PODCAST
DW | Amharic - News
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
-
14
አሜሪካን ጀርመን የሚገኙ ወታደሮቿን የማስወጣት እቅዷ መልዕክትና አንድምታው
ዩናይትድ ስቴትስ ጀርመን የሚገኙ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቿን እንደምታሳውጣ ባለፈው ሳምንት ማሳወቋ በጀርመን ብሎም በአውሮጳ የሰሞኑ ዐቢይ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። ይህ የአሜሪካን ውሳኔ የጀርመን መራኄ መንግሥት ዋሽንግተን በኢራን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ስልት ከተቹ በኋላ ይፋ መደረጉ ጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲስብ አድርጓል።
-
13
የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም
የጥንት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ በዛሬዉ ዕለት ታስቦ ዉሏል። ሚያዚያ 27 ኢትዮጵያውያን የፋሽስት ወረራን በሕብረትና በአርበኝነት ተጋድሎ የቀለበሱበት ቀን ነው። ይህ ድል ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ውድመት፣ እልቂት ከደረሰ እና መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የተገኘ ነዉ።
-
12
በምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞን
በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ገዢው ፓርቲ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀም እያደረሰብን ያለው ተጽዕኖ እና በአካባቢው ያለው የጸጥታ ስጋት ለምርጫ ቅስቀሳ ሥራችን እንቅፋት ሆኖብናል አሉ። ፓርቲዎቹ ይህ የምርጫውን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከተዉ ነዉ ብለዋል።
-
11
የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ የሚኖረው ጫና
የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ትናንት ጉልህ ጭማሪ አድጓል። በዚህ መሠረት በሊትር 23 ብር ጭማሪ የተደረገበት ቤንዚን 167 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል። አንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ኹኔታው አደጋ እንዳይፈጥር ሥጋታቸውን ገልፀዋል።
-
10
የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን የመውጣት አንደምታ
የአሜሪካ የጦር ሚኒስቴር (ፔንታጎን) በጀርመን ከሰፈሩት ወታደሮቹ ቢያንስ አምስት ሺውን የሚያስወጣ መሆኑን ባለፈው አርብ አስታውቋል።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማግስቱ በሰጡት መግለጫም ተጨማሪ ወታደራች ከጀርመን ሊወጡ እንደሚችሉ ብቻ ሳይሆን በጣሊያንና ስፔን ካሉት ወታደሮችም ተመላሾች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ስተዋል።
-
9
የደን ልማትን ለማስፋፋት የግለሰብ ጥረት በአሶሳ
ለደን ሀብት መመናመን ዋነኛ ምክንያቱ በአብዛኛው ሰዎች ቢሆኑም የተራቆተ አካባቢን በዛፍና ተክሎች ሸፍነው አረንጓዴ የሚያለብሱትም ያው ሰዎች ናቸው። የዛሬው የጤና እና አካባቢ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ከ30 ዓመታት በላይ የተራቆተ አካባቢን በሀገር በቀል ዛፎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች በማልበስ የተሸለሙ ሰው ያስተዋውቀናል ።
-
8
የትግራይ ክልል አዲስ ፕሬዝደንት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ እየጠበቀ ነው-ግጭት የማቆም ሥምምነቱስ?
በህወሓት ውሳኔ መሠረት በጳጉሜ 2012 በተካሔደው እና ፌድራል መንግሥት “ሕገ-ወጥ” ባለው ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪዎቹ ቀናት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ወደ ሥራ መመለስም ይሁን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ቀጣይ ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚበይኑ ይሆናል።
-
7
የናሳ አዳዲስ ፕላኔቶች ፍለጋ
ናሳ ያለፈው ማክሰኞ፣ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 22 ቀን ፣ ከስርዓተ ፀሐይ/ Solar System/ ውጭ ያሉ ፕላኔቶችን ለመፈለግ እና ያልታወቀ ቁስ ሀይልን ሚስጥሮችን ለመመርመር አዲስ ቴሌስኮፕ ይፋ አድርጓል። በመጭው መስከረም ተልዕኮውን ለመጀመር ወደ አፅናፈ ዓለም ወይም ዩንቨርስ የምትጓዘው ይህቺ ቴሌስኮፕ ሮማን የሚል ስም ተሰጥቷታል።
-
6
የነዳጅ እጥረቱ በአማራ ክልል በርካቶችን ለኑሮ መመሰቃቀል ዳርጓል ተባለ
በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መዳረጉ ተገለጸ። አሽከርካሪዎች፣ ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ ወር ለሚደርስ ጊዜ ስራ በማቆማቸው ለቤት ኪራይና ለዕለት ጉርስ መቸገራቸውን ተናግረዋል።
-
5
ለኦሮሚያው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ የሚጠይቁት ወጣቶች
በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት ዕልባት እልባት እንዲያገኝ ጥረቶች ቀጥለዋል። ከሰሞኑ ፋነ ነጋ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ወጣቶችን ያሳተፈ የሰላም ጉባኤ አዳማ ከተማ ውስጥ ተካሂዷል። በክልልu የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ሄድ መለስ የሚለው የጸጥታ መደፍረስ ዘላቂ እልባት እንዲበጅለት ሁሌም ምኞታችን ነው ይላሉ ።
-
4
አፍሪቃ ወደ ኋላ የቀረችበት የተመድ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ያሰቀመጠው ቀነ ገደብ ከአምስት አመታት ያነሰ ጊዜ ብቻ ቀርተውታል።አብዛኛዎቹን ግቦች ከማሳካት አንጻር ግን አፍሪካ ወደ ኋላ መቅረቷን በህብረቱ ጉባኤ ላይ የተገኙ ተናጋሪዎች አመልክተዋል።
-
3
«በኢትዮጵያ አካታች ዕርቅ ይምጣ» የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኅበራት ጉባዔ በአሜሪካ
በኢትዮጵያ ድህረ ግጭት አካታች የእርቅ እና የሰላም ሂደት ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን፣የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኅበራት ጉባዔ (ኢሕማጉ) አመለከተ። በአሜሪካ የሚገኘው ማኅበሩ፣ “ኢትዮጵያን ለማዳን ምን መደረግ አለበት” በሚል ርዕስ፣ሰሞኑን በታዋቂ ምሁራን የተመራ ሕዝባዊ ጉባኤ አካሂደዋል።
-
2
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር የጀመረው የብትን ጭነት አገልግሎት
አገልግሎቱ አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት በተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት የወጪ ንግድ ትልቅ ፈተና የሆነው የኮንትነር እጥረት በመቅረፍ ወጪ-ገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ እንደሚረዳ ተገልጿል።
-
1
የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ወቅታዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ለሚያዚያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. በተናጥል በ10 ከተሞች ጠርቶ የነበረውን የአደባባይ ሰልፍ መሰረዙን ዐሳወቀ፡፡ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነትን ከመሰረቱ አራት የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢሕአፓ ሰልፉ እንደትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅት ወደፊት ቀኑ ተለይቶ እንደሚጠራም ነው ያሳወቀው፡፡
-
0
የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ቤት ያንኳኳው የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀውስ ራሷን ማግለል የምትችለበት አቅም በርግጥ የላትም። ምክንያቱም ከ90 በመቶ በላይ ለምትጠቀመው ነዳጅ ጥገኝነቷ በዚህ በተቃወሰውው የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ላይ በመሆኑ ነው። ይህ ደግሞ የሩቁ ሰደድ እሳት ዛሬ ለአንዳንዱ ቤተሰብ አስቀድሞ የቀውሱ ገፈት ለመቅመስ ምክንያት መሆኑ ነው ከየአካባቢው የሚሰማው።
-
-1
የሚያዝያ 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በዛሬው የስፖርት መሰናዶ፦ አዲስ አበባ ውስጥ ስለተደረገው የመጀመሪያው ግራንድ ፕሪ ፉክክር ዘገባ ይኖረናል ። ባዬር ሙይንሽን ከወዲሁ ዋንጫውን ማንሳቱን ስላረጋገጠበት የጀርመን ቡንደስሊጋም ዳሰሳ ይኖረናል ። ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን ድል አድርጎ በነጥብ ተጠግቶታል ።
-
-2
ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረ
በሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ።
-
-3
ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» - አዲስ ስታንዳርድ
ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ቦታው የተወሰደው ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» ሲል አሠሪው አዲስ ስታንዳርድ ዛሬ አሳወቀ።
-
-4
ሕገወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው?
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ እና ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ውስጥ በተናጥል የተፈጸሙ ድርጊቶች በማኅበራዊ መገናኛው የበርካቶችን ትኩረት ስበዋል። በሮቤ ዕድሜያቸው ጠና ያለው አባት በጎረምሶች ሲደበደቡና በአምቦ ደግሞ የተደራጁ ናቸው የተባሉ ወጣቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ድብደባዎችን ሲፈጽሙ ነው የታዩት።
-
-5
ህወሓት ከ2013 ዓ.ም በፊት የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወሰነ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጥቅምት 24 ከ2013 ዓ.ም በፊት የተመረጠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ መወሰኑን አስታወቀ። የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የሲቪክ ድርጅት፣ የህወሓት ውሳኔ በክልሉ ዳግም የጦርነት ሥጋት እንደሚፈጥር ገልፀዋል።
-
-6
የጄነራል ታደሰ ወረደ ሹመት መራዘም ለክልሉ መፍትሔ ወይስ ሌላ ቀውስ ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሣምንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዳራዘሙ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በገታው ግጭት የማቆም ሥምምነት ለተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ሉቴናንት ጄኔራል ታደሰ ሁለተኛ ፕሬዝደንት ናቸው።
-
-7
የ "ሰላም ለኢትዮጵያ" ጥምረት ራሱን ከምርጫ ለማግለል የሚገደድበት ኹኔታ መኖሩን ገለጸ
ስምንት ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሰባሰበው "ሰላም ለኢትዮጵያ" የተባለው ጥምረት፣ በጥምረቱ ላይ ደረሱ ያላቸው ጥሰቶችና ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ራሱን ከምርጫ ለማግለል እንደሚገደድ ገለፀ። ጥምረቱ ዓርብ ባወጣው መግለጫ በአባሎቹ፣ በደጋፊዎቹ እና በዕጩዎቹ ላይ "ጥቃት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት" እየተፈፀመ መሆኑን አስታውቋል።
-
-8
ሶማሊያ ቱርክ የነዳጅ ክምችቷን እንድትጠቀም ለምን ፈቀደች?
ቱርክ በሶማሊያ የባህር ዳርቻ ነዳጅ ለማውጣት ዝግጅት ላይ ነች፡። ለነዳጅ ፍለጋው ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ትልቅ መርከብ ካግሪ ቤይ፤ ከሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ደርሳለች። በጎርጎሪያኑ በ2024 ሁለቱ ሀገራት የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብሩ አሁን ወደ ነዳጅ ፍለጋ አድጓል።
-
-9
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና
ወደብ ተከራይታና ነዳጅ ከዓለም ገበያ ገዝታ የምታስገባው ኢትዮጵያ በአሜሪካ፣ እስራኤል - ኢራን ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚዋ በብርቱ ሊፈተን እንደሚችል በነዳጅ ማቅረብ ዘርፍ የተሠማሩ ሰው ሥጋታቸውን ገለፁ። ጦርነቱ "የዓለም የንግድ ሥርዓትን አዛብቷል" ያሉ አንድ ተንታኝ በበኩላቸዉ"ጦርነቱ ቢቋጭ እንኳን ጉዳቱ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው" ብለዋል።
-
-10
ውይይት፤የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 8 የስልጣን አመታት ሲቃኙ
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዶክተር ዓብይ አህመድ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ወደ መንበረ ስልጣን መጥተዋል። የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት የኢህአዴግን አመራር ይወቅሱ በነበሩ በብዙዎች ዘንድ የለውጥ ተስፋ አሳድሯል።ያም ሆኖ፣ መንግስታቸው እንዳጀማመሩ አለመቀጠሉ፤ የነበረው የለውጥ ተስፋ መደብዘዙ ይነገራል።
-
-11
ሕወሓት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለአንድ ዓመት በመራዘሙ ተቃወመ
ህወሓት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለአንድ ዓመት መራዘሙ በፕሪቶሪያው ግጭት የማቆም ስምምነት ፈራሚዎች ውይይት ያልተደረገበት፣ ከእውቅናየ ውጪ የተላለፈ እና የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል ውሳኔ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል አለ።
-
-12
በታይላንድ ሱፐር ማርኬት ውስጥ 1000 ዶላር ይከፈላችኋል ተብለው በካምቦዲያ የታለሉ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ
በታይላንድ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ትሰራላችሁ በሚል ተታለው ሄደው ካምቦዲያ የሚገኝ የአጭበርባሪዎች ማዕከል ውስጥ ራሳቸውን ያገኙ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተሞክሮዋቸውን አጋርተውናል። ለአራት ወራት ያህል በግጃጅ ህገ ወጥ ስራ እንዲሰሩ ተደርገው ነበር።
-
-13
ጄኔራል ታደሰ ወረደ በኃላፊነት መቀጠል ላይ የተሰጡ አስተያየቶች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንቱን የዛሬ ዓመት ሲሾሙ "የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት" ለማሳካት እንደምጠቅም ጠቅሰው ፕሬዝዳንቱ "እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ምኞታቸውን ገልፀው ነበር።
-
-14
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ
የዓለም የቱሪዝም፣ የዓየር መንገድና የሆቴል ኩባንዮች ከስረዋል።የከፋዉ ኢራን የሆርሙስ ወሽመጥን መዝጋትዋ ነዉ።የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ ዘይት፣ የማደበሪያ ንጥረ ነገር፣ ማዕድናት፣ የግብርና ዉጤቶችና ሌሎች ሸቀጦች የሚተላለፍበበት መስመር በመዘጋቱ ጦርነቱን የከፈቱት የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤልን ጨምሮ የዓለም ምጣኔ ሐብት እየተሽመደመደ ነዉ።
-
-15
84ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል
84ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል ዛሬ ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተከብሯል። የፋሽስት ጣልያን መንግሥት ኢትዮጵያን ዳግም የወረረበትና ከአምስት ዓመታት የአርበኞች ተጋድሎ በኃላ ተሸንፎ የወጣበት ይህ ዕለት፣ በወራሪው ኃይል ወርዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም በክብር የተሰቀለበት ነው።
-
-16
82 ኛዉ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል በድምቀት ተከበረ
ኢትዮጵያ ከጣሊያን ዳግማዊ ወረራ ተላቃ በ1933 ዓ.ም. ከአደዋ ድል በኋላም ዳግም ነጻነቷን ያረጋገጠችበት እለት የሚታወስበት የአርበኞች ቀን ዛሬ አዲስ አበባ በአርበኞች ሃውልት እለቱ ለ82ኛ ጊዜ ነው ታውሶ የዋለው፡፡ ዕለቱን በማስመልከት ማለዳ ላይ መድፍ ተተኩሷል፡፡ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር አርበኞች አደባባይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡
-
-17
78ኛው የኢትዮጵያ የድል ቀን
የኢትዮጵያ አርበኞች ከአምስት ዓመታት ዉጊያ በኋላ የኢጣሊያ ወራሪ ጦርን ድል ያደረጉበት 78ኛ ዓመት በዓል ዛሬ በመላዉ ኢትዮጵያ ተከብሮ ዋለ።
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Loading similar podcasts...