የስነ ፈለክ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ፕሮፌሰር አታላይ አየለን አነጋግረናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  22. 11

    የእስራኤል እውቅና ለሶማሊላንድ ፦ የሶማሊያ ተቃዉሞ እና የቀጣናው እጣፈንታ

    ሶማሌላንድ ከእስራኤል ያገኘችው የሀገርነት እውቅና በተወሰነ ደረጃ ህጋዊነትን እንድታገኝ ቢያስችላትም፣ ከሶማሊያ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራት እየተሰጠው ያሉ ምላሾች በመጭው ጊዜያት የግዛት አንድነት ጥያቄዎች ማዕከላዊ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳያል። "እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ፣ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ ይታያል … በቀጣናው ሶማሊላንድ አዲስ ተዋናይ ሆና ብቅ ልትል ትችላለች፣ አዲስ ዓይነት የኃይል አሰላለፍም ሊፈጠር ይችላል" ሲሉ ጠበቃ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን እንመለከታለን። በቀዳሚው ጥንቅራችን ከሰሞኑ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችዉን የሀገርነት እውቅና እንስተን አንድምታዎቹን እንመለከታለን። ለዚህም ኢትዮጵያዊውን ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በማንሳት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባ የሚኖረዉን ሚና እንቃኛለን። ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር፣  የሺዓለም ገዛኸኝ (ዶ/ር) በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ትመህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር፣ እና አቶ አበበ ፀጋዬ በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የአይሲቲ ዋና ዳይሬክተርን አነጋግረናል። በመጨረሻው ጥንቅራችን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ዝግጅትን መነሻ አድርገን ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ዲቪዚዮን የከባድ ጥገና ማዕከል ምክትል አዛዥ ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡትን ገለፃ ወደእናንተ እናደርሳለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

  23. 10

    የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር

    “ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል። ”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አንዳለ ንጉሴ ናቸው።  በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ወቅት ያነሷቸዉን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ከዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ እና ከደቡብ ለደቡብ ትብብር አንፃር የሚኖራቸዉን አንድምታዎች እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉን ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋን (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን አንዳለ ንጉሴን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  24. 9

    የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ እና የሩሲያ በዘመናት የተፈተነ ከጭቁኖች ጋር የመቆም ታሪክ

    “የብሪክስ መድረክ ለአባል ሀገራት የበለጠ ስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂ እና የጋራ ጥቅምን መሰረት ያድረጉ ግንኙነቶችን ለመመስረት እድል ይሰጣል። ከዚህ አናፃር የኢትዮጵያ እና የህንድ ግንኙነት ከዚህ ማዕቀፍ በእጅጉ ይጠቀማል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከብሪክስ አገራት ትብብር አንፃር ቀዳሚ ጉዳዩ አድርጎ ይቃኛል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን የሶቪየት ኅብርት ለአፍሪካ የነፃነት ምን ሚና ነበራት ሲል ይጠይቃል ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን አጋርነትም በሰፊው እንዳስሳለን። “ሩሲያ በታሪኳ በሙሉ በአፍሪካ ሕዝቦች ጭቆና ውስጥ ተሳትፋ አታውቅም ካለማወቋም በላይ እራሷን በዓለም ዙሪያ ለተጨቆኑ ሕዝቦች ድምፅ እንዲሁም የትግላቸው ደጋፊ ነች” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የታሪክ ተመራማሪ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  25. 8

    የጥቁር ህዝቦች የካሳና ፍትህ ጉዳይ ፦ አውሮፓዉያኑ እንዲነሳ የማይፈልጉት ጥያቄ ለምን ሆነ ?

    "ብዙዎቻችን ከየት እንደመጣን ምንም ባናውቅም፣ ስደተኞች ግን አይደለንም። በእገታ የተወሰድን አፍሪቃውያን ነን። አያት ቅድመ አያቶቻችን ማንነታቸዉን ሳያውቁ ወደ መቃብር ወርደዋል። የ'ባሪያ' ልጆች መሆናችንን ብቻ ነው የተማርነው። ይህም ለሕዝባችን ብዙ ግራ መጋባት ፈጥሯል፣ የማንነት እጦትን ፈጠሯል"- ሲሉ ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኟ ጅኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን፣ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት በደልና ፍትህ እንዲሁም የካሳ ጥያቄን እናነሳለን ፡፡ ይሄው ጥያቄ በአውሮፓውያን ዘንድ ከመውያያ አጀንዳነት ለምን እንደሚገፋና ሌሎችንም ጉዳዮችን መነሻ አድርገን ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ጅኔል ሆይሌት ጋር በሰፊው እንወያያለን። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ አፍሪካ ከሕገ መንግሥታዊነት፣ ከዳኝነት ነፃነት ጋር በተያያዘ ያላትን ቀጣይ ትግል እና በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዙሪያ ስላለው ሰፊ ክርክር እንመለከታለን። ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና አቶ ቸርነተት ሆርዶፋ፣ የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ዳኝነት ኮንፈረንስ አባልን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  26. 7

    ድርብ መስፈርት ፡- የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና የአፍሪካ የፍትህ ጥያቄ

    ‘‘ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሶሪያ ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በብሪታኒያ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ተጀምረው የነበሩ ምርመራዎች በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በድንገት እንዲቋረጡ ሆነዋል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቃቸው ግን አሳማኝ ምክንያት አይሰጡህም፡፡ ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መንገድ የሚዳኝበት መንገድ በጣም የገዘፈ ነው፡፡’’ ሲሉ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡የዛሬው ድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ በቀዳሚነት አፍሪካን ማጥቂያ የሆነው በዓለምአቀፉ ወንጀለኞች ፍርድቤት የሚደርስባት አድሏዊ አሰራርና በደልን እንዳስሳለን። ለዚህም የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የአፍሪካ ደራሲያን እና አሳታሚዎች የአህጉሪቱ የባህልና የቋንቋ ሀብቶች ተገቢ እና እውነተኛ እውቅና ያገኙ ዘንድ በአለም አቀፍ መድረኮች ስለሚያሰሟቸው ጥሪዎች እንወያያለን ፤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነጽሁፍ መምህር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር)ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  27. 6

    ከትናንት እስከ ዛሬ ፡ የዓለምአቀፍ ተቋማት አድሏዊነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ ከሊግ ኦፍ ኔሽን እስከ ጸጥታው ም/ቤት

    "አፍሪካ እንደገና የተዋቀረ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት ዓለም አቀፍ ስረዐት ያስፈልጋታል። የተባበሩት መንግስታት አሁን ባለው አቋም የአፍሪካን ጥቅም የሚያስከብር አይደለም። በእኔ እይታ የተባበሩት መንግስታት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚጋለብ፣ምዕራባውያን የሚነዱት ፈረስ ነው።" - ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን ፣ በቀዳሚነት አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋመት ውስጥ ፍትሃዊ እና እኩል ውክልና ለማግኘት የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ጥረት እንፈትሻለን። ለዚህም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እን አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሂኑትም አቶ ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችንም ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን ጠብቆ ማቆየት ለአፍሪካ፣ ብሎም ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ ካሉ አገራት ጋር ለሚኖራት መልካም ግንኙነት ስለሚኖራቸው ቦታ ደግሞ ሁለተኛው ጥንቅራችን ያስቀኛናል። በዚህ ጉዳይ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያጋሩን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑትን መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤልን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  28. 5

    የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ነጻ ማውጣት፦ በ ንጉግ ዋ ቲዮንጎ እይታ

    "እኛ ደግሞ አፍሪካውያኖች የራሳችን ታሪክ የምንነግርበት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናስተላልፍበት ጥበብ፣ የራሳችን መንገድ አለን። ስለዚህ ይሄ የአውሮፓ ተኮር የሆነውን አመለካከት ከአፍሪካ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አውጥተን በአፍሪካ ተኮር ወይም ደግሞ አፍሮ ሴንትሪክ በሆነው ስንተካ አንደኛ ዲኮሎናይዝ እያደረግን ነው ማለት ነው።" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሁፍ መምህርና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ስነጽሁፍ አስተማሪ እና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰን (ዶ/ር) አነጋግሮ የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ለማላቀቅ መደረግ ያሉባቸውን ጉዳዮች በቀዳሚው ክፍል እናስደምጣችኋለን። እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ መለያ የሆኗትን አትሌቲክስ (አትሌቶቿን) እና ቡናን በዲፕሎማሲ ረገድ ''ሶፍት ዲፕሎማሲ'' አማራጭነት መጠቀም በምትችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁለተኛው ጉዳያችን አድርገነዋል። ለዚህም የታሪክ አጥኝ እና የመገናኛ ብዙሀን ጥናት ባለሞያ የሆኑትን ተረፈ ወርቁን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  29. 4

    ካሳ ወይስ የቀድሞውን መመለስ ፡ የአፍሪካ ጥሪ ለእውነተኛ ፍትህ

     "ይህ የአፍሪካ ዕዳ ተብሎ የሚጠራው ነገር በቀላሉ መወገድ አለበት። ሌባ ከቤትህ ሰርቆ ሲያበቃ እንዴት እንካ ቤትህን ስራበት ብሎ ገንዘብ ሊያበድርህ ይችላል? እንዴትስ ከራስህ ሰርቆ ያበደረህ ገንዘብ ላይ ወለድ ሊጥል ይችላል? ይህ ግራአጋቢ ነገር ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ "ፍትህ ለአፍሪካውያን እና አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው ሁሉ በካሳ መልክ" የሚለው ሐሳብ የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ 2025 መሰባሰብያ ጭብጥ ነው። የአፍሪካ ፍትህና ካሳ በምን መልኩ ሊለካ ይችላል ፣ መልሱ ከባድ አከራካሪም ነውና ለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ጋር ቆይታ አርጓል። የኢትዮጵያ የባህር ባለቤትነት ጥያቄን በተመለከተ በሰላሌ ዩኒቨርስቲ የታሪክና የቅርስ ጥበቃ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪውን ደረጀ ኃይሌ አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  30. 3

    የአፍሪካ ቀጣናዊ ጥምረቶች ፣ የአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ወይስ ወጥመዶች?

    "አፍሪካ የገንዘብ ሀብት እጥረት እንደሌለባት ልብ ማለት ያስፈልጋል - አፍሪካውያን የጎደለን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሆን ፍላጎት ነው። በእውነት የሚያስፈልገን ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚያስችል ቁርጠኝነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ቁርጠኝነት ስለጎደለንም ልብ በሚሰብር መልኩ ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነን ቀርተናል" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ድራም ኦፍ ቼንጅስ በዛሬው ዝግጅቱ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል ፡፡ አህጉሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጣናዊ ጥምረቶች ለአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ናቸው ወይስ በውስን የፋይናንስ አቅማቸው ምክንያት አፍሪካን የማጥመጃ መረብ ሆነዋል ? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ 'በአረቡ ዓለም ፖለቲካ በተሳሳተ መንገድ እንድትሳልና ብሔራዊ ጥቋንም ለማስከበር ' የአረብ ሊግ ሊሆን ቀጣይ የጥምረት መዳረሻዋ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምክለታቸውን አጋርተውናል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  31. 2

    ከምዕራቡ ዓለም ባሻገር :- ኢትዮጵያ ለቱሪዝሟ እድገት ወደ ደቡባዊው ዓለም ታማትራለች

    "ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉ አቅፋ ይዛለች ። ስለዚህ አንድ ሰው አፍሪካን በእውነት መጎብኘት ከፈለገ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሁሉንም ማየት ይችላል።[…] ስለዚህ፣ በብሪክስ ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገሮችን፣ ጥሩ የህዝብ ብዛትን እና ጥሩ ኢኮኖሚን በተመሳሳይ ጊዜ እናገኛለን፤ ይህም እነርሱን የቱሪስት እንግዶቻችን ልናደርጋቸው ያስችለናል።[...] ስፑትኒክ አፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ብዙዎች ጋር ለማድረስ ይረዳናል። ሚዲያው ቢሮውን በኢትዮጵያ መክፈቱም ከራዕያችን ጋር በእጅጉ የተጣጣመ ነው" - ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን አነጋግሮ የኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ሀገራት ጭምር በማዞር አዲስ የቱሪዝም የገበያ እያማተረች ስለመሆኗ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን ይዳስሳል። እንዲሁም ቻይና በቅርቡ ለአፍሪካ ሀገራት '' እተገብረዋለሁ'' ያለችውን የዜሮ ታሪፍ ጉዳይ ያነሳል። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ክቡር ገናን አነጋግሯል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

HOSTED BY

Zelalem Demissie

Frequently Asked Questions

How many episodes does Drum of Changes have?

Drum of Changes currently has 31 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is Drum of Changes about?

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa...

How often does Drum of Changes release new episodes?

Drum of Changes has 31 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to Drum of Changes?

You can listen to Drum of Changes on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts Drum of Changes?

Drum of Changes is created and hosted by Zelalem Demissie.
URL copied to clipboard!